ረቡዕ 30 ኤፕሪል 2014

የኢትዮጵያ መሪዎች በቃላት የመሸነቋቀጥ !.......

የመሪዎች በቃላት የመሸነቋቀጥ  ማክተም ምልክት!
    
     ባለፈው ሀሙስ 26ኛው መደበኛ የተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለፓርላማው  ባቀረቡትየሥራ ሪፖርት ላይ ከዚህ በፊት ባልተለመደ መልኩ እጥፍ ልመልስ አይነት በቃላት መሸነቋቀጥና ማናናቅ፣ አሽሙርና ተረት እምብዛም ያልታየበት ሪፖርትና የምላሽ  ሂደት ነበር የአየነው ለማለት ይቻላል፡፡
   በዚህ ጹህፍ  በሪፖርቱ ላይ ይህ ትክክል ነው ይሄ መሬት ላይ  ያልወደቀ  ሪፖርት  ነው ወይም ምላሹ ተገቢና ሀቀኛ  ነው ወይም ለመመለስ ተብሎ የተመለሰ አሊያም ዙሪያ ጥምጥም  መልስ  ነው  በማለት  አስተያየት ለመሰንዘር  አይደለም፡፡  ይልቁንስ  ከላይ  እንደገለጽኩት  ብዙ ተረት ያልበዛበትና ህዝቡን ያስቀይማል የሚል አስተሳሰብ የሌለበት  የዘለፋ ንግግሮች  አለመታየታቸው ነው፡፡

   አሁን  አሁን  የፓርላማ አባላቶች ጥያቄ አቀራረብና  አስተያየት  አሰጣጥን  በሦስት  ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡   አንደኛው ጠቅላይ  ሚኒስትሩ  የተናገሩትን የሚደግፍ  ጥያቄ የሚጠይቁ(አነሳሳቸው የመጠይቅ  ይመስላል  ግን  ተቃራኒ  የሆነ ሰው  እንዳይጠይቅ ወይም ይችን  ረሳት  አይነት አስታዋሽ ጠያቂ) ወይም አስተያየት  የሚሰጡ፤ ሁለተኛው በምስጋና በተለሳለሰ  ስሜት ወይም  በመቅለስለስ ጥያቄ ወይም አስተያያየት የሚጀምሩና  በዚሁ ስሜት ችግሮቹን  እየተቅለሰለሱ የሚጠይቁ ወይም የሚጠቁሙ፤  ሦስተኛው የአቶ  ሰይፉ  ግርማ  ምድብ  ሲሆን  በእሳቸው አስተሳሰብ  ምስጋና ይገባዋል የሚሉትን  በማመስገን  የመንግስት ችግሮች ናቸው የሚባሉትን በቀጥታ ወይም ችግሩን  አጉልቶ በሚያሳይ  ቋንቋ የሚገለጽበት የጥያቄና  የአስተያየት ምድብ   ነው፡፡

     በሐሙሱ ስብሰባ ለይ ዘውትር ከምናየው የተወካዮች ምክር ቤት በቃላት  የመወራረፍ ባህል ወጣ ያለ ሁኔታ  አይተናል፡፡  ጠቅላይ  ምኒስትር   ኃ/ማርያም  ቀደም  ሲል  ከምናውቀው የመንግስት  ወይም የኢህአዴግ  ባለሥልጣኖች  በተለይ  ድርጅቱ  በቀናነት የማያያቸው የህብረተሰብ  ክፍሎች  ሆነ የተቃዋሚ   ሃይሎች  ላይ  በአጋጣሚው በማያያዝ  የሚያስተላፉትን ሽንቆጣ ፣አንዳንዴ ማስፈራራት ባልተለመደ  ሁኔታ የተላቀቀ ሪፖርት ነው በማቅረብ  የምክር  ቤቱን ውይይት  ሠላም  የማድረግ  ሚናቸውን  የተጫወቱት፡፡   በመቀጠልም   አቶ ግርማ  ሰይፉ ከወትሮ የተለየውን  አቀራረብ በማድነቅ  አልፎ አልፎ  በቃላት  ለመሸንቆጥ ከሞሞከራቸው  በስተቀር በሠላማዊ ሁኔታ  ውይይቱ እንዲቀጥል የራሳቸውን አስተዋፆ አድርገው ጥያቄያቸውን በመሰንዘር ያጠናቀቁ  ሲሆን  ከምክር ቤቱ  ጥያቄ  በኃላ የማጠቃለያ  ሀሳባቸውን  የሰጡት  ጠቅላይ  ሚኒስትሩ  በቃላት  ለመወራረፍ  የማይፈልጉ  መሆናቸውን ለተሰነዘረው  አሽሙር ምላሽ  ሳልሰጥ ወደ ጉዳዬ  እገባለው  ብለው ለተነሳው  ጥያቄ  ብቻ የራሳቸውን መልስ  በመስጠት ንግግራቸውን  ቀጠሉ፡፡ ጠ/ሚኒስትሩ መልስ  ነው  የሚሉትን  ምላሽ  እየሰጡ  በስተመጨረሻ   ለመመለስ  የተዘጋጁበትን  ከመልካም  አስተዳደር  ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን  ለመመለስ  ሲሉ ቀደም  ሲል  ያሳዩ  የነበሩት ስሜት  በመግታት፤ በስተመጨረሻ  ላይ ብቻ ከመልካም  አስተዳደር  ጋር በማያያዝ የፓርቲዎች  ምክር ቤት አባል  ባልሆኑ የተቃዋሚ ፓርቲዎች   በሚል ምክንያት የቃላት  ሽንቆጣ አሳተይዋል፡፡

 እርግጥ  ነው በዕለቱ   በአንድ  ሳምንት  ተበጥብጦ የማይጠጣ ነው  ዲሞክራሲ፤ ቀይ ምንጣፍ  ዘርግተን፤  አሸባሪ ድጅቶች  ጋር  ሶኬት  አድርገው ስለሚንቀሳቀሱ  ሶኬቶ  ይነቀልባቸዋል፣ ዕድለቢሱ የመጨረሻ ባለኮንደም ማነው፣ አዲስ  የምንጽፈው  ነገር  የለም የሚሉ  ከዚህ  ቀደም  የተራረፉ የቃላት ሽንቆጣዎች  በስብሰባው ላይ የተነሱ ቢሆንም በአብዛኛው ቀደም ብለን ከምናያቸው የፓርላማው መዘላለፍ  የመላቀቅ  አዝማሚያ  የአየንበትና  መሪዎች ከመዘላለፍ የነፃ እና የቃላት መሸንቋቀጥ የሌለበት ውይይት ወይም ክርክር ማድረግ መለመድ ያለበት አዲስ ባህል መሆን አለበት እንላለን ፡፡

በቃላት  መሸነቃቀጥ ትርፍ  አለው  እንዴ?
 በመሰረቱ በክርክር  ወቅት ወይም በተቃራኒ ጥያቄና  መልስ ውቅት  የለሰለሰ  ንግግር አለመኖር ብዙም  አዲስ  ነገር  አይደለም ፡፡ ምክንያቱም  በተለይ በአንድ ጉዳይ ላይ የተለያየ  አቋም ያላቸው አካላቶች  መንፈሳዊ  አይነት ስሜት ያለው ንግግር  ያደርጋሉ ተብሎ አይጠበቅም፡፡ ቢሆንም  ግን  ኢትዮጵያዊ የመከባበር ሥነሥርዓትና ሥነምግባር ያለው  ህዝብን  የሚመራ ፣ከዚህ ህዝብ  ውስጥ  የወጣ ፣ እርሱ የሚናገረው  ንግግር ብዙዎችን  ሊያስተምር  ወይም  ሊያጠፋ  የሚችል  መሆኑን የተገነዘበ አርአያ የሚሆን መሪ በተቻለ መጠን መዘላለለፍ  በቃላት  መሸነቋቆጥ የሚመራው ህዝብ ከእርሱ እንዳይማር አርቆ  ማሰብ  አለበት፡፡   መሪ የመልካም  ተግባር አርአያ  መሆን  አለበት፡፡  አንድ  ጊዜ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር  በፓርላማ  ንግግራቸው ላይ ተሞዳሞዱ፣እየተመዶሞዱ  ባሉበት  በንጋታው አንድ የቀበሌ አስተዳደር  ጽ/ቤት በአጋጣሚ ሄጄ  የቀበሌው  ሊቃመንበር እየተሞዳሞዳችሁ እያለች በጠቅላይ ሚንስትሩ ሁኔታ በስልክ ስታወራ፤ እንደዋዛ የተወረወረ ቃል እንደወረደ እንዴት በቅጽበት እንደሚተገበር በገረሜታ  ነው  ያየሁት፡፡
  
የመሪዎች በቃላት የመሸነቋቀጥ  ማክተም ምልክት!
    
 በዝራው አሻግሬ
     Zirawashagre@yahoo.com

መሪ ታጋሽ መሆን የግድ  ያስፈልገዋል
 በእርግጥ  የምናወዳድረው  ባይሆንም ለምን  በቀላሉ ተወዳጅ  የሚባሉ  መሪዎች ምንድን  ነው  ተወዳጅ  ያደረጋቸው  ብለን  ብናስብ አንደኛው ታጋሽ መሆናቸው  ነው፡፡  ስሜታዊነትና የማንኛው ቡድን መሪነት አብረው  አይሄዱም፡፡  መሪ  በጭራሽ  ስሜታዊ  መሆን  የለበትም፡፡  ወይም  ስሜቱን  መቆጣጠር  መቻል  አለበት፡፡  ሰሜታዊ የሆነ መሪ የሚመራውን  ህዝብ በስሜት ላለመንዳቱ  ዋስትና  ማግኘት  ያዳግታል፡፡  ታጋሽ  ለመሆን መንፈሳዊ  መሆን  አያስፈልግም በመሪነት  ስብዕና፡፡ ስሜታዊ አለመሆን  ብስለትን  ያሳያል፡፡

ለፓርላማ  ንግግር  ተረት  ምን ይጨምራል?

ተረት  መተረት እንደ  የተሻለ ሰው የሚታይበት ቦታ  ቢባል ፓርላማ  ነው  ለማለት እየዳደን  ነበር ያለነው( በእርግጥ  በአሁኑ  የፓርላማ ውይይት  ከተሸሻሻሉ ጉዳዮች  ተራች አለመብዛቱ ወይም  ተረት ብዙ አለማያታችን ነው)፡፡  እንደ እኔ እንደ  እኔ ተረት መተረት የህዝቡ ችግር አይደለም፡፡ እሳት  ዳር  ተቀምጦ ተረት እየተረተ ወይም እየተተረተለት የኖረ ህዝብ  ይሄ ለእሱ ምኑ ነው!? ባይሆን ህዝቡ  መስማት  የሚፈልገው ለዕለት ከዕለት ችግሩ የመፍቴሔ አቅጣጫ  የሚያሳየው መሪ ነው፡፡
   ፓርላማ ውስጥ የሽንቁጣ ተረት ይተረታል የማያስቅም  ቢሆን ደጋፊዎች ይስቃሉ፣ያጨበጭባሉ ምንዓልባት አንዳንዱ ከእንቅልፉ ድንገት ባንኖ  ሁሉ ሊሆን  ይችላል የሚያጨበጭበው፡፡  ተረት  መተረት  ለማስረዳት  ዘና  ለማድረግም ይግባ ቢባል  እንኳን  አንድ ወገንን ለማጥቂያ እንደመሳሪያ የምንጠቀምበት  ክፉ ተረት  መሆን  የለበትም፡፡   ተረቱ  የተተረተበትን  ሰውን  ጨምሮ  በሆዱ  እውነቱን  ነው ከየት  አመጣው የሚያስብል አስተማሪ ተረት  ነው  መሆን  ያለበት፡፡ አለበለዚያ  በተረት ጥይት የምንቆሳሰል  ከሆነ  ለተከታዮቻችን  ሆነ ለመጪው ትውልድ መሪነት ከሥራ ብቃት ይልቅ  በተረት  ተቃራኒን ወገንን ጭንቅላቱን  መቀወር  ነው አላልንም  ልንል  አንችልም፡፡      

ሲጠቃለል!
 ባለፈ  ሀሙስ ያየነው በቃላት የመሸነቋቀጥ የፓርላማ አጉል  ባህል እያከተመ የመጣ የሚመስል ምልክት፤ ሽንቆጣ ሙሉ ለሙሉ ማክተሙን  በተሻለ  ሁኔታ በቀጣዩ 26ኛው ጉባዔ ላይ ተሰብሳቢዎቹ ሊያሳዩን ይገባል፡፡  ይህ ብቻ አይደለም የይምሰል ጠያቂና መልስ  ሰጪ ቁጥሩ እየቀነሰ መምጣት  አለበት፣ በደመነፍስ መደገፍና  መቃወም ቁጥር እየቀነሰ ወይም እየጠፋ  መምጣት  አለበት፣ የሀሰት ዳታ  ማቅረብ እየቀረ  መምጣት  አለበት፣ ከእንቅልፍ ተነስቶ ማጨብጨብ መቀረፍ  አለበት፣ የህዝቡን  ጥያቄ ጉያ ውስጥ  ወሽቆ ወንበር  አሙቆ መሄድም ሃላፊነት  አለመወጣት ስለሆነ ሊታሰብበት  ይገባል፡፡  

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ