ረቡዕ 19 ፌብሩዋሪ 2014

መንበር ናፋቂ ከያኒዎች! ክፍል -፪



መንበር ናፋቂ ከያኒዎች!

   ክፍል -፪

ባለፈ ጊዜ በክፍል ፩ ጹህፌ ስለ መንበር ናፋቂ  ሙዚቀኞ የሚዚቃ ሥራና ሰትራቴጂያቸውን  በማንሳት መንበርና መድረክ  እንዴት  እንደሚያገኙ በወፍ በረር ለማስቃኘት ሞክሬ ነበር ፡፡ዛሬ የመንበር ፈላጊ ተዋንይን አካሄድን እንይ እስቲ፡፡
   ተዋናዮቻችን እንደአሰላለፋቸው  መደብ  አውጥተን በአራት ተርታ ብናሰልፋቸው  ስዕል ለመስጠት የሚረዳ  ይመስለኛል፡፡

1ኛ) ትኩረታቸውን ጥበቡ ላይ ብቻ በማድረግ ህብረተሰቡን ያስከፋል ከሚሉት ተግባር በመቆጠብ የጥበብ ሥራ ለመስራት ብቻ የሚፈልጉ የተከበሩ ተዋናዮች
2ኛ) በተገኘው  አጋጣሚ ገንዘብ የማግኘት፣ የመታየት  አጋጣሚ  ወይም ላቅ ብለው ለመታየት መንበር  የሚያገኙበትን  ሁኔታ የሚቆፍሩ(የእነዚህ አካሄድ ቀጥታ ወደ መንግስት ጠጋ ጠጋ በማለት ሳይጠራቸው  አቤት ሳይልኳቸው ወዴት በማለት በተገኘው  የመንግስት ንቅናቄ፣ የመንግስት  መድረኮች  ላይ ተጋግጠው  ፊጢጥ የሚሉና  የሚረባ የማይረባ የከተፋ ሥራ በመስራት ገንዘብ የሚገኙበትን  የሚያነጣሩ ናቸው፡፡)
3ኛ) በአብዛኛ በቲያትር ቤቶች  ውሥጥ  ተቀጥረው የሚሰሩ በድርጅት አባለትንት በይፋ የሚታወቁ ምነዓልባት የድርት አባል ለመሆን ፍላጎት የሌላቸው ላይ የአለቃነት መንፈስ የሚያሳዩና ስንጥር ከምታክል ስልጣን እስከ የአርቲስቱን የህይወት አቅጣጭ የመቀየር አቅም ያለው ስልጣን ያላቸው እና የድርጅት አባልነታቸውንና አሰተታቸውን እንደ ብቃት (efficiency) በመጠቀም የከፍተኛ ትምህርት አጋጣሚን ጨምድደው የሚዙ ወይም ተጨማሪ ስልጣንየሚሹ ናቸው፡፡)
4ኛ) እነዚህ ደግሞ የሚተወን ነገር ወይም ገንዘብ ይገኝ እንጂ ህብረተሰቡን ያስከፋል ወይም የወደፊት ህይወቴ ላይ ጥላሸት ይቀባል የማለት ግድ የሌላቸው ናቸው፡፡

       በነገራችን ላይ  አይናቸውን  በጨው አሽተው  የተሰጣቸውን የሙያ ከበሬታ በመጠቀም የካድሬ ስራ በመሥራት ከህዝቡ ልብ ውስጥ የወጡ  እና ከህዝቡ ልብ ለመውጣት አፋፍ ላይ ያሉት ካልሆነ በስተቀር  በአብዛኛው ተዋንያን  ከመንግስት ጋር የመጣበቅና የፕሮፓጋንዳ አይነት ሥራ መስራት ወይም መንበር የመናፈቅ ፍላጎት አላቸው ለማለት አይቻልም ወይም በግርድፉ ተቀላቅለዋለ  ቢባል እንኳን የነበረው ወይም ያለው ሁኔታ አስገድዷቸው ቢቸግር የተጣመሩ ናቸው  ማለት ይቻላል፡፡ እስቲ መጠሪያ እየሰጠናቸው ባህሪቸውን እንይ፡-

የቲያትር ቤት ፊት አውራሪዎች 
    እነዚህ  ተዋንያን  ገሚሱ ወንበር ያገኙ  ገሚሱ  ወንበር  እንዳያገኙ የተለያየ የቲያትር ቤቱ መስፈርት( የትምህርት  ደረጃ ሊሆን ይችላል ) እንቅፋት የሆነባቸው ሲሆኑ ይሁንና በተለያየየኢህዴግ የድርጅት  መዋቅር ውስጥ ያሉ በመሆናቸው  ወንበር  ከያዙት  ያላነሰ  አቅም ያላቸው  ሆነው የተለያየ ጥቅም የሚያገኙ ናቸው፡፡  ስብሰባ፣ የፕሮፓጋንዳ ዝግጅቶች፣  የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትሩ  ቀብር ማሰፈጸም፣ የንቅናቄ ስራ፣የብሄር ብሄረሰብ ዝግጅት ላይ አለን አለን የሚሉ፣ ስም የሚመዘግቡ፣ አመራር የሚሰጡ፣ ፕሮግራም የሚያወጡ፣ ጉድጋድ ሳይቆፈር ቀድመው ችግኝ ተካይ ነንኝ የሚሉ፣በአውቶብስ ውስጥ እየተጋፉ ከአወውቶብሱ ውጪ የጠቅላይ ሚንስትሩን ፎቶ ያለበት ያደፋ ከነቴሪያ የለበሰ የእምሮ በሽተኛ የአውቶብስ ግፊያቸውን ትተው በሞባየላቸው ፎቶ ለማንሳት የሚንደፋደፉ፣ ሰው የሚያስተኩሱ፣ ባልተገራ  አንደበታቸው ወይም የፊደል እጥረት ባለው አስተሳሰባቸው  በቴለቪዥን ወይም በሬድዮ እነርሱን ፈትቶ የሚገጥማቸውን ህዝብ  እንደዚህ ነው ማድረግ ያለብህ፣ እኛን ተመልከት፣ አትሳሳት ወዘተ.. እያሉ ከኛ ወዲያ ንቃት ሲሉ  ይታያሉ፡፡  
       እነዚህ  አጋፋሪዎች አጋፋሪነታቸው የሚያተርፈው ጥቅሞች አሉት፡፡ የሰው ቲያትር እነዲያልፍ ወይም እንዲወድቅ ጫና የመፍጠር  አቅም፣ መድረክ የመስጠት ወይም የማግኘት  አቅም፣ የተደራደሩባቸው ፊልሞች ለዕይታ እንዲበቃ የመወሰን ወይም የማስወሰን አቅም፣ የተለያየ  አበል ያላቸው ስልጠናዎች  ማግኘት ወይም ማስገኘት፣ በፈለጉት ሰዓት የመንቀሳቀስ ወይም የማንቀሳቀስ አቅም የተወሰኑት ናቸው፡፡
     አንድ  ጊዜ አንድ ቲያትር ቤት አንድ  ተዋናይን ለሥራ  ጉዳይ  ላናግር ቢሮው ቀጠረኝና  እኔና አንድ ባልደረባዬ ወደ ተቀጠርንበት ቲያትር ቤተ ሄድን ግለሰቡ  ቢሮው ጋበዘንና የመጣንበትን ጉዳይን ስናወራው በየተወሰነ የንግግራችን አንጓ ላይ 2ኛ  ዲግሪየን  ቲያትር ለልማት(theater for development) እየሰራሁ ስለሆነ የሚለው ንግግር  አሰለቸንና እኔና ባልደረባዬ አይን ለዓይን ስንተያይ ቆይተን ከቢሮው ስንወጣ  ጉዳያችንን ትተን ፤ አይ ሁሌተኛ ድግሪ! ብለን እንኳን በድርጅት ጉያ ስር ተሸጉጦ በወጉ ሳይማሩ ለሚወሰድ ድግሪ ቀርቶ በአግባቡ በአለም አቀፍ ደረጃ የተቀመጠለትን መስፈርትና የትምህርት ጊዜ  በተገቢው ሁኔታ ያለምንም ጥገኝነት ተከታትለው  ሁለት ሶስት ድግሪ መያዝ በየሰዓቱ እንደ ዳዊት  የሚደገም  ጉዳይ አይደለም አሁን አሁን! አልን፡፡ የሚገርመው ደግሞ! አለኝ ባልደረባዬ፤ ይህ ሰው እኮ ተገቢውን  የዩኒቨርስቲ መግቢያ ነጥብ ሳያማሉ በማበረታቻ በዘመቻ  ገብተው በዲፕሎማ ራሳቸውን አማሙቀው  ወደ ድግሪ በመከራ  ከተዘዋወሩት ተዋናዮቻችን መሃል ነው አለኝ፡፡ እኔም ያም ሆነ ይህ ወረቀት ይዞ መገኘት  ነው አልኩት ወረቀት በሚናፈቅበት የትያትር ቤት ምህዳር ውስጥ ሆኖ፡፡  
    ስለ አንድ የቲያትር ቤት አጋፋሪ ገጠመኝ አስነብቢያችሁ ከቲያትር ቤት ልውጣ፡፡ አንድ አንጋፋና በየፊልሞች ላይ የማናጣው ተዋናይ  አጋፋሪ ከመሆኑ በፊትና  በኃላ  እራሱን  በመስታወት ያየበትን ሁኔታ ላጫውታችሁ፡፡  አርቲስቱ  ወደ መኖሪያ ቤቱ ሲገባ በመኖሪያ ቤቱ አቅራቢያ ካለ መጠጥ ቤት አንድ ሁለት  እየለ የአካባቢው ወጣቶች እንደ  መልካም መሪያቸው እያዩ  ጋሽ  እከሌ ዛሬ እኔ ነኝ የምጋብዝ ፣ዛሬ እኔነኝ የምሸኝ እያሉ ዘና ብሎ በአጃቢ እቤተ የሚገባ ሰው ነበር ፤ ታዲያ ይህ አንጋፋ አርቲስት የቤት ችግር አለበት ነበርና (ሁኔታው ኃላ ሲጣራ  ነው) የቤት  ጉዳዩን ለመፍታት  በድርጅት ታቅፎ ውሥጥ ለውስጥ በሰውር ንቅናቄ ሲያደርግ ቆይቶ  የድረጅት ቁርጠኝነት የሚለካበትን የህዝብ ተቀባይነትን ለስልጣን ማቆያ መጠቀም በሚለው ስልት ለምርጫ እንቅስቃስው እጩ ተወዳዳሪ ሆኖ ፎቶው በአካባቢው ይለጠፍና  ምርው ካለፈ በኃለ ይህ ለመሬት የከበደ ተዋናይ ግርማ ሞገስ ያለውን ጥቁርና ነጭ ጸጉሩን አሳምሮ  አገር ሰላም ብሎ ያች ማታ ማታ ጎራ የሚልባት መጠጥ ቤት ገብቶ መጠጡን መጠጣት ሲጀምር ከገባበት ጊዜ ጀምሮ ሁኔታውን በንቀት  ሲከታተሉ  ከነበሩት ወቶች አንዱ ከሚጠጣበት በደንምብ ፍላት ድንገት ብድግ ብሎ  የተዋናዩን እናት አሰጠያፊ ስድብ በመሳደብ ምን ታየኛለህ ብሎ ሲያፈጥ አርቲስቱ እርሱን የተባለ መሆኑን  በመጠራጠር ፊቱን ወደ ኃላ አዙሮ አጣርቶ በመመ ለስ እኔን ነው ያናገርከኝ ብሎ በማሳዘን ሲጠይቅ ወጣቱ ጠረጴዛው ያለውን የመጠጥ ጠርሙስ በእጁ አፈፍ አድርጎ ሊወረውር ሲል አጠገቡ ያሉት ባልነጀሮች ገላገሉት፡፡ የመጠጥ ቤቱ ባለቤቶች ምንድን ነው  ነገሩ በምን ጊዜ ተነጋግራችሁ ነው ብለው  ለማጣራት ሲሞክሩ የወጣቱ ባልንጀሮች አርቲስት ነው  ብለን ስናከብረው ለካ እስከ ዛሬ ሲሰልለን ነበር ብለው፤ ሁኔታው ግራ የተጋባው አርቲስቱ ነገር ለማብረድ ወጥቶ ሲሄድ ሰላም  እንደተፈጠረ  ሁኔታውን የተከታተለ አንድ ሰው ያጫወተኝ ለፊት አውራሪ ተዋናዮች ክብር የሚሰጣችሁ ህዝብን የሚያከብር ስራ ስትሰሩ እንጂ መንበር ስትናፍቁ አይደለም  የሚል መልዕክት ያስተላለፈ አጋጣሚ ነው፡፡ 

ባለድርጅትፊታውራሪ ተዋናዮች
   እነዚህ  በድህና ጊዜ በህዝብ ተወዳጅነታቸው በመጠቀም ቶሎ ቶሎ ንብረት እና ድርጅት አፍተው ከንብረታችን ወዲያ ያለ ህዝብ ለምኔ! በማለት የመንግስት የተለያየ የቅስቀሳ መድረኮች ላይ ከባለስልጣኖች ፊት በመቆም ለአብዮቱ ዘብ የቆሙ መሆናቸውንና ታማኝነታቸውን ያሰስመሰከሩ፣ የተለያየ ፕሮጀክት እየነደፉ የቁርጥ ቀን ልጅ  መሆናቸው የሚያሳይ የምስክር ወረቀት ከፕሮጀክታቸው ጋር ኣባሪ ደብዳቤ በማድረግ ገንዘብ የሚሰበስቡ ከህዝብ ልብ ውስጥ መውጣታቸውን ልቦናቸው ስላወቀ በተለያየአጋጣሚ  በቴሌቪዝን መስኮት ብቅ በማለት ለተመልካች አሰልቺ ሥራ በመስራት አለው ምን ታመጣላችሁ!በሚል ስሜት ብር የሚሰበስቡ የራሳቸውን ፊልም ከመንግስት ፖሊሲ ጋር በማገናኘት ማንነታቸውን ጠንቅቆ የሚያውቃቸው ህዝብ ላይ እንደ አገር ወዳድና ገለልተኛ ኢትየጵያዊ የፈጠራ ታሪክ እየሰሩ ወይም በአምሳዮቻቸው  ሙገሳ እያሰሩ ይህንን በጥንቃቄ የሚስተውላቸውን ህዝብ ላይ ከመድረክ ባሻር አርቴፊሻል ትወናበመተወን ወደ ሀብት ጉዞ የሚጋልቡ ናቸው፡፡ ባለ ድርጅት ፊታውራሪዎች ፊልም ከሰሩ ለምረቃታቸው የሚያገለግል የመሰብበሰቢያ  አዳራሽ መደበኛ ፕሮግራም የማሰረዝ  ደንብና መመሪያ ጥሶ የእነርሱ ዝግጅት እንዲካሄድ የማድረግ አቅም አላቸው፣ በአገሪቱ በየትኛውም አቅጣጫ  የሚካሄዱ ቴሌቶኖች ላይ አስታዋዋቂና መድረክ መሪዎች ናቸው፡፡ ከሚሰበሰበው  ገንዘብ  በፐርሰንት እነርሱና ሙሰኛ  የቴሎቶን ኃላፊዎች ጋር በሚያደርጉት ከመጋረጃ  ጀርባ  ድርድር ለክልሉ ልማት ተጨናቂ በመምሰል የብሄሩን አልባሳትና ቁሳቁስበመጠቀም ከራሱ ከለፈፉለት ህዝብ በሚልየን በገዛ እጃቸው የሚወስዱ ናቸው፡፡     
     አንድ የማስታወቂያ ባለሞያ የሆነ ሰው አንድ ጊዜ ወደ በደ/ብ/ብ/ህ/ክልላላዊ መንግስት አንድ ዞን ላይ የወጣት ማዕከል ለመገንባት ከዞኑ ባላስሥልጣናት ጋር  ከሚገኘው ገቢ በእርሱ  ሥም ለእነርሱም ጭምር ኮሚሽን እንዲይዝላቸው መደበኛ ባለሆነ(unofficial) መልኩ በመደራደር መደበኛ የሆነ ውል  ተዋውለው ሥራ ይጀመራሉ፡፡  ታዲያ ሥራው ከአዲስ አበባ ወደዚሁ ዞን በግል መኪና በመመላለስ ለማስታወቂያ ሥራ የዞኑን መልካምድርና አይን ገብ የሆኑ ቦታዎችን በመቅረጽ ተግባራዊ እንቅስቃሴ አድርገው ለሥራ ማካሄጃ ከዞኑ የሚጠበቀውን  ብር ልቀቁልን በሚል በዚህ ጉዳይ ላይ ቀጠሮ እየያዙ በመነጋገር ላይ እያሉ በዞኑ ላይ ልዩ ግምገማ ተያዘ ተባለና ግምገማው እስኪጠናቀቅ ለተወሰነ ጊዜ የተግባሩ እንቅስቃሴው ተቋርጦ ግምገማው ሲጠናቀቅ ይህ ደንበኛዬ ከግምገማው በኃላ የሥልጣን  ማሸጋሸግ ተፈጥሮ ነበርና ቀደም ሲል በድርድሩ ውስጥ  የነበረና በግምገማው የተሻለ መንበር ያገኘውን ሰው ጉዳያችን ምን ደረሰ ብሎ ሲጠይቀው የተለያየ ምክንያት  ሲያቀርብና ሳምንት፣ አሥራ አምስት ቀን ሲቀጥራቸው ቆይቶ  እነዚህ የቁርጥ ቀን  መሆናቸውን የሚያሳይ  አባሪ ደብዳቤ የያዙ ባለ ድርጅት ፊታውራሪዎች ከሆኑት መካከል አንደኛው የተሻለ መደራደሪያ አቅርቦ የነጠቃቸው  መሆኑን  ነግሮኝ ከዞኑ አስተዳደር ጋር የተዋዋለበትን ውል ይዞ የህግ ምክር የጠየቀኝን ሰው አስታውሳለው፡፡

ታዳጊ (the up coming)ፉት አውራረሪ ተዋናዮች
 እነዚህ  ተዋናዮች ወጣቶች ወይም የወጣትነት  ዕድሜ ላይ ያሉ ሲሆኑ፤ ቀደም  ሲል የድርጅት ባለቤት ፊታውራሪ የሚባሉ ተዋናዮችን አርአያ በማድረግ የሚንቀሳቀሱ ሲሆኑ ከቀደሞቹ  ለየት የሚያደርጋቸው በገንዘብ  አቅም ያልጎለበቱ መሆናቸው፣ ወጣት  መሆናቸው፣ ምንአልባትም ስም ያለው ወይም የገንዘብ አቅም ያለው ድርጅት የሌላቸው በመሆናቸው፣ አካሄዳቸው  እነደቀድሞዎቹ ፍጥነቱን ጠብቆ በማለሳለስ ፊት አውራሪነታቸውን የተቆናጠጡ ሳይሆን ፤ፈጣጣ የሆነ ችኩልነት የሚያሳዩ(ከጠቅላይ ሚንስትሩ  ወይም ከመከላከያ ሚኒስትሩ አጠገብ አይናቸውን በማፍጠጥ ፊጢጥ ብለው ሊያነብንቡ የሚችሉ ወይም  የጥበብ ሰው ነኝ አድናቂዎቼ ከፖለቲካ መሪዎቹ ጋር ያመሳስሉኛል(Associate) ያደርጉኛል ብለው ጥንቃቄ የማያደርጉ ወይም እንደዚህ የማይገባቸው ናቸው፡፡ስልጠናና ከፍተኛ ትምህርት የሚያገኙበትን ቀዳዳ የሚፈልጉ ወይም የሚጠቀሙ፣ ልታይ ልታይ የሚሉ ለንግግራቸው ዜማና ቃና የሚፈጥሩ እራሳቸውን እንደ ጋዜጠኛ  እንደ  መድረክ መሪ የሚያደርጉ መንበር ናፋቂነታቸውን በቀላሉ ስማቸው ሊታወቅ የማችሉ የመንግስት ኃላፊዎችን ነባር ታጋዮችን  እስከ አያታቸው ስም በመጥራት  ነጥብ ማስመዝገባቸውን  ማረጋገጥ የሚፈልጉ፤ በታላላቅ እና እኩያ የሞያ  አጋሮቻቸው  ፊት ላይ ያለምንም ይሉኝታ ዘለል ዘለል የሚሉና የሚዘባነኑ! ከእነእርሱ ወዲያ ሰው ያለ የማይመሰላቸው ፣የተለየ መብት(Immunity) ያለቸው የሚያስመስሉ፣የተለያዩ ዝግጅቶ(ፊልም ምረቃ፣ቲያትር ምረቃ፣ መጽሀፍ ምረቃ ወዘተ ላይ አጋፋሪ የሚሆኑ የመንግስትየሚመለከታቸው አካላቶች እንደ ጋደኞቻቸው ሊጠሩ እንደሚችሉ ስልካቸውን እያሳዩ የሚያሰወሩ) አዋቂነኝ አይነት ስታየል የሚያሳዩ፣ ሬድዮ ፕሮግራሞች ሊሰሩ የማይመለሱና  ራሳቸውን እንደ አስተማሪ የሚጠቀሙ ወይም  በሚሰሩት ዝግጅት ላይ ቀጥተኛም ሆነ ቀጥተኛ ባልሆነ መልኩ ሊጠቅማቸው የሚችለውን ኃላፊ የሚጋብዙ፣ቴሌቪዥን ወይም ሬድዮ ፕሮግራሞች አለያም የመድረክ ዝግጅቶች ከሞያ ባለደረቦቻቸው አፍ ላይ ነጥቀው ያለምንም ይሉኝታ የሚናኙበት፣እነርሱ  ከተሰማሩበት ሞያ ጋርና ከመንግስት ጋር የማያግባባ ጉዳይ ወይም ሊያስከፋ የሚችል የመንግስት ህፀፅ የማይነኩ ናቸው፡፡
                                     
ታዳጊ ፊታውራሪ ተዋናዮች  አጋጣሚ የሚሹ(opportunity seeker) ናቸው፡፡  አሰተሳሰባቸው ህዝብ እንዲያደንቀን  ወይም እንዲያከበረኝ ልሥራ ሳይሆን የገዢው መንግስት ቱባ ባለሥላጣኖች እንዲደንቃቸው ወይም ታዛዥነታቸውንና ቁርጠኝነታቸውን  እንዲመዘግቡላቸው ነው የሚሹት፡፡  ለዚህ  ዓላማቸው የሚረዳቸው ህዝብና መንግስት የማይገባባቸው አጀንዳዎች ላይ መንግስት ዝግጅት ቢያዘጋጅ ዘለው መድረክ ላይ ፊጥ የሚሉ ፊታውራሪዎች  እነርሱ ሆነው ፤ የዚህ ሥራ ባለቤት የሆኑት ካድሬዎቹ ሳይቀር ሥራቸውን ከእነሱ  እጥፍ በሆነ መልኩ ሲሰሩላቸው አይተው አፋቸውን ከፍተው እንዲያያቸው ያደርጋቸዋል፡፡  

 ስለ ህዝብና ስለ ስም መጠልሸት  ስለ ህሊናዊነት ግድ የሌላቸው እውቅናና  ገንዘብ  ብቻ  ወደፊት የሚሉ ተዋናዮች

 እነዚህ  ተዋናዮች ዋነኛ  ዓላማቸው ትወናቸውን  መስራት ፣ገንዘብ  ማግኘት፣ በህዝቡ ተደንቀው መታየት(ማነታቸውን በማያውቁ ሰዎች ወይም  በእነርሱ ቢጤ አድናቂዎቻቸው(በተለይ ሴቶች)  ልብ ስር  መንገስ)፣  አንድ ቦታ  ተመሽገው ስለ ሰው እያወሩ ሲጋራቸውን ማጨስ ጫታቸውን  ማመንዠግ ጨብሲያቸውን አቅም ያላቸው አልኮል መጠጥ የሚጋቱ አቅም የሌላቸው ደግሞ ድራፍታቸውን ወይም ሃረቄያቸውን እየጨለጡ በስተመጨረሻ ሲመሻሽ ወይ ሲነጋባቸው ክብር የሰጣቸውን ህዝብ ክብር የሚነሱ፣  ስለ ስማቸው መጠልሸት፣ስለ ለህዝብ ምንይለኛልና የሚሰሩት ሥራ ከሚያደንቃቸው ህዝብ ጋር የሚያጋጭ ነው አይደለም፤ ግድ የማይሰጣቸው፣ በሚያዩት  የህዝብን የመንግስት ቁርቁስ  ሙድ የሚይዙ ፣ ማህበራዊ ኃላፊነት የማሰማቸው ፣ ኃላፊነት የሚሰማቸው ከያኒዎችን የሚተቹ፣ መሻሻል የማይታይባቸው  ሁል ጊዜ የሰው ተቀጣሪ የሚሆኑ ፣ ስልጠና  ከፍተኛ ትምህርት ታሪካዊ ጠላታቸው የሆነ፣ መኪና መያዝ የምተዓመቱ  ግባቸው የሆኑ ናቸው፡፡  በእርግጥ  እነዚህ ተዋናዮች መንበር የመናፈቅ  ዕቅድ በማስታወሻቸው ላይ  ያልሰፈረ ቢሆንም  ለመንበር ናፋቂዎች ምርኩዝ እየሆኑ የመንበር ናፋቂዎችን ቁጥር ይጨምራሉ፡፡
    
የህዝብ ልብ መንበራቸው የሆነና ለህሊናቸው ና ለጥበብ የሚሠሩ የተከበሩ ተዋናዮች

እነዚህ ተዋናዮች የሚሰሩትን ሥራ የሚያውቁ ፣ከህዝብ ጋር የሚያጋጭ ሥራ የትየለሌ ገንዘብ የሚያስገኝ ቢሆን እንን በጭራሽ አያፈልጉም፣የጥበብበ ሥራ ሊሰሩበመጀመሪያ  ቅድመ ሁኔታቸው ከሞያ አፍቃሪያቸው ጋር የማያጋጫቸው መሆኑንና ደረጃውን የጠበቀ መሆኑን ነው፣ እምብዛም ባለንብረትና ከፍተኛ የሆነ የገነዘብ  አቅም የላቸውም፣ ሥማቸው በህዘቡ ውስጥ ከፍተኛ ቦታ ያለውና አብረቅራቂ ነው፣የሥልጣን መንበር አይፈልጉም ወይም  ለእነርሱ ምንማቸው ነው፣  አጋጣሚ ካገኙ የህዝቡን ስሜት ና ብሶት የሚያሳዩ ወይም የሚገልጹ  ሥራ መስራት ያረካቸዋል፣ ለሞያ እኩዩቻቸው ከፍተኛ  ከበሬታ አላቸው፣ መንበር ናፋቂዎች ሆኑ ከታፊ ተዋናዮች ከፍተኛ አድናቆት ይቸራቸዋል፣ የመንግስት ባለሥላጣናት በልባቸው ከበሬታ ይሰጣቸዋል፣ አብዛኞቹ አጉል ሱስ የለባቸውም ፣ ነውርና ሞራል ይገባቸዋል፣ ሃይማኖታቸውን ያከብራሉ ጠንከር ያሉት ደግሞ ፃሚ ፀላዮች ናቸው፣ ማህበራዊ ኃላፊነት ይሰማቸዋል፣ ደስተኛ ህይወት ነው የሚኖሩት፣ ለቤተሰቦቻቸው  ከበሬታ አላቸው፣ትዳራቸው ወይም ለፍቅር ጋደኞቻቸው ታማኝ ናቸው ፣ ሰውን በክፋት  ማንሳት አይወዱም፣ ሀብት ለማግኘት ብለው ሰይጣናዊ ቦታዎች አይሄዱም፣ የሰላም እንቅልፍ ይተኛሉ ፡ወዘተ…..
    አንባቢያን እንግዲህ ለዛሬ የተዋናዮቻችንን  እንቅስቃሴ በምድብ፤ በምድብ  አስቀምጠን  እንዲሁም ባህሪያቸውን፣ ተግባራቸውንና ዓላማቸውን  በጥቂቱ ለማሣየት ሞክሬያለው፡፡  ስለ ተዋናዮቻችን አካሄድ ብዙም ላልተገለጸላቸው  አድናቂዎች ምስል የሚከስት በተጨማሪ ደግሞ እራሳቸው የአገራችን ተዋንያንን ምድባቸው እንዲለዩ ያደርጋል ብዬ እገምታለው፡፡  በሚቀጥለው ጊዜ አንድ ተጨማሪ የመንበር  ናፈቂ ከያኒዎች ሞያን እንቅስቃሴ በማስነበብ  ጹህፌን አጠናቅቃለው፡፡ መልካም ሁኑ፡፡  

ሐሙስ 13 ፌብሩዋሪ 2014

ማንዴላ!!!



  ማንዴላ!!!
ጠላቶቹንም  ጭምር  በትዕግስትና በፍቅር ያሸነፈ የሁሉም ሰው መሪ!
          በዝራው አሻግሬ
          Zirawashagre@yahoo.com
        በዚህ ሳምንት ውስጥ  ዓለም ዓቀፍ ሚዲያው ላይ ወደር የሌለው ሽፋን በማግኘት  በደቂቃና  በሰከንድ ውስጥ ዜና ፣ዘገባ፣መጣጥፍ እና  ዶክመንተሪ  ፊልም  ዘገባ ሲካሄድባቸው  የነበሩት  አሁንም  እየተዘገበላቸው ያለው  የደቡብ  አፍሪካው የነፃነት  ታጋይ የኔልሰን  ማንዴላ  በ95  ዓመታቸው  ባለፈው ሳምንት ህዳር  27,2006 ዓ.ም  ሐሙስ  ዕለት ከዚህ ዓለም  በሞት  መለያታቸው ነው፡፡   ማንዴላ  ለአፍሪካ እንዲሁም  ለዓለም   መንግስታት  መሪዎች አርአያ ሊሆኑ የሚችሉ መሆናቸውን  የዓለም  ህዝብ  እንዲሁም የተለያዩ  መሪዎች  ያለምንም  ቀስቃሽ ስሜታቸው እየናጣቸው ማንዴላ የተለየ መሪ  መሆናቸው  አረጋግጠዋል፡፡ ማንዴላ ማናቸው? አስተዳደጋቸውስ እንዴት ነበር? ህይወታቸው ምን ይመስላል?  በተወሰነ  እንመልከት፡፡ 
የማንዴላ ውልደትና  እድገት
   ሮሊሂላላ  ማንዴላ ሚቭዞ  በምትባል አንዲት ትንሽ መንደር ውስጥ ምባሺ ወንዝ  ዳርቻ ትራንስኪ ውስጥ እ.ኤ.አ ሐምሌ  18, 1918  በደቡብ  አፍሪካ ተወለደ ፡፡ ሮሊሂላላ በዞሳ  ቋንቋ  ቃል በቃል  ሲተረጎም የባህር ዛፍን ቅርንጫፍ ለመገንጠል  መታገል ማለት  ሲሆን በተለምዶ  አዋኪ ዉም ረባሽ በሚል  ይተረጎማል፡፡
የኒልሰን ማንዴላ  አባት የጎሳ መሪ እና የጎሳ መሪዎች መማክርት ሆነው  ለበርካታ  ዓመታት ያገለገሉ ሲሆን፤ሁለቱንም  ሥልጣናቸውን  በጊዜው ከነበሩ የቀኝ  ገዢዎች ጋር በፈጠሩት  እስጣ  ገባ  አጥተውታል፡፡  በዚህ  ጊዜ ማንዴላ  ብቸኛ  ልጅ ነበር፡፡ የአባቱ  ከስልጣን  መነሳት እናቱ ቤተሰቡን ከሚቬዞ በስተደቡብ  የምትገኝ ኩኑ የምትበል ትንሽ መንደር ይዛ ለመዘዋወር ምክንያት  ሆናት፡፡  
 በማንዴላ አባት  ጋደኛ  ሀሳብ  አመንጪነት ማንዴላ  ሜቶዲስት ቤተክርስቲያን  ተጠመቀ፡፡ ከቤተሰቡ የመጀመሪያው ትምህርት ቤት የገባ  ልጅም  ሆነ፡፡ በወቅቱ በተለምዶ  እንደሚደረገው እንዲሁም በደቡብ  አፍሪካ ላይ  የእንግሊዝ  የትምህርት ሥርዓት ተጽዕኖ  በማሳደሩ ምክንያት የማንዴላ  የመጀመሪያ  መጠሪያ ሥሙ ኔልሰን እንዲሆን የማንዴላ  መምህር ገለጹለት፡፡
ማንዴላ በ9 ዓመቱ  የአባቱ በሳንባ  በሽታ መሞት የህይወቱን አቅጣጫ በአስገራሚ  ሁነታ ቀይሮታል፡፡ ማንዴላ ጆንጊታባ  ዳሊን ዲዬቦ በተባሉ የጎሳ መሪና  አባቱ በህይወት  እያሉ የጎሳ  መሪ እንዲሆኑ  ሀሳብ ባቀሩቡላቸው ሰው እንደ ውለታ  መሥራት አይነት በጉዲፈቻ ልጅነት  ወሰዱት፡፡  ማንዴላ በትንሿ ኩኑ መንደር ያገኝ የነበረውን  እንክብካቤና ነጻነት ዳግም እንደማያገኝና  የሚወዳትን መንደር ተመልሶ ሊያያት እነደማይችል እያሰበ  በስጋት  ትቷት ተጓዘ፡፡  ማንዴላ የቴምቡላንድ   ጊዚያዊ ከተማ  ወደ ተባለችው የንሳን  ቤተሰብ አለቃ መኖሪያ ምኪኪዚዌኒ በሞተር ባይስክል  ተጓዝ፡፡   ማንዴላ ምንም  እንኳን የሚወዳትን  ኩኑ  መንደር  ያልረሳ ቢሀንም  አዲሷንና ግራ የምታጋባውን ምኪኪዚዌኒ ከተማ በቀላሉ  ተለማመዳት፡፡
ማንዴላ የጎሳ መሪው የበኩር ልጅ የሆነው ጀስትስ እና ኖማፉ ከተባለች ሴት ልጁ  ያላቸውን አይነት  ክብርና  ኃላፊነት  እኩል ተሰጠው፡፡ ማዴላ  ከቤተ መንግስቱ አጠገብ  በሚገኘው ባለ አንድ  ክፍል ትምህርት ቤት  ውስት  ገብቶ እንግሊዘኛ፣  ዞሳ፣ ታሪክና የህብረተሰብ ሳይንስ ትምህር  ተማረ፡፡ በዚህን ግዜ ነበር  ማንዴላ ስለ አፍሪካ ታሪክ የማወቅ  ፍላጎት  ያደረበት፡፡  
እ.እ.አ በ1939,  ማንዴላ የጥቁሮች ብቸኛ የከፍተኛ ትምህርት  ማዕከል በሆነው ፎርት ሐሬ ዩነቭረስቲ ኮሌጅ ገባ፡፡  በወቅቱ ፎርት ሐሬ ዩኒቨርስቲ እንደ  ኦክስፎርድና ሃርቫርድ ዩኒቭረዝቲ ጋር  በእኩል  የሚታይና ከሰሃራ በታች ያሉ  ሀገራት ምሁራንን  ያፈራ ነበር፡፡ በዩኒቨርስቲው የመጀመሪያው ዓመት ቆይታው  አስፈላጊውን ኮርሶች የወሰደ ቢሆንም  ህብረተሰቡን  ለማገልገል እንዲረዳው በወቅቱ ለጥቁሮች የሚሰራውን ምርጥ ሞያ ተብሎ የሚወሰደውን የህግ ተርጋሚኒትና  ጸሐፊ ሞያ በማጥናት የሮማን ደች  ህግ ትምህሩት ላይ  ትኩረትን   አደረገ፡፡
በዩኒቭርስቲ ቆይታው ሁለተኛ ዓመት ሲሞላው የተማሪዎች ተወካይ መማክረት ሆኖ  ተመረጠ፡፡ በተወሰነ ጊዜ ተማሪዎች  የሚቀርብላቸውን ምግብና  የተማሪዎች መማክርት ያለው  ሥልጣንን  አስመልክቶ እርካታ የላቸውም  ነበር፡፡  በምርጫው ወቅት አብዛኛው ተማሪ   ጥያቂአቸው  ካልተመለሰ ምርጫውን ጥሎ ለመውጣት በእጅ  ብልጫ ወሰኑ፡፡  በዚህን  ጊዜ ማንዴላ ከአብዛኛው ተማሪ ጎን  በመሆን  ከተማሪዎች  መማክርት  ተወካይነት  ራሱን  አገለለ፡፡
  የዩኒቭርስቲው ኃላፊ ዶ/ር ኬር  ማንዴላን  ከትምህርት ቤቱ በማባርር  የተማሪዎችን  መማክርት  ተወካይነቱን  የሚቀጥል  ከሆነ ትምህርቱን  ሊያስቀጥልው  እንደሚችል መደራደሪያ አቀረቡለት፡፡  ወደ ቤቱ ሲመልሰ  የጉዲፈቻ አባቱ  በቁጣ አስተናግደውት የሚለውን ሳያዳምጡ  አቋሙን  ቀይሮ ወደ ትምህርት  ቤቱ እንዲመለስ  አዘዙት፡፡
የማንዴላ  እስር  ጉዳይ
ማንዴላ  ወደ መኖሪያ ቤቱ  ከተመለሰ  ከጥቂት  ጊዚያት  በኃላ የጉዲፈቻ  አባቱ ሬጀንት ጆንጊታባ ሚስት እንዲያገባ አስፈላጊውን  ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን  ገለጹለት፡፡ የማንዴላ  የጉዲፈቻ አባት  ማንዴላ የተስተካከል  ህይወት እንዲመራ የራሳቸውን  ዝግጅት  ትክክል ነው የሚሉትን  ተግባር በማድረግ በሀገሩ ባህል  መሰረት አደረጉ፡፡ ይሀንን አስደንጋጭ  ዜና የሰማው ማንዴላ  አሁን ያለው  አማራጭ ትዕዛዙን  አክብሮ  መቀበል ብቻ  መሆኑንና ወጥመድ  ውስጥ  እንደገባ ሲሰማው   መኖሪያ ቤቱን  ለቆ ጠፋ፡፡  ጉዞውን  ወደ  ጆሃንስበርግ  አድርጎም  ዘበኝነትን እና ጸሐፊነትን ጨምሮ ኑሮውን የተለያየ ሥራ  በመስራት ይገፋ ጀመረ፡፡  በዊትዋትረሰታንድ ዩኒቭርስቲም ህግ ትምህርት  ለማጥናት  ተመዘገበ፡፡
ወዲያውኑ የዘአፍሪካ ናሽናል  ኮንገረስ (ኤአንሲ) ውስጥ እ.ኤ.አ በ1942 በመቀላቀል የፀረ አፓርታድ  ትግል እንቅስቃሴ በንቃት ይሳተፍ ጀመር፡፡  በኤ ኤን ሲ ውስጥ የአፍሪካ ናሽናል  ኮንግረስ የወጣቶች ህብረት የሚል ቁጥራቸው አናሳ የሆኑ የወጣት  አፍሪካውያን ስብስብ  ነበር፡፡  የዚህ  ህገብረት  ዓላማ ኤኤን ሲን  የሰፊው ህዝብ ሥር ነቀል እንቅስቃሴ ማድረግ፣ በሚሊየን የሚቆጠሩ  በአገዛዙ ምንም ድምጽ የሌላቸውን በገጠር የሚገኙ ጭሰኛ  ገበሬዎችንና የሠራተኛው ክፍልን የማጠናከርና የማብቃት  ሥራ  መስራት  ነበር፡፡ በተለይ  ህብረቱ የኤኤንሲ ያረጀ የህዝቡን ድጋፍ የማግኛ ዘዴው ውጤታማ አይደለም  የሚል  ነው፡፡ እ.ኤ.አ በ1942  ኤኤንሲ የወጣቶቹ  ረግጦ የመውጣት፣ የዓመጽ፣ የዓለመታዘዝና ያለመተባበር  የትግል  ዘዴን  የእኩል ዜግነት ፣የመሬት  ክፍፍል ፣የንግድ ማህበር መብቶች፣ ነጻና አስገዳጅ የሆነ የህፃናት የመማር መብት  የፖሊሲን  ግብ ይፋዊ  በሆነ መልኩ የራሱ የትግል ዓላማ  አድርጎ  ተቀበለው፡፡
ለ20 ዓመታት   እ.ኤ.አ የ1952ቱን የትግል ዘመቻና  እ.ኤ.አ የ1955 የህዝብ መማክርትን እንቅስቃሴን  ጨምሮ  ማንዴላ  በሠላማዊና ኃይል ያልተቀላቀለበት  ትግል በደቡብ  አፍሪካ  መንግስት  ላይ የሚደረገውን እንቅስቃሴ  መርቷል፡፡  ማንዴላና  ታምቦ የህግ አገልግሎት ድርጅት የሚባል ፎርት ሄር ዩኒቨርስቲ  ሲማር  በጉብዝናው ከሚያውቀው ኦሊቨር ታምቦ ጋር በመሆን በጋራ  ከፍተዋል፡፡ የህግ ድርጅቱ  በቅማናሽና በነጻ የህግ አገልግሎት ድጋፍ ላልተወከሉ ጥቁሮች ያደረግ  ነበር፡፡
እ.ኤ.አ በ1956 ማንዴላ እና  150 ሰዎች በፖለቲካዊ ምክክር በሚል ምክንያት  ክስ  ተመስርቶባቸው ታሰሩ፡፡ በዚህን  ጊዜ ኤኤንሲ  አፍሪካውያኖች(Africanist) አዲሱ የጥቁር ታጋዮች(black activist) ውልዶች ነን በሚሉና የኤኤንሲ የሠላማዊና የዝምታ  መንገድ ውጤት ዓልባ ሆኗል በሚሉ ሰዎች እንቅስቃሴ ነውጥ ውስጥ  ገብቶ ነበር፡፡  አፍሪካውያኖች ወዲያውኑ  ከኤኤንሲ በመነጠል ፓን አፍሪካዊያን ኮንግረስ የሚል  አቃቁመው ኤኤኒሲ ላይ  አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳደሩ ሲሆን  ኤኤን ሲ  አብዛኛው ታጣቂ  ደጋፊዎቹን  አጥቶበታል፡፡
በ1961  ሃይል ያልተቀላቀለበት ትግል ያስኬዳል  በማለት  ሲሟገት የነበረው  ማንዴላ  በስተመጨረሻ የትጥቅ  ትግል  ብቸኛው  አማራጭ ነው ወደ የሚለው  ድምዳሜ ደርሶ ነበር፡፡ በማስከተልም ዩምኮንቶ ዊ ሲዚዊ  ወይም ኤም ኬ  የተሰኘ አፓርታይድን ለመጣል የሚረዳ ሸማቂ ኃይል ከአቋቋሙት  መኃል  ሆነ፡፡ በ1961 ማንዴላ  የ3ት  ቀን  ብሄራዊ  የሥራ  ማቆም  አድማ አቀናብሮ በቀጣዩ ኣመት ዓመጽ በማስነሳት  በሚል  በ1963 ዓ.ም የ5 ዓመት የእስር  ውሳኔ ተወሰነበት፡፡
በድጋሚ ፍርድ ቤት ቀርቦ ማሴርና ፖለቲካዊ ጥቃቶች  በሚል ክስ እሱና  አሥር የኤኤኒሲ  መሪዎች የዕድሜ ልክ  እሥራት  ተፈረደባቸው፡፡
ኒልሰም  ማንዴላ ከ27 ዓመት የእሥር  ቆይታው 18 ቱን ዓመትን በሮቢን ደሴት ነው  ያሳለፈው፡፡  በእስር  ቆይታው የሳምባ ነቀርሳ በሽታ ይዞት የበረ ሲሆን  እንደማንኛውም  ጥቁር የፖለቲካ  እስረኛ በደካማ ህክምና  አገልግሎት  በእስር ቤቱ ሠራተኞች  ነበር የተሰጠው፡፡  ምንም  እንኳን  በህመም  ላይ  ቢሆንም  ማንዴላ  የህግ ትምህርቱን  ከሎንደን  ዩኒቨርስቲ በተልዕኮ አግኝታል፡፡
እ.ኤ.አ በ1981 የደቡብ  አፍሪካ የደህንነት ወኪል  በሆነው ጎርደን ዊንተር አማካኝነት በደቡብ  አፍሪካ መንግስት  ማንዴላን ከእስር  ቤት  እንዲያመልጥ  ሁኔታዎችን  በማመቻቸትና  ከእስር ቤት ሊያመልጥ  ሲልነው በማለት በጥይት ሊመቱት ሴራ  ተጎንጉኖለት በእንግሊዝ የደህንነት ኣማካኝነት  ከሽፋል፡፡ (ኢትዮጵያ ውስጥም በኮልፌ  ፈጥኖ ደራሽ የፖሊስ ማሰልጠኛ  ተቋም የግድያ  ሙከራ የተደረገበት  መሆኑ  በቅርብ  ጊዜ እተገለጸ ያለ  ዜና  ነው፡፡ )  ማንዴላ የጥቁሮች የነፃነት ምልከት  ተደርጎ በዓለም  ላይ መናኘቱ ቀጥሎ እርሱን የማስፈታት  እንቅስቃሴዎች ተበራክተው  ነበር፡፡   
  እ.ኤ.አ በ1982  ማዴላና ሌሎች የኤኤን ሲ መሪዎች   ከደቡብ አፍሪካ  መንግስት  ጋር  ለመነጋገር  እንዲያመች ወደ ፖልስሙር  እስርቤት  ተዘዋወሩ፡፡  እ.ኤ.አ በ1985 ፒ .ደብሊው ቦሳ የትጥቅ ትግልን በማቆምንና ማንዴላ ለመፍታት የፈለገ ቢሆንም ታሳሪዎቹ ሀሳቡን አጣጥለውታል፡፡  በአቅራቢያውና በዓለም ዓቀፍ ደረጃ  በደቡብ አፍሪካ  መንግስት  ላይ ከፍተኛ  ግፊት  ይደረግ የነበረ  በመሆኑ መንግስት ከማንዴላ ጋር ለመደራደር ብዙ ንግግር አድርጎ  ግን ምንም  አይነት ስምምነት  ላይ  አልተደረሰም፡፡   ይህ ድርድር  ፒ ደብሊው ቦሳ ሥልጣናቸውን  ለቅቀው ፍሬድሪክ ዊሊያም ዲ ክለርክ ፕሬዚዳንት  በመሆን የማንዴላ ከእስር  መፈታት  እ.ኤ.አ የካቲት 11,1990 ድረስ ድርድሩ አልተሳካም  ነበር፡፡   ዲክሌርክ  ማንዴላን  ከማስፈታት  በስተጨማሪ  የኤኤን ሲ ፖለቲካዊ  እንቅስቃሴ  እገዳ እንዲነሳ እንዲሁም የፖለቲካ  ቡድኖች  እንቅስቃሴ ላይ የተጣለው  እገዳዎች  እንዲነሳም  አድርገዋል፡፡ 
ከእስር  መፈታትና የፕሬዚዳንትነት  ጊዜ

ኒልሰን ማንዴላ ከእስር  ከተፈቱ በኃላ ወዲውኑ ለውጭ  ሃይሎች የደቡብ  አፍሪካ  መንግስት ህገመንግስታዊ ሪፎረም እንዲያደርግ  ግፊታቸውን  እንዲቀጥሉ ጥያቄያቸውን  ያቀርቡ  ጀመር፡፡ ከዚህው ጎን ለጎን በሰላማዊ  እንቅስቃሴ  ረገድና የኤኤኔሲ የትጥቅ ትግል  የአብዛኛው ጥቁሮች  በድምጽ የመወሰን  መብት እስኪረጋገጥ ድረስ  መቀጠል  እንዳለበት  አወጁ፡፡  

እ.ኤ.አ በ1991  ማንዴላ  የህይወት ዘመን ባልደረባው የሆኑት ኦሊቨር ታምቦ  የአፍሪካን ብሔራዊ  ኮንገረስ ሊቀመንበር ሆኖ ሲመረጡ   ኒልሰን ማንዴላ  ደግሞ ፕሬዚዳንት  በመሆን  ተመረጡ፡፡ ማንዴላ  ከኤፍ  ደብሊው  ክለርክ  ጋር ሁሉን  አቀፍ  ምርጫ  እንዲካሄድ  ድርድር  ማድረግ  ጀመሩ፡፡  በዚህ  ወቅት  ነጭ   ደቡብ  አፍሪካኖች ሥልጣን  መጋራት የሚፈልጉ ሲሆን  ጥቁሮቹ  አፍሪካኖች ደግሞ ሙሉ በሙሉ ስልጣን መረከብ የሚፈልጉ በመሆኑ በዚህ ምክንያት በተለያየ  ጊዜ ብጥብጥ እየተነሳ የኤኤኒሲ  መሪዎችም  መታሰራቸው  አልቀረም፡፡

ማንዴላ  በዚህን  ወቅት  ማንዴላ  ሚዛናዊ የሆነ ፖለቲካዊ አቅም እንዲኖርና  ህዝባዊ እንቅስቀሴውና የትጥቅ  ትግሉ መካከል ድርድሩ  ላይ ግፊት  ነበር፡፡

እ.ኤ.አ በ1993 ማንዴላና ፕሬዚዳንት ዲ ክለርክ   አፓርታየድን ለመሰወገድ  ባደረጉት  ጥረት   በጋራ   የሠላም ኖቤል ሽልማት  አግኝተዋል፡፡
 ደቡብ አፍሪካ የራሷን የመጀመሪያ  ዲሞክራሲያዊ ምርጫ  አካሂዳ ግንቦት 10,1994 ኔልሳን  ማንዴላ  በ77 ዓመታቸው የአገሪቱ የመጀመሪያ  ጥቁር  ፕሬዚዳንት  ሆነው  የተመረጡ ሲሆን ዲ ክለርክም  ምክትላቸው   ሆነው  ተመረጡ፡፡
 በዚሁ  ዓመት ማንዴላ  በአብዛኛው  እስር  ላይ  በነበሩት  ወቅት ጽፈውት  የነበረውን የነፃነት  ጉዞ( Long Walk to Freedom) የተሰኘውን  የግል ታሪካቸው የሚያሳይ  መጽሐፍ አሳተሙ፡፡
የማንዴላ  ተግባራቶች
·         እ.ኤ.አ ከ1994 እስከ ጁን 1999 እ.ኤ.አ ማንዴላ  ከጥቂት  ነጮች የአገዛዝ ሥርዓት  ወደ  ብዙኃኑ ጥቁሮች  እንዲለወጥ ከፍተኛ  ጥረት  አድርጋል፣
·          ስፖርታዊ ዝግጅቶችን  ጥቁርና  ነጭን የማግባቢያና የማስታረቂያ  መድረክ  አድርገዋል፣
·           ማንዴላ በእርሳቸው የአገዛዝ  ዘመን  አገሪቱ ሊገጥማት  የነበረውን  የኢኮነሚ ውድቀት ለመከላላከል ሠርተዋል፣ በእሳቸው የመልሶ ግንባታ የልማት ዕቅድ  የጥቁር  አሜሪካ  መንግስት  ለዜጎቹ የሥራ  ዕድል፣ የመኖሪያ  ቤት  አቅርቦትና  የጤና  እንክብካቤ   ለማመመቻቸት ችለዋልል፣
·         እ.ኤ.አ በ1996 ማንዴላ  በአብላጫ  ድምጽ የሚመራ አዲስ  ጠንካራ የማዕከላዊ መንግስት፣ የአነሳ ቡድኖች  መብት የሚያከብር እና  የሀሳብ  ነጻነትን የሚያረጋግጥ  አዲስ   ህገመንግስት  ተግባራዉዊ እንዲሆን  አድርገዋል፣
·         በጡረታቸው  ጊዜም በእርሳቸው ስም  በተቋቋመው ፋውንዴሽን በደቡብ  አፍሪካ  በየገጠሩ  ት/ቤትና  ክሊንክ  እንዲገነባ  አድርገዋል፡፡  
·         በብሩንዲ የእርስ በእርስ  ጦርነት   በሸምጋይነት  ሰርተዋል፣
·         በህይወት  ዘመናቸውና  በትግል  ሂደታቸው  ዙሪያ  የሚያትቱ  መጽሐፍቶች   አበርክተዋል  ለአብነት  ያህልም   ለነጻነት  መንገዱ  ጨርቅ  አይደለም (No Easy Walk to Freedom)፣ ኒልሰን ማንዴላ(Nelson Mandela) መታገል ህይወቴ  ነው( The Struggle is my Life)  እና የኔልሰን  ማንዴላ  ተወዳጅ የአፍሪካ  አፈታሪኮች  ( Nelson Mandela's Favorite African Folktales) የተወሰኑት ናቸው፤
·        ማንዴላ  እ.ኤ.አ ጁላይ 18,  2007  ዴዝሜንቱቱን  ጨምሮ ታዋቂ የአገር ሽማግሌዎች  ያሉበት  › ሽማግሌዎቹ › የሚባል ቡድን ሰብስበው  በኢሲያ ፣ሩቅ ምስራቅና አፍሪካ ላይ  ሰላምን፣ የሴቶች እኩልነትና  የሰብአዊ ሥራ  ላይ  ቀላል  የማይባል  ተግባር  አከናውነዋል፤
·         ማክጋቶ የተባለው  ወንድ ልጃቸው የሞተበትን  የኤች አይቪ  ኤድስ  በሽታን  በመከላለከል  ዘመቻ ረገድ ላይም  ተሳትፈዋል፤
የማንዴላ የጋብቻ  ሁኔታ
ማንዴላ እ.ኤ. አ 19 44-1957 ኤቪሊን ንቶኮ ማዚ  ከተባለች የመጀመሪያ  ሚስቱ አራት  ልጆች  የወለደ  ሲሆን በ1958 እ.ኤአ የተፋቱ  ሲሆን፤  በዚሁ ዓመት ዊኒ  ማዲኬዚላን በማግባት ሁለት ሴት ልጆች  ወልደው፤ ለሁለተኛ  ጊዜ ከእርሷ  ጋር ፍቺ ፈጽመው እ.ኤ.አ በ1998  ከቀድሞ የሞዛምቢኩ መሪ ባለቤት ከነበሩት ግራሳ ማቼል ጋር ለሦስተኛ ጊዜ ጋብቻ   ፈጽመዋል፡፡
 የማንዴላ አሟሟት
ኒልሰን ማንዴላ እ.ኤ.አ  በ2001 የፐሮስቴት   ካንሰር  በሽታ  ተጠቅተው የተከሙ  ሲሆን፤  ለመጨረሻ  ጊዜ  ለህዝብ የታዩት   በ2010 በደቡብ  አፍሪካ  በተደረገው  የዓለም የእግር  ካስ የዋንጫ ውድድር  ላይ  ሲሆን  ከዚያ ወዲያ ጊዚያቸውን የሚያሳልፉት  የልጅነት መኖሪያቸው  በነበረው የኩኑ መንደር   ህብረተሰብ  ጋር  ነበር፡፡  ማንዴላ  በ2011 ላይ  በሰንባ  ኢንፌክሽን ታምመው ሲሰቃዩ ቆይተው የተለያየ  ህክምና  ሲሰጣቸው  ቆይተው  ከዚህ  ዓለም በ95  ዓመታቸው ዴሴምበር 5,2013 በሞት  ተለይተዋል፡፡
         እ.ኤአ በ2009 የኒልሰን  ማንዴላ የልደት ቀን የሆነው ጁላይ 18, የማንዴላ ቀን  በማለት በአለም ደረጃ እንዲከበር  በማድረግ  ሠላምን  ለማበራታትና  የደቡብ  አፍሪካዊው  መሪን ሌጋሲ ለማከበር  ታውጃል፡፡



 የማንዴላ  አስተምሮት
ማንዴላ  ለመላው የጥቁር  ህዝብና  ለዓለም  ትግስትን፣ለዓላማ  ታማኝነትን፣ ውጣውረድን፣ ለህዝብ ጥቅም ህይወትን  አሳልፎ መስጠትን፣ የዓላማ ጽናትን ፣ መልካምነትን  እንዲሁም ሥልጣን  ሲይዙ ተቃናቃኞቻቸውን  ድምጥማጥ የሚያጠፉ መሪዎች በበዙባት የአፍሪካ  ምድር  እርቅ ያወረደ  የተበደለበበትን  ጊዜ  ወደ ኃላ  የአለየ፣ በህዝቡ ላይ ይቅርታ መንፈስ እንዲሰፍን የደቡብ  አፍሪካ የእውነትና የእርቅ ኮሚሽን የተሰኘ ፍርድ ቤት  መሰል አግባቢ ተቋም  ከእነ ዲዘሞንቱቱ  ጋር  በማቋቋም ተቀናቃኞቹና የማድቀቂያ የሥልጣን  መንበር በቁጥጥሩ ስር  ሆኖ ሳለ ብሔራዊ መግባባትና የይቅርታ  በመላ  አገሪቱ እንዲሰፍን  ያደረገ  ብልህ  መሪ  ነው፡፡    
 የኒልሰን ማንዴላ መታሰነቢያ  ማዕከል  ድረገጽ  እነደህ  የሚል  ጹህፍ  አስፍራል፡-
    “ ሚስተር  ማንዴላ  የ67 ዓመት  ዕድሜ ዘመኑን ለሰው  ልጅ  መብት  መከበር  በመታገል አሳልፋል !  አሁን  እኛ የምንጠይቀው እውን   ቢያንስ  ለ67  ደቂቃ ም ያህላችን ነን  ለሰብአዊ ተግባር  ወይም  የአካባቢያችን ህብረተሰብ  ለማገልገል የምናውልው?! ”  ብሎ ይጠይቃል፡፡
     እውነት  ነው  ማናችን   ለህዝብ ጥቀም  ብለን  ምንም  በግላችን  ባላጠፋነው  ጥፋት የቀለም ልዩነት፣ የዘር ቆጠራ ይቅር፣ በእኩል  ዓይን  እንታይ ስላልን  27  ዓመት  ተፈርዶብን በትግስት የያዝነውን  አቋም ይዘን  በጽናት  እንቆያለን?!  ከአሳሪዎቻችን  ጋር  አንደራደርም በጋሮ በኩል?  ወይም  የህዝብ  መሪነን  እያልን  በአፍ ቀላጤነት ላይ ላዩን እያመስን  የእስር  ጉዳይ  ፊት ለፊችን  ሲደቀን የምንመራውን ትተን የጨበጥነውን  በትነን  በአሳሪዎቻችን  ጉያ ሥር አንወሸቅም?! ልጄን  ሚስቴን  የወጣትነት ያማደጊያ  የሠርቶ መብያ  ጊዜዬን ብለን  ከዓላማችን  በተቃራኒ የማንቀመጥ ወይ ደግሞ እጃችንን  አጣምረን በደልን አልሰማውም  አላየሁም ብለን የምንመለከተስ የለንም?!  በጊዚያዊ ጥቅምስ ዓላማችንን አንቀይርም? ሥልጣን  በእጃችን  ገብቶስ በመብራት  እየፈለግን  ጠላቶቻችን  ናቸው  የምንለውን አናሳድድም?!   ማንዴላ  ግን ይህንን  አላደረገም!!  እሱ  ነው በትግስትና  በፍቅር  ያሸነፈ  የጠላቶቹም  ጭምር የሁሉም መሪ!!