ማንዴላ!!!
ጠላቶቹንም ጭምር በትዕግስትና
በፍቅር ያሸነፈ የሁሉም ሰው መሪ!
በዝራው አሻግሬ
በዚህ ሳምንት
ውስጥ ዓለም ዓቀፍ ሚዲያው ላይ ወደር የሌለው ሽፋን በማግኘት በደቂቃና በሰከንድ
ውስጥ ዜና ፣ዘገባ፣መጣጥፍ እና ዶክመንተሪ ፊልም ዘገባ
ሲካሄድባቸው የነበሩት አሁንም እየተዘገበላቸው
ያለው የደቡብ
አፍሪካው የነፃነት ታጋይ የኔልሰን ማንዴላ በ95 ዓመታቸው ባለፈው
ሳምንት ህዳር 27,2006 ዓ.ም ሐሙስ ዕለት
ከዚህ ዓለም በሞት መለያታቸው ነው፡፡
ማንዴላ ለአፍሪካ እንዲሁም ለዓለም መንግስታት መሪዎች አርአያ ሊሆኑ የሚችሉ መሆናቸውን የዓለም ህዝብ እንዲሁም የተለያዩ
መሪዎች ያለምንም ቀስቃሽ ስሜታቸው እየናጣቸው ማንዴላ የተለየ መሪ መሆናቸው አረጋግጠዋል፡፡
ማንዴላ ማናቸው? አስተዳደጋቸውስ እንዴት ነበር? ህይወታቸው ምን ይመስላል?
በተወሰነ እንመልከት፡፡
የማንዴላ ውልደትና
እድገት
ሮሊሂላላ ማንዴላ ሚቭዞ
በምትባል አንዲት ትንሽ መንደር ውስጥ ምባሺ ወንዝ ዳርቻ
ትራንስኪ ውስጥ እ.ኤ.አ ሐምሌ 18, 1918 በደቡብ አፍሪካ
ተወለደ ፡፡ ሮሊሂላላ በዞሳ ቋንቋ ቃል በቃል
ሲተረጎም የባህር ዛፍን ቅርንጫፍ ለመገንጠል መታገል ማለት ሲሆን በተለምዶ
አዋኪ ዉም ረባሽ በሚል ይተረጎማል፡፡
የኒልሰን ማንዴላ አባት
የጎሳ መሪ እና የጎሳ መሪዎች መማክርት ሆነው ለበርካታ ዓመታት ያገለገሉ ሲሆን፤ሁለቱንም ሥልጣናቸውን
በጊዜው ከነበሩ የቀኝ ገዢዎች ጋር በፈጠሩት እስጣ ገባ አጥተውታል፡፡
በዚህ ጊዜ ማንዴላ ብቸኛ ልጅ
ነበር፡፡ የአባቱ ከስልጣን መነሳት እናቱ ቤተሰቡን ከሚቬዞ በስተደቡብ የምትገኝ ኩኑ የምትበል ትንሽ መንደር ይዛ ለመዘዋወር ምክንያት ሆናት፡፡
በማንዴላ አባት ጋደኛ
ሀሳብ አመንጪነት ማንዴላ ሜቶዲስት ቤተክርስቲያን ተጠመቀ፡፡ ከቤተሰቡ የመጀመሪያው ትምህርት ቤት የገባ ልጅም
ሆነ፡፡ በወቅቱ በተለምዶ እንደሚደረገው እንዲሁም
በደቡብ አፍሪካ ላይ የእንግሊዝ
የትምህርት ሥርዓት ተጽዕኖ በማሳደሩ ምክንያት
የማንዴላ የመጀመሪያ መጠሪያ ሥሙ ኔልሰን እንዲሆን የማንዴላ መምህር ገለጹለት፡፡
ማንዴላ
በ9 ዓመቱ የአባቱ በሳንባ በሽታ መሞት የህይወቱን አቅጣጫ በአስገራሚ ሁነታ ቀይሮታል፡፡ ማንዴላ ጆንጊታባ ዳሊን ዲዬቦ በተባሉ የጎሳ መሪና አባቱ በህይወት
እያሉ የጎሳ መሪ እንዲሆኑ ሀሳብ ባቀሩቡላቸው ሰው እንደ ውለታ መሥራት አይነት በጉዲፈቻ ልጅነት ወሰዱት፡፡
ማንዴላ በትንሿ ኩኑ መንደር ያገኝ የነበረውን
እንክብካቤና ነጻነት ዳግም እንደማያገኝና የሚወዳትን
መንደር ተመልሶ ሊያያት እነደማይችል እያሰበ በስጋት ትቷት ተጓዘ፡፡
ማንዴላ የቴምቡላንድ ጊዚያዊ ከተማ
ወደ ተባለችው የንሳን ቤተሰብ አለቃ መኖሪያ ምኪኪዚዌኒ
በሞተር ባይስክል ተጓዝ፡፡ ማንዴላ
ምንም እንኳን የሚወዳትን ኩኑ
መንደር ያልረሳ ቢሀንም አዲሷንና ግራ የምታጋባውን ምኪኪዚዌኒ ከተማ በቀላሉ ተለማመዳት፡፡
ማንዴላ
የጎሳ መሪው የበኩር ልጅ የሆነው ጀስትስ እና ኖማፉ ከተባለች ሴት ልጁ
ያላቸውን አይነት ክብርና ኃላፊነት
እኩል ተሰጠው፡፡ ማዴላ ከቤተ መንግስቱ
አጠገብ በሚገኘው ባለ አንድ ክፍል ትምህርት ቤት
ውስት ገብቶ እንግሊዘኛ፣ ዞሳ፣ ታሪክና የህብረተሰብ ሳይንስ ትምህር ተማረ፡፡ በዚህን ግዜ ነበር ማንዴላ ስለ አፍሪካ ታሪክ የማወቅ ፍላጎት
ያደረበት፡፡
እ.እ.አ
በ1939, ማንዴላ የጥቁሮች ብቸኛ የከፍተኛ ትምህርት ማዕከል
በሆነው ፎርት ሐሬ ዩነቭረስቲ ኮሌጅ ገባ፡፡ በወቅቱ ፎርት ሐሬ
ዩኒቨርስቲ እንደ ኦክስፎርድና ሃርቫርድ ዩኒቭረዝቲ ጋር በእኩል
የሚታይና ከሰሃራ በታች ያሉ ሀገራት ምሁራንን ያፈራ ነበር፡፡ በዩኒቨርስቲው የመጀመሪያው ዓመት ቆይታው አስፈላጊውን ኮርሶች የወሰደ ቢሆንም ህብረተሰቡን
ለማገልገል እንዲረዳው በወቅቱ ለጥቁሮች የሚሰራውን ምርጥ ሞያ ተብሎ የሚወሰደውን የህግ ተርጋሚኒትና ጸሐፊ ሞያ በማጥናት የሮማን ደች ህግ ትምህሩት ላይ
ትኩረትን አደረገ፡፡
በዩኒቭርስቲ
ቆይታው ሁለተኛ ዓመት ሲሞላው የተማሪዎች ተወካይ መማክረት ሆኖ
ተመረጠ፡፡ በተወሰነ ጊዜ ተማሪዎች የሚቀርብላቸውን
ምግብና የተማሪዎች መማክርት ያለው ሥልጣንን
አስመልክቶ እርካታ የላቸውም ነበር፡፡ በምርጫው ወቅት አብዛኛው ተማሪ ጥያቂአቸው
ካልተመለሰ ምርጫውን ጥሎ ለመውጣት በእጅ ብልጫ
ወሰኑ፡፡ በዚህን ጊዜ ማንዴላ ከአብዛኛው ተማሪ ጎን በመሆን
ከተማሪዎች መማክርት ተወካይነት
ራሱን አገለለ፡፡
የዩኒቭርስቲው ኃላፊ ዶ/ር ኬር ማንዴላን
ከትምህርት ቤቱ በማባርር የተማሪዎችን መማክርት ተወካይነቱን የሚቀጥል
ከሆነ ትምህርቱን ሊያስቀጥልው እንደሚችል መደራደሪያ አቀረቡለት፡፡ ወደ ቤቱ ሲመልሰ
የጉዲፈቻ አባቱ በቁጣ አስተናግደውት የሚለውን
ሳያዳምጡ አቋሙን ቀይሮ ወደ ትምህርት
ቤቱ እንዲመለስ አዘዙት፡፡
የማንዴላ እስር
ጉዳይ
ማንዴላ ወደ መኖሪያ ቤቱ
ከተመለሰ ከጥቂት ጊዚያት
በኃላ የጉዲፈቻ አባቱ ሬጀንት ጆንጊታባ ሚስት
እንዲያገባ አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን ገለጹለት፡፡ የማንዴላ
የጉዲፈቻ አባት ማንዴላ የተስተካከል ህይወት እንዲመራ የራሳቸውን ዝግጅት
ትክክል ነው የሚሉትን ተግባር በማድረግ በሀገሩ
ባህል መሰረት አደረጉ፡፡ ይሀንን አስደንጋጭ ዜና የሰማው ማንዴላ
አሁን ያለው አማራጭ ትዕዛዙን አክብሮ
መቀበል ብቻ መሆኑንና ወጥመድ ውስጥ
እንደገባ ሲሰማው መኖሪያ ቤቱን ለቆ ጠፋ፡፡
ጉዞውን ወደ ጆሃንስበርግ
አድርጎም ዘበኝነትን እና ጸሐፊነትን ጨምሮ ኑሮውን
የተለያየ ሥራ በመስራት ይገፋ ጀመረ፡፡ በዊትዋትረሰታንድ ዩኒቭርስቲም ህግ ትምህርት ለማጥናት
ተመዘገበ፡፡
ወዲያውኑ
የዘአፍሪካ ናሽናል ኮንገረስ (ኤአንሲ) ውስጥ እ.ኤ.አ በ1942
በመቀላቀል የፀረ አፓርታድ ትግል እንቅስቃሴ በንቃት ይሳተፍ
ጀመር፡፡ በኤ ኤን ሲ ውስጥ የአፍሪካ ናሽናል ኮንግረስ የወጣቶች ህብረት የሚል ቁጥራቸው አናሳ የሆኑ የወጣት አፍሪካውያን ስብስብ
ነበር፡፡ የዚህ ህገብረት
ዓላማ ኤኤን ሲን የሰፊው ህዝብ ሥር ነቀል እንቅስቃሴ
ማድረግ፣ በሚሊየን የሚቆጠሩ በአገዛዙ ምንም ድምጽ የሌላቸውን
በገጠር የሚገኙ ጭሰኛ ገበሬዎችንና የሠራተኛው ክፍልን
የማጠናከርና የማብቃት ሥራ መስራት
ነበር፡፡ በተለይ ህብረቱ የኤኤንሲ ያረጀ የህዝቡን
ድጋፍ የማግኛ ዘዴው ውጤታማ አይደለም የሚል ነው፡፡ እ.ኤ.አ በ1942 ኤኤንሲ የወጣቶቹ
ረግጦ የመውጣት፣ የዓመጽ፣ የዓለመታዘዝና ያለመተባበር
የትግል ዘዴን የእኩል ዜግነት ፣የመሬት ክፍፍል ፣የንግድ ማህበር መብቶች፣ ነጻና አስገዳጅ የሆነ የህፃናት
የመማር መብት የፖሊሲን ግብ ይፋዊ
በሆነ መልኩ የራሱ የትግል ዓላማ አድርጎ ተቀበለው፡፡
ለ20
ዓመታት እ.ኤ.አ የ1952ቱን የትግል ዘመቻና እ.ኤ.አ የ1955
የህዝብ መማክርትን እንቅስቃሴን ጨምሮ ማንዴላ
በሠላማዊና ኃይል ያልተቀላቀለበት ትግል
በደቡብ አፍሪካ መንግስት
ላይ የሚደረገውን እንቅስቃሴ መርቷል፡፡ ማንዴላና
ታምቦ የህግ አገልግሎት ድርጅት የሚባል ፎርት ሄር ዩኒቨርስቲ
ሲማር በጉብዝናው ከሚያውቀው ኦሊቨር ታምቦ ጋር
በመሆን በጋራ ከፍተዋል፡፡ የህግ ድርጅቱ በቅማናሽና በነጻ የህግ አገልግሎት ድጋፍ ላልተወከሉ ጥቁሮች
ያደረግ ነበር፡፡
እ.ኤ.አ
በ1956 ማንዴላ እና 150 ሰዎች በፖለቲካዊ ምክክር በሚል
ምክንያት ክስ
ተመስርቶባቸው ታሰሩ፡፡ በዚህን ጊዜ ኤኤንሲ
አፍሪካውያኖች(Africanist) አዲሱ የጥቁር ታጋዮች(black
activist) ውልዶች ነን በሚሉና የኤኤንሲ የሠላማዊና የዝምታ
መንገድ ውጤት ዓልባ ሆኗል በሚሉ ሰዎች እንቅስቃሴ ነውጥ ውስጥ
ገብቶ ነበር፡፡ አፍሪካውያኖች ወዲያውኑ ከኤኤንሲ በመነጠል ፓን አፍሪካዊያን ኮንግረስ የሚል አቃቁመው ኤኤኒሲ ላይ
አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳደሩ ሲሆን ኤኤን ሲ አብዛኛው ታጣቂ
ደጋፊዎቹን አጥቶበታል፡፡
በ1961 ሃይል ያልተቀላቀለበት ትግል ያስኬዳል በማለት ሲሟገት
የነበረው ማንዴላ በስተመጨረሻ የትጥቅ
ትግል ብቸኛው አማራጭ ነው ወደ የሚለው ድምዳሜ ደርሶ ነበር፡፡ በማስከተልም ዩምኮንቶ ዊ ሲዚዊ ወይም ኤም ኬ
የተሰኘ አፓርታይድን ለመጣል የሚረዳ ሸማቂ ኃይል ከአቋቋሙት
መኃል ሆነ፡፡ በ1961 ማንዴላ የ3ት
ቀን ብሄራዊ የሥራ
ማቆም አድማ አቀናብሮ በቀጣዩ ኣመት ዓመጽ
በማስነሳት በሚል በ1963 ዓ.ም የ5 ዓመት የእስር ውሳኔ ተወሰነበት፡፡
በድጋሚ
ፍርድ ቤት ቀርቦ ማሴርና ፖለቲካዊ ጥቃቶች በሚል ክስ
እሱና አሥር የኤኤኒሲ መሪዎች የዕድሜ ልክ
እሥራት ተፈረደባቸው፡፡
ኒልሰም ማንዴላ ከ27 ዓመት የእሥር ቆይታው 18 ቱን ዓመትን በሮቢን ደሴት ነው ያሳለፈው፡፡
በእስር ቆይታው የሳምባ ነቀርሳ በሽታ ይዞት የበረ
ሲሆን እንደማንኛውም ጥቁር የፖለቲካ
እስረኛ በደካማ ህክምና አገልግሎት በእስር ቤቱ ሠራተኞች
ነበር የተሰጠው፡፡ ምንም እንኳን
በህመም ላይ ቢሆንም
ማንዴላ የህግ ትምህርቱን ከሎንደን
ዩኒቨርስቲ በተልዕኮ አግኝታል፡፡
እ.ኤ.አ
በ1981 የደቡብ አፍሪካ የደህንነት ወኪል በሆነው ጎርደን ዊንተር አማካኝነት በደቡብ አፍሪካ መንግስት
ማንዴላን ከእስር ቤት እንዲያመልጥ
ሁኔታዎችን በማመቻቸትና ከእስር ቤት ሊያመልጥ
ሲልነው በማለት በጥይት ሊመቱት ሴራ ተጎንጉኖለት
በእንግሊዝ የደህንነት ኣማካኝነት ከሽፋል፡፡ (ኢትዮጵያ ውስጥም
በኮልፌ ፈጥኖ ደራሽ የፖሊስ ማሰልጠኛ ተቋም የግድያ
ሙከራ የተደረገበት መሆኑ በቅርብ
ጊዜ እተገለጸ ያለ ዜና ነው፡፡ )
ማንዴላ የጥቁሮች የነፃነት ምልከት ተደርጎ
በዓለም ላይ መናኘቱ ቀጥሎ እርሱን የማስፈታት እንቅስቃሴዎች ተበራክተው ነበር፡፡
እ.ኤ.አ በ1982 ማዴላና ሌሎች የኤኤን ሲ መሪዎች ከደቡብ አፍሪካ
መንግስት ጋር ለመነጋገር
እንዲያመች ወደ ፖልስሙር እስርቤት ተዘዋወሩ፡፡ እ.ኤ.አ በ1985 ፒ .ደብሊው ቦሳ የትጥቅ ትግልን በማቆምንና ማንዴላ ለመፍታት
የፈለገ ቢሆንም ታሳሪዎቹ ሀሳቡን አጣጥለውታል፡፡ በአቅራቢያውና
በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በደቡብ አፍሪካ መንግስት
ላይ ከፍተኛ ግፊት ይደረግ የነበረ
በመሆኑ መንግስት ከማንዴላ ጋር ለመደራደር ብዙ ንግግር አድርጎ
ግን ምንም አይነት ስምምነት ላይ
አልተደረሰም፡፡ ይህ ድርድር ፒ ደብሊው ቦሳ ሥልጣናቸውን ለቅቀው ፍሬድሪክ ዊሊያም ዲ ክለርክ ፕሬዚዳንት በመሆን የማንዴላ ከእስር መፈታት እ.ኤ.አ
የካቲት 11,1990 ድረስ ድርድሩ አልተሳካም ነበር፡፡ ዲክሌርክ
ማንዴላን ከማስፈታት በስተጨማሪ
የኤኤን ሲ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ እገዳ እንዲነሳ እንዲሁም የፖለቲካ ቡድኖች
እንቅስቃሴ ላይ የተጣለው እገዳዎች እንዲነሳም
አድርገዋል፡፡
ከእስር መፈታትና የፕሬዚዳንትነት ጊዜ
ኒልሰን ማንዴላ ከእስር ከተፈቱ በኃላ ወዲውኑ ለውጭ ሃይሎች የደቡብ አፍሪካ መንግስት ህገመንግስታዊ ሪፎረም እንዲያደርግ ግፊታቸውን እንዲቀጥሉ ጥያቄያቸውን ያቀርቡ ጀመር፡፡ ከዚህው ጎን ለጎን በሰላማዊ እንቅስቃሴ ረገድና የኤኤኔሲ የትጥቅ ትግል የአብዛኛው ጥቁሮች በድምጽ የመወሰን መብት እስኪረጋገጥ ድረስ መቀጠል እንዳለበት አወጁ፡፡
እ.ኤ.አ በ1991 ማንዴላ የህይወት ዘመን ባልደረባው የሆኑት ኦሊቨር ታምቦ የአፍሪካን ብሔራዊ ኮንገረስ ሊቀመንበር ሆኖ ሲመረጡ ኒልሰን ማንዴላ ደግሞ ፕሬዚዳንት በመሆን ተመረጡ፡፡ ማንዴላ ከኤፍ ደብሊው ክለርክ ጋር ሁሉን አቀፍ ምርጫ እንዲካሄድ ድርድር ማድረግ ጀመሩ፡፡ በዚህ ወቅት ነጭ ደቡብ አፍሪካኖች ሥልጣን መጋራት የሚፈልጉ ሲሆን ጥቁሮቹ አፍሪካኖች ደግሞ ሙሉ በሙሉ ስልጣን መረከብ የሚፈልጉ በመሆኑ በዚህ ምክንያት በተለያየ ጊዜ ብጥብጥ እየተነሳ የኤኤኒሲ መሪዎችም መታሰራቸው አልቀረም፡፡
ማንዴላ በዚህን ወቅት ማንዴላ ሚዛናዊ የሆነ ፖለቲካዊ አቅም እንዲኖርና ህዝባዊ እንቅስቀሴውና የትጥቅ ትግሉ መካከል ድርድሩ ላይ ግፊት ነበር፡፡
እ.ኤ.አ
በ1993 ማንዴላና ፕሬዚዳንት ዲ ክለርክ አፓርታየድን ለመሰወገድ ባደረጉት
ጥረት በጋራ የሠላም ኖቤል ሽልማት
አግኝተዋል፡፡
ደቡብ አፍሪካ የራሷን
የመጀመሪያ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ አካሂዳ ግንቦት 10,1994 ኔልሳን ማንዴላ
በ77 ዓመታቸው የአገሪቱ የመጀመሪያ ጥቁር ፕሬዚዳንት
ሆነው የተመረጡ ሲሆን ዲ ክለርክም ምክትላቸው
ሆነው ተመረጡ፡፡
በዚሁ ዓመት
ማንዴላ በአብዛኛው እስር
ላይ በነበሩት ወቅት ጽፈውት
የነበረውን የነፃነት ጉዞ( Long
Walk to Freedom) የተሰኘውን የግል ታሪካቸው የሚያሳይ መጽሐፍ አሳተሙ፡፡
የማንዴላ ተግባራቶች
·
እ.ኤ.አ ከ1994 እስከ ጁን 1999 እ.ኤ.አ ማንዴላ
ከጥቂት ነጮች የአገዛዝ ሥርዓት ወደ
ብዙኃኑ ጥቁሮች እንዲለወጥ ከፍተኛ ጥረት
አድርጋል፣
·
ስፖርታዊ ዝግጅቶችን ጥቁርና
ነጭን የማግባቢያና የማስታረቂያ መድረክ አድርገዋል፣
·
ማንዴላ በእርሳቸው
የአገዛዝ ዘመን አገሪቱ ሊገጥማት
የነበረውን የኢኮነሚ ውድቀት ለመከላላከል ሠርተዋል፣
በእሳቸው የመልሶ ግንባታ የልማት ዕቅድ የጥቁር አሜሪካ
መንግስት ለዜጎቹ የሥራ ዕድል፣ የመኖሪያ ቤት አቅርቦትና
የጤና እንክብካቤ ለማመመቻቸት ችለዋልል፣
·
እ.ኤ.አ በ1996 ማንዴላ በአብላጫ ድምጽ
የሚመራ አዲስ ጠንካራ የማዕከላዊ መንግስት፣ የአነሳ ቡድኖች መብት የሚያከብር እና
የሀሳብ ነጻነትን የሚያረጋግጥ አዲስ ህገመንግስት ተግባራዉዊ እንዲሆን
አድርገዋል፣
·
በጡረታቸው ጊዜም በእርሳቸው ስም
በተቋቋመው ፋውንዴሽን በደቡብ አፍሪካ በየገጠሩ ት/ቤትና ክሊንክ እንዲገነባ አድርገዋል፡፡
·
በብሩንዲ የእርስ በእርስ ጦርነት በሸምጋይነት ሰርተዋል፣
·
በህይወት ዘመናቸውና
በትግል ሂደታቸው ዙሪያ የሚያትቱ መጽሐፍቶች
አበርክተዋል ለአብነት ያህልም ለነጻነት መንገዱ ጨርቅ አይደለም (No Easy Walk to Freedom)፣ ኒልሰን ማንዴላ(Nelson Mandela) መታገል ህይወቴ ነው(
The Struggle is my Life) እና የኔልሰን
ማንዴላ ተወዳጅ የአፍሪካ አፈታሪኮች
( Nelson Mandela's Favorite African Folktales) የተወሰኑት ናቸው፤
·
ማንዴላ እ.ኤ.አ ጁላይ 18,
2007 ዴዝሜንቱቱን ጨምሮ ታዋቂ የአገር ሽማግሌዎች ያሉበት ›
ሽማግሌዎቹ › የሚባል ቡድን ሰብስበው በኢሲያ ፣ሩቅ ምስራቅና አፍሪካ
ላይ ሰላምን፣ የሴቶች እኩልነትና የሰብአዊ ሥራ
ላይ ቀላል የማይባል ተግባር አከናውነዋል፤
·
ማክጋቶ የተባለው ወንድ ልጃቸው የሞተበትን የኤች አይቪ
ኤድስ በሽታን በመከላለከል
ዘመቻ ረገድ ላይም ተሳትፈዋል፤
የማንዴላ
የጋብቻ ሁኔታ
ማንዴላ
እ.ኤ. አ በ19 44-1957 ኤቪሊን ንቶኮ ማዚ ከተባለች የመጀመሪያ
ሚስቱ አራት ልጆች የወለደ ሲሆን
በ1958 እ.ኤአ የተፋቱ ሲሆን፤ በዚሁ ዓመት ዊኒ
ማዲኬዚላን በማግባት ሁለት ሴት ልጆች ወልደው፤ ለሁለተኛ ጊዜ ከእርሷ
ጋር ፍቺ ፈጽመው እ.ኤ.አ በ1998 ከቀድሞ የሞዛምቢኩ መሪ ባለቤት ከነበሩት ግራሳ ማቼል
ጋር ለሦስተኛ ጊዜ
ጋብቻ ፈጽመዋል፡፡
የማንዴላ አሟሟት
ኒልሰን ማንዴላ እ.ኤ.አ በ2001 የፐሮስቴት ካንሰር በሽታ ተጠቅተው የተከሙ ሲሆን፤ ለመጨረሻ ጊዜ ለህዝብ
የታዩት በ2010 በደቡብ አፍሪካ በተደረገው የዓለም የእግር
ካስ የዋንጫ ውድድር ላይ ሲሆን ከዚያ
ወዲያ ጊዚያቸውን የሚያሳልፉት የልጅነት መኖሪያቸው በነበረው የኩኑ መንደር ህብረተሰብ
ጋር ነበር፡፡ ማንዴላ በ2011
ላይ በሰንባ
ኢንፌክሽን ታምመው ሲሰቃዩ ቆይተው የተለያየ ህክምና ሲሰጣቸው ቆይተው ከዚህ ዓለም
በ95 ዓመታቸው ዴሴምበር 5,2013 በሞት ተለይተዋል፡፡
እ.ኤአ
በ2009 የኒልሰን ማንዴላ የልደት ቀን የሆነው ጁላይ 18, የማንዴላ ቀን በማለት በአለም ደረጃ እንዲከበር በማድረግ ሠላምን ለማበራታትና
የደቡብ አፍሪካዊው መሪን ሌጋሲ ለማከበር ታውጃል፡፡
የማንዴላ አስተምሮት
ማንዴላ
ለመላው የጥቁር ህዝብና
ለዓለም ትግስትን፣ለዓላማ ታማኝነትን፣ ውጣውረድን፣ ለህዝብ ጥቅም ህይወትን አሳልፎ መስጠትን፣ የዓላማ ጽናትን ፣ መልካምነትን እንዲሁም ሥልጣን
ሲይዙ ተቃናቃኞቻቸውን ድምጥማጥ የሚያጠፉ መሪዎች
በበዙባት የአፍሪካ ምድር እርቅ ያወረደ
የተበደለበበትን ጊዜ ወደ ኃላ የአለየ፣
በህዝቡ ላይ ይቅርታ መንፈስ እንዲሰፍን የደቡብ አፍሪካ
የእውነትና የእርቅ ኮሚሽን የተሰኘ ፍርድ ቤት መሰል አግባቢ
ተቋም ከእነ ዲዘሞንቱቱ ጋር
በማቋቋም ተቀናቃኞቹና የማድቀቂያ የሥልጣን መንበር
በቁጥጥሩ ስር ሆኖ ሳለ ብሔራዊ መግባባትና የይቅርታ በመላ
አገሪቱ እንዲሰፍን ያደረገ ብልህ
መሪ ነው፡፡
የኒልሰን ማንዴላ መታሰነቢያ ማዕከል
ድረገጽ እነደህ የሚል
ጹህፍ አስፍራል፡-
“ ሚስተር
ማንዴላ የ67 ዓመት ዕድሜ ዘመኑን ለሰው
ልጅ መብት መከበር
በመታገል አሳልፋል ! አሁን እኛ የምንጠይቀው እውን ቢያንስ
ለ67 ደቂቃ ም ያህላችን ነን ለሰብአዊ ተግባር
ወይም የአካባቢያችን ህብረተሰብ ለማገልገል የምናውልው?! ” ብሎ ይጠይቃል፡፡
እውነት
ነው ማናችን ለህዝብ ጥቀም
ብለን ምንም በግላችን
ባላጠፋነው ጥፋት የቀለም ልዩነት፣ የዘር ቆጠራ
ይቅር፣ በእኩል ዓይን እንታይ ስላልን
27 ዓመት ተፈርዶብን በትግስት የያዝነውን አቋም ይዘን
በጽናት እንቆያለን?! ከአሳሪዎቻችን
ጋር አንደራደርም በጋሮ በኩል? ወይም
የህዝብ መሪነን እያልን
በአፍ ቀላጤነት ላይ ላዩን እያመስን የእስር ጉዳይ ፊት
ለፊችን ሲደቀን የምንመራውን ትተን የጨበጥነውን በትነን
በአሳሪዎቻችን ጉያ ሥር አንወሸቅም?! ልጄን ሚስቴን
የወጣትነት ያማደጊያ የሠርቶ መብያ ጊዜዬን ብለን
ከዓላማችን በተቃራኒ የማንቀመጥ ወይ ደግሞ
እጃችንን አጣምረን በደልን አልሰማውም አላየሁም ብለን የምንመለከተስ የለንም?! በጊዚያዊ ጥቅምስ ዓላማችንን አንቀይርም? ሥልጣን በእጃችን
ገብቶስ በመብራት እየፈለግን ጠላቶቻችን
ናቸው የምንለውን አናሳድድም?! ማንዴላ
ግን ይህንን አላደረገም!! እሱ ነው
በትግስትና በፍቅር ያሸነፈ
የጠላቶቹም ጭምር የሁሉም መሪ!!
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ