ከቴዲ አፍሮ ዘመቻ በስተጀርባ!
አንድ ጊዜ አንድ እራሱን እየተቆጣ ተመርጫለው የሚል ሬድዮ ጣቢያ ላይ የይቅርታና የእርቅ ፕሮግራም አዘጋጅ ሆኜ ወቅቱ ፕሮግራሙ ለመጀመሪያ ጊዜ ለህዝብ ሊቀርብ የነበረበት ቀን ነበርና የፕሮግራሙን
ፓኬጅ(ተቀርፆ የተዘጋጀ የሬድየ ፕሮግራም)እንዲተላለፍ ለቴክኒሻን
ሰጠው፡፡ ከተወሰነ ሠዓታት በኃለ ፕሮግራሙ አየር ላይ ሲውል ለመከታታል
ሬድዮ ጣቢያው ስመጣ ቴክንሻና የፕሮግራም መግቢያ የሆነው ዘፈን በኃላፊ
መቀየር አለበት ተብላል አለችኝ፡፡ ምንድን ነው ነገሩ ዘፈኑ እኮ ለፕሮግራሙ
መክፈቻ ተስማሚ ነው፣ በዚህ ፕሮግራም ላይ
ደግሞ መግባባትን፣ይቅርታንና እርቅን የሚሰብኩ ዜማዎች እንደምናቀርብ ነው
በፕሮጀክታችን ላይ ያቀረብነው ይሄ ዘፈን ደግሞ ተገዳደሉ
የሚል አይደለም ታረቁ እንጂ እንጂ አልኩ፤ ወቅቱ የአዲስ ዘመን አይደለም አይተላለፍም ተባልኩ፡፡ እረ ስለ አዲስ ዘመን ብቻ
አይደለም የሚያወራው መሰረታዊ መልዕክቱ ጊዜው የእርቅ ነው
የሚለው አልኩ፤ (ልክ እነድ የተሃድሶ ዘመን እነደሚባለው እንዲወሰድልኝ ቃላቶቹን እየቀለጽኩ)
የሚሰማኝ ጠፋ፡፡ ወዲያው በዚህ ሬድዮ
ጣቢያ መሥራት ፈታኝ እንደሚሆን
ተገነዘብኩ በርግጥም እኔና ባልደረቦቼ ብዙ ፈተነን፡፡ እንደዚህ አይነት ውጣ ውረድ በመንግሰትም
ይሁን የመንግስት ደጋፊ የሆኑ መገናኛ ጣቢያዎች ላይ ከጀርባ የሚሰሩ የተለመዱ ህግ የሌላቸው እስር ቤቶች መሆኑአቸውን ሬድዮ ፕሮግራም የማዘጋጀት ልምድ ያላቸው ባለሞያዎች የለመዱት ችግር
ነው፡፡ ለግንዛቤ እንዲረዳን አይተላለፍም የተባለው ዘፈንን የግጥም መልዕክት አስቲ እንየው፡፡
ምልኤላዊው ዘመን የአምላክ በረከቱ፣
በኢትዮጵያትንሳኤ ዘመነ..ው ዕለቱ
ስትሰሙ መለከት ወደ ምስራቅ ተመልከቱ!
እነዚህ ስንኞች የግድ ተሃድሶ
የሚል ቃል ይጨመርበት ካልተባለ በስተቀር ወይም እነሱ ካላሉት በስተቀር ሌላ ትረጉም የሚሰጥ ካልሆነ በስተቀር ስለ ኢትዮጵያ ትንሳኤ
ነው የሚያወራው፡፡ አሁንም ዚህው ዜማ ሌላ ስንኝ ልጨምር፤
ወዲህ ወዲህ ና ተው ያገሬ ሰው ፣
ሰው ሀገር ሆንህ ሆድክን አይባስው፤
ስንኮራረፍ ጠላት ይስቃል፣
የአገር ሰማይ በማን ይደምቃል፤
ስማህ
ስጠራ በዚህ ማስንቆ፣
ይታወቅ እንጂ ሁሉም ሰው ታርቆ፡፡
ይህ እንግዲህ ገልብጠን ካላየነው በስተቀር በስደት
ያላችሁ ወገኖቼ ሰው አገር ሆናችሁ ሆድ አይባሳችሁ ወደ አገራችሁ
ግቡ፣ስንኮራረፍ ጠላት ይስ ይለዋል፣ ስጠራህ በማሰንቆ ስማ ሁሉም
ሰው ታርቆ ይታይ ነው የሚለው፡፡(በእርግጥ ይህ ሬድዮ ወይም ቴሌቪዥን ቢሆን ጋዜጣ ሆነ እንጂ እንዴት የዜማውን ወደር የሌለው መሆኑንን
በድምጽ ከቅንብሩ ጋር በማስማት ምስክርነታችንን እንሰጥ ነበር)
ታዲያ እንግዲ ይህ ዜማ ነው አዲስ ዘመን አይደለም አይቀርብም የተባለው፡፡ ጉዳዩ የአዲስ ዘመን ጉዳይ እንዳልሆነ ስሌት ሳያስፈልገኝ ተረድቸዋለው ቢሆንም ለሬድዮ
ጣቢያ ኃላፊም ለእኔም የሚመጥን ምላሽ አይደለም አሁንም ጥቂት ስንኞች ልሰንዝር፡፡
አርንጋዴና ቢጫ ቀይ አርማው፣
ከፍ ይላል ገና ወጥቶ
ከማማው፤
ሰለሞን አለ ጊዜ ለኩሉ፣
ይሰግድልሻል የናቀሽ ሁሉ፤
አሳልፈናል ክፉ ደጉን፣
ቃል ኪዳን አለው እንዳይለየን፤
ባንድራችን ከማማ ላይ ወጥቶ ከፍ ይላላ የናቁሸ
ሁሉ ይሰግዱልሻል ማለት ያስከፋ ይሆን! አገር ለናቀ ሰው ካልሆነ
በስተቀር፡፡ ስንኞቹ በእርግጥ ስለአገር ከወሬ የዘለለለ ስሜት ለሌለው ወይም በአገር ስም ለሚነግድ ሰው እውነተኛ አገር ወዳድ በስሜት ተውጦ ስለአገር
ሲያወራ እረፍት ሊነሳ ይችላል፡፡
የቴዲ አፍሮ ዘፈንኖች እንደዚህ የሰውን ስሜት መግዛት የሚችሉ ዘፈኖች
ናቸው፡፡ ከግጥም፣ከዜማ ከቅንብርና ካዘሉት ጠንካራ መልዕክት አንጻር
ስናይ ይህ ዜመኛ የሚስተካከለው የለውም ማለት መሬት የወደቀ እውነት
ነው፡፡ ቴዴ አፍሮን በአካል አላውቀውም፣ የእርሱን የሙዚቃ ዝግጅቶችንም
አይቼ አላውቅም፣ ተሳትፌም አላውቅም በምንም አጋጣሚ ተገናኝቼው አላውቅም፣ ግን ሙዚቃውን ሳዳምጥ ስሜቴ እንደሚሰጠኝ
መናገር እወዳለው፡፡ ወይም ይሄ ስሜት ሰዋሪነቱ የአደባባይ ሚስጥርነቱን ከብዙዎች ተረድቻለው፡፡ ለዚህ ነው ከፍተኛ ተወዳጅነት በህዝቡ መከካል ያገኘው፣ ለዚህ
ነው ሰው እሱን አትንኩነብኝ የሚለው፡፡ ይህ ሰው የሚማርክ ድምጽ
ስላለው፣ ስነ ግጥሞቹ ጠንካር ስለሆኑ፣ ዜማው በራሱ ስለሚናገር፣
የሙዚቃ ሥራዎቹ በአብዛኛው የእርሱ የአህምሮ ጭማቂ ውጤት መሆኑ፣
የተመረጡ አቀናባሪዎች ስለአሉት፣ ብቻ አይደለም የሚወደደው፡፡ የአልበሞቹ
ጭብጦች ፍቅር ናቸው፣ ሀገር ናቸው፣ሰላም
ናቸው፣ ነጻነት ናቸው፣በጥናት የሚሰሩ ናቸው፣ ህሊናዊ መሆንን የሚሰብኩ ናቸው ለሆዳሞች ህሊና ለሌላቸው
ጣር ነው
የሚፈጥሩት፡፡ ታገሱኝና አሁንም ከሌላ ዜማው ደግሞ ተጨማሪ
ስንኝ ላስነብባችሁ፡፡ ሰላም ይሰኛል ስንኙ፡፡
ዋሽቶ ለመኖር አፌ አይችልም ከቶ፣
ታምኖ ይኖራል እንጂ ያለውን በልቶ፤
ደልቶኝ የሞላ ኑሮ መኖር ባልጠላም፣
ገንዘብ ለማግኝት ብዬ አላጣም ሰላም፣
እኔ አላጣም ሰላም፣
አላጣም ሰላም እኔ አላጣም ሰላም፡፡
ታምኖ ይኖራል እንጂ ያለውን በልቶ፤
ደልቶኝ የሞላ ኑሮ መኖር ባልጠላም፣
ገንዘብ ለማግኝት ብዬ አላጣም ሰላም፣
እኔ አላጣም ሰላም፣
አላጣም ሰላም እኔ አላጣም ሰላም፡፡
በቀላሉ ዋሽቶ መኖር ጠቃሚ እንዳልሆነ ሰላም
እንደሚነሳ የሚሰይ ዜማ ነው
ታዲያ
ለምን ዘመቻ?
አቅምና
ተስጥኦ
ከላይ
ለማሳየት እንደመኮርኩት የቴዎድሮስ
ዜማዎች በአብዛኛው የአገር ፍቅርን
የሚሰብኩ መልካምነተን የሚያወድሱ፣ ለሆድ መገዛት የእንሰሳት ባህሪ መሆኑን የሚያመላክቱ፣ በድህነት በህሊና መኖር የሰላም ባለቤት እንደሚያደርግ፣ ፍቅር እንደሚያሸንፍ
፣ተስፋ ማድረግ እንደሚያስፈልግ በመግለጽ አድማጩን የሚያበረቱ፣ የህብረተሰቡን እውነተኛ ስሜት
ፈልቅቆ በማውጣት ለህብረተሰቡ
በተለገሰው ተስጦ ስሜት በሚገዛ መልክ የሚቀርቡ፣
ለውጥ የማያመጡ መሪዎችን በድፍረት የሚገስጹ፣
ስንኞቹ ጨቋኞችን በእሳት አለንጋ የሚገርፉ፣ ግፈኞችንና አሽከሮቻቸውን
ተግባራቸውን በመጠቆም በቆሙመት የሚያርዱ፣ ታሪክን የሚያውጁ፣ አለምግባባትን
የሚያስታርቁ፣ወዘተ ናቸው፡፡ ከጥቁር ሰው
አልበም ዜማ አንድ ሁለት ስንኝ ማሳየት አባባሌን ያጠነክርልኛል ብዬ
ስለማስብ የተወሰነ ላክል፡፡
ጊዮረጊስ ፈረሱ ቆሞ ሳይ፣
ድል ቀናኝ ሳልል ዋይ(2)
አባቴ ወኔውን ተኮሰው፣
ምንሊክ ጥቁር ሰው፤
ዳኛው ያሉት አባ መላ ፊት/ ሐብቴ ዲነግዴ፣
ስልፉን በጦር አስምረው ፊት ሆኖ በዘዴ፤
ሳልል ዋይ፣
ሳልል
ዋይ፡፡
ምኒሊክ ጥቁር ሰው ወኔን ይጭራል ዋይ! ዋይ!
ሳልል በዘዴ ድል ቀናን በማለት የምኒልክን ጥበብ ጀግንነት በማሰየት በሚኒልክ ላይ የሚነሳውን ከኦሮሞ ጋር የተያያዘ አሉታዊ ጉዳይ በጥበብ ከኦሮሞ
ህዝብ ጋር ለማግባባት ዜማውን በኦሮምኛ ስልት መሀል መሀል ላይ የኦሮምኛ
ግጥም በማስገባት ሰላም ለማውረድ ሲጥር ይታያል፡፡
ወይ ሳልላት ብቅር ያኔ፣
እኔን አልሆንም ነበር ያኔ፤
ኢጆሌ ቢያኮ ጀጀባዳ መሌ፣
ጀዴቶ ከኤ ያገሬ ኮበሌ፤
ዱበት ኢንደዴምኑ እልከንተኤ ጉያ፣
ዲናፍ ኢላኑ ኢትዮጵያ፡፡
ጀዴ!
ስብዕና
ቴዎድሮስ በግል ባህሪው ፍጹም ነው እንከን የለበትም ብለን ለመናገር የሚከብድ ቢሆንም
በተለይ በአገር ጉዳይ ጠንካራ ስብዕና እና አስተዋይ አህምሮ እንዳለለው መናገር ይቻላል
፡፡ ይህ
ሰው ህዝቡን አክባሪ፣ ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ሞያውን የማያውል፣ ገንዝበ የማይደልለው፣ እያንዳንዱ እንቅስቃሴውን እንደ መልካም መሪ ከሚወደው ህዝብ
ፍላጎትና ጥቅም ጋር የሚያይይዝ፣
(በአሁኑ ዘመን ቀላል የማይባለ የፖለቲካ መሪዎች፣
ታዋቂ ሰዎች ፣ሙህራኖች ባለሀባቶች፣ የህዝብ ናቸው የሚባሉ የኪነጥበብ
ሰዎች ጓዛቸውን ጠቅልለው ወደ ምንም
አላየንም ቡድን ሲጠቃለሉና ሀሰት ሲሰብኩ በነፈሰበት
የማይነፍስ ጸንቶ የቆመ የኪነጥበብ ሰው ነው፡፡ ) በተገኘው
አጋጣሚ መልካም ሥራ በመስራት ቀናኢነቱናና
አርአያነቱን የሚያሳይ ነው፡፡
የህዝብ ፍቅር
የዕድሜ
፣ፆታ ፣የሃይማኖት፣ የማህበራዊ ማንነት፣ የሞያ አይነት፣የእውቀት ደረጃ ሳይወስነው
ከፍተኛ የሆነ የህዝብ አድናቆትና ድጋፍ ያለው ነው፡፡ በእሱ ዝግጅቶች፣ በእርሱ ሙዚቃዎች ሰዎች በስሜት ይናጣሉ፣ እራሳቸውን ወደ ውስጥ ያያሉ፣ ስለፍቅር ስለሃገር ያስባሉ፣ በሰሜት ይተቃቀፋሉ፣ ኢትዮጵያዊነት ውስጣቸው ይሰርፃል፡፡ ህዝቡ
የእሱን ፍቅርና ለመግለጽና በዜማው የሚያስተላልፈውን መልዕክት ለመቋደስ የሙዚቃ አልበሙን በውድ ዋጋ ሆዱን እየራበው ስልፎ ይዞ
በመግዛት አክብሮቱን ያሳያል፡፡
በስተጀርባ
ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም ሚስጥሩ የጠፋቸው
ባይሆንም ቴዎድሮሰ ካሰሁን ምንድን ነው ጥፋቱ? ብለው በቴዎድሮስ
ላይ የተከፈተውን ዘመቻ ምክንያት በማድረግ ባለፈ ሳምነት በአንድ መጽሔት ላይ ለፃፉት መጣጥፋቸው
በተወሰነ መልኩ ነገሩ እንደዚህ ነው
ብዬ እግረ መንገዴን መልስ ልስጥ፡፡
ይህ ሰው ከላይ
በገለጽኩት መልኩ የሰው ፍቅር ያለው ከሆነና ለህሊናው የማደር ምልከት ከሆነ፣ ለህሊናቸው የማያድሩ ሆዳቸውን ለመሙላት ብቻ
ቆርጠው የተነሱ፣ ሀገር ከኔ ወዲያ ለአሳር የሚሉ፣ታሪክ የሚያጠፉና አርቴፊሻል ታሪክ በእጅ የሚያስዙ፣ በህዝቡ የሚቆምሩ፣
የሀገር አንድነት ስጋታቸው የሆነ፣ ዓላማቸው ገንዘብ መሰብሰብና ገንዘብ መሰብሰብ ብቻ የሆነ፣ በዜማዎቹ የደቆሳቸው ግለሰቦችና ቡድኖች
ቴዎድሮስን ለማዳከም ሞራሉን ለመንካትና ተቀባይነት ለማሳጠት ቀን
ተሌት አይሰሩም አጋጣሚዎችን አይጠቀሙም ማለት የማይቻል መሆኑ የዘመቻው
መሰረታዊ ምክንያት ነው፡፡
እነዚህ
ናቸው እንግዲህ መልካቸውን እየቀያየሩ፣ ወንበራቸውን እየተጠቀሙ
ዜመኛውን ለማንኳሰስ ከዚህ ቀደም እንዳንኳሰሷቸውና እንዳንበረከኳቸው የተለያዩ ሰዎቸ ለማንበርከክ በተለያየ አቅጣጫ አስደናቂ ድራማ የሚሰሩት፡፡
አሁን እየተቃረበ ለአለው በ2007 ምርጫ ይህ አርቲስት ወቅታዊ ሁኔታዎችና
መሬት ላይ ያለውን ተጨባች ሁኔታ በዜማው ቀምሮ
የመስራት አቅሙን በመጠቀም እርስ በእርስ መቆራቆስ የስራቸው
ዋነኛ ክፍል
ለአደረጉት ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሆነ የሚያግባባ አጀንዳ ይሰጥብናል፣ የሚያደንቀውን ህዝብ አስተውል፣ አትታለል፣
ንቃ፣ አጋጣሚህን ተጠቀም ብሎ አመራር ይሰጥብናል ብሎ የገዢው ፓርቲ ቀድሞ የቤት
ሥራውን እየሰራ ነው ብሎ መጠርጠርም ጤነኝነት
ነው እላለው፡፡ እንዲህ አይነት ለክፋት የሰለጠነ ዘመቻ ካለተኬደበት ሌላው አማራጭ በዓል
ሲቃረብ ደጋጋሚ የሌቦነት ልምድ ያላቸውን
ሌቦች ህብረተሰቡ በዓሉን በሰላም እንዲያሰልፍ
ከየአሉበት ፖሊስ ሰብስቦ በማሰር ከበዓል በኃላ እንደሚለቃቸው፤ የምርጫ ወቅት ፈታኝ የሆኑ
ሰዎችን ቢያንስ ምርጫው እሲኪያልፍ
አንድ ምክንያት አደራጅቶ መሰብሰብ
ያስፈልጋል ብሎ ወደ ዘብጥያ ካልተጣለ በስተቀር ፡፡
ሲጠቃለል
ቴዲ አፍሮ
ዘፈኑ የማይጥማቸው፣ ለሆዳቸው የሚዘምቱ፣ጥቅማቸውን የሚያሳድድዱ ስለለሀገር መስማት የማይፈልጉ ግለሰቦች ወይም ቡድኖች ምንም
ጊዜም ቢሆን መልካቸውን እየቀያየሩ ዘመቻ ማድረጋቸው
የእህል ውሃቸው ጉዳይ ነው፡፡ ቴዲ በእነዚህ ቡድኖች ላይ ጠንካራ መልዕከት ያዘሉ፣ የሚያርዱ ዜማዎች ወይም ስጋት የሚፈጥሩ
ዜማዎች ማቀንቀን እስካላቆመ ድረስ በተገኘው አጋጣሚ እርሱን መታነኮሳቸው
የማይቀር በመሆኑ፤ ቴዲ ለዚህ አይነት ደካማ ወጥመድ ቦታ ሳይሰጥ የሚጠበቅበትንና የህዝቡን ስሜትን ተፈጥሮ በለገሰችው
ተሰጥኦ በመጠቀም የበኩሉን አስተዋፆ ማድረግ የእርሱ የህልውና ጉዳይ መሆኑን ማስገንዘብ እወዳለው፡፡ ብዙ ቴዎድሮሶችም እየተፈጠሩ እንዳለ እንደሚፈጠሩም
እያየን ነው፡፡
እነ በደሌም ሆነ ኮካኮላ አርቲስቱ ተወዳጅነቱን ከግምት በማስገባት በሙዚቃው
ስራው የኢትዮጵያን ህዝብን እንደገዛ በመረዳት ምርታችንን በአርቲስቱ ዝና ጥላ ሥር እናሻሽጥበታለን
ብለው በሚለዮኖች ብር ክፍያ ውል ከተዋዋሉ በኃላ በቂ ባልሆነ ምክንያትውላቸውን ማፍረሰቸው የእርሱን ስሜት፣ ዕውቅናን
ለማዳከም የወሰዱት እርምጃ ላለመሆኑ ማሳመኛ አላሳዩንም፡፡ በተጨማሪም የዘማቻው አካል ስላለመሆናቸው ጥያቄ እንጠይቃለን፡፡ በሌላ
ማሊያ እነእርሱው እየተጫወቱ ስላለመሆናቸው እንደ ሰው ካልጠረጠርንም
የዋኽ! ልንባል እንችላለን፡፡
በዝራው አሻግሬ
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ