ረቡዕ 1 ኤፕሪል 2015

ይድረስ ለባዶ ራሶች!



ይድረስ ለባዶ ራሶች!
  
   ይህ መልዕክት በተለያየ ቦታ ሆነው ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊያንን ለሚያደክሙ፣ ለሚያሳምሙ፣ለሚያራቁቱ፣ለሚያሰቃዩ በህሊናው ኢትዮጵያኖች ስም የተጻፈ የኢትዮጵያ ራዕይ ነው፡፡
           በተለያየ ወንበር ላይ ተቀምጣችሁ እናንተና እናንተን ብቻ የምታዩ፣ ያለእናንተ አዋቂ የሌለ የሚመስላችሁ ማሃይሞች በገረወይና ጭንቅላታችሁ ስትነኩ ከመጮህ በስተቀር ማስተዋል የሌላችሁ፡፡ ምላሳችሁ የሚርገበግብ አንገታችሁን ዞር አድርጋችሁ ለማየት የተሳናችሁ በገዛ እጃችሁ አንገታችሁን የቀሰራችሁ፡፡ ቢሮአችሁ ውስጥ ኢትጵያዊነትን ለማጥፋት ተግታችሁ የምትሰሩ፡፡ ወንደማችውን ጠላት ጠላታችሁን ወዳጅ የምታድርጉ፡፡ አይናችሁ የፈጠጠ ግን የማያይ፡፡ ጆራችሁ የቆመ ግን የኢትዮጵያ ህዝብ የሲቃ ጨኹትና እሪታ የማይሰማችሁ፣ ታሪክ የምትከልሱ የምታፈርሱ  የራሳችሁን የተሳሳተ ታሪክ በጉልበት የምታስውጡ፡፡ ድንቁራናችሁ ያልገባችሁ ቀሽም ድራማ ፈትቶ ለሚገጥማችሁ ህዝብ የምትሰሩ፡፡ አይኔን ግንባር ያርገው የደንቆሮ ለቅሶ የማይገባችሁ፡፡ ህሊናችሁን ፈጥፍጣች በእግራችሁ የጨፈለቃችሁ፡፡ ንጹህነት ጠላታችሁ፡፡ መልካም መሥራት ሴጣናችሁ፡፡ ህግ ማክበር እብደታችሁ፡፡ በቴሌቪዥን በሬድዮ፣በአዳራሽ በሆቴሉ የውሸት የምትለፍፉ፣ ዶሮ ሳይጮህ ጩህታችሁ መቶ ጊዜ ውሃ የሚበላው የጮሆኃችሁበትን ሰነድ በእግራችሁ የምትረጋግጡ፡፡ የራሳችሁን ጩህት ለራሳችሁ የምታዳምጡ፡፡ ህይወት ጤፉ፣ አዛውንት፣ ሽማግሌ፣ የሃይማኖት መሪ፣ እርጉዝ፣ እመጫት፣ ሴት፣ ህጻን፣አቅመ-ደካማ የማይገባችሁ፡፡ የኢትዮጵያዊያን ደም ጥቁር ነው የምትሉ፡፡ እናንተ ወራሪዎች ኢትዮጵያን የማፈራረስ ስራ የምትዳክሩ፡፡
          አናንተኛዎቹ ደግሞ! ከኃላ ከኃላ ጡልጡል እያላችሁ ንጹህ የምታስፈጁ፣ በመኪና መንሸራሸራችሁ፣ ህንጻ መገንባታችሁ ብርቃችሁ፡፡ የስምዝርዝር እየሰጣችሁ በድንጋይ የምታስወግሩ፣በጥይት የምታስደበድቡ፣ የእኛ ነው የእነሱ ነው እያላችሁ እንደ ቅርጫ በመመደብ ሰው በቁም የምትገሉ፡፡ ወንድም እህታችሁን እናት አባታችሁን ለሆዳችሁ ለክርሳችሁ ብላቻሁ የምታስፈጁ፡፡ ኢትዮጵያዊ ስነልቦና ከውስጣችሁ ያጸዳችሁ፡፡ በሰው ህይወትና፣ ኑሩ ቁርጥ የምትቆርጡ ወስኪ የምትለጉ፡፡ አንድ ኪሎ ሥጋ ለመግዛት የትየለሌ ሰልፍ ጸሃይ አናቱን እየወቀረው በሚጠብቅ የአገር እድገት ላም አለኝ በሰማይ የሆነበት ህዝብ ላይ ሙድ የምትይዙ፡፡ ነገ ማለት የማታስቡ፣ ልጆቼ፣ሀገር ፣ትውልድ መጥፋት ለቅንጣት ያህል ስሜት የማይሰጣችሁ፡፡ የተለያያ ካባ ለብሳችሁ ያለቆቻችሁን  መፈክር ጉሮሮአችሁ አስኪነቃ ድረስ የምታስተጋቡ፡፡ ጎረቤት፣ቤተሰብ፣ዘመድ ሰው ምን ይለኛል የማትሉ፡፡ አንገታችሁ ላይ የተቀመጠውን ገረወይናችሁን ነቅነቅ ማድረግ እንኳን ያልቻላችሁ፡፡ እከሌ እንደዚህ ነው… እከሌ ደግሞ….. እንደዚህ እያላችሁ ደምወዝ የሚከፈላችሁ፣ቤት የሚሰጣችሁ፣ መኪና የሚለገሳችሁ፣ መሬት የምትወሩ፣ይምታስወርሩ፣የደሃ ቤት የምታስፈርሱ ለሃብታም ደሃ የምትጠርጉ፣ጎዳና ተዳዳሪ በየእለቱ የምትፈለፍሉ፣ በአንድ ብርሌ ቤት የምትንዱ፣የምታስንዱ፡፡ ከራስ በላይ ህግ የምትሉ፡፡ ድንጋይ ትራስ አድርጎ አውላላ ሜዳ ላይ የሚተኛን ህዝብ በስፖንጅ ፋራሻችሁ መተኛት አቅቷችሁ በድንጋይ ትራስ የምተቀኑ፡፡ ንኮች!   
   እናንተ የእውር መሪዎች፡፡ በማይረባ ጥቅማጥቅም በህዝብ ስሜትና ህይወት ጥባጥቤ የምትጫወቱ፡፡ ኑሮአችሁን ለማደላደል ሳይጠራችሁ አቤት፤ ሳይልኩአችሁ ወዴት የምትሉ፡፡ በነጻ ሞያተኛ ስም ሸፍጥ የምትሰሩ፣ ከርሳችሁን የምትሞሉ፡፡ ባገኛችሁት መንበር ምላሳችሁን  የምታንቀጠቅጡ፡፡ የራበው ህዝብ መሪዎቹን እንደሚበላ እናንተ የገዳዮች አሽከሮችን መብላት ብቻ አይደለም በጥርሱ ያኝካችኃል! ይሰለቅጣችሁልም! የተቀበላችሁት እጅ መንሻ፣ በግፍ የከመራችሁት ሀብት የተራራ ያህል ቢቆለልም መደበቂያ አይሆናችሁምና፡፡ ሚለየን ብራችሁ አይናችሁ እያየ ጉም ይሆናል፡፡ በፈጠራ ወሬያችሁ የናዳችሁት ታሪክ፣ ያፈረሳችሁት ቤት፣ማህበር፣ ህዝብ የመጨረሻው ሰዓት ላይ ፊታችሁ ለፍርድ ይቀርብላችሁና ሴጣን አሳስቶኝ ነው፣ለእንጀራዬ ነው፣ መሳሪያ ተደቅኖብኝ ነው፣አማራጭ ስሌለኝ ነው፣አህምሮዬ ተሰውሮብኝ ነው፣መድሃኒት ተደርጎብኝ ነው ብላችሁ ብትመልሱ አጠገባችሁ ሲጮህባችሁ ጆራችሁን ይዛችሁ አልሰማሁም የማሪያምን ብቅል እፈጫላሁ እያላችሁ መደንቆራችሁ አይጠቅማችሁምና ያን ግዜ ወየውላችሁ፡፡    
  ለወጋናቸው አለው የሚሉ ንጹህ ኢትዮጵያውያኖችን እንደ እብድ የመትቆጥሩ፣ ቀውሶች! ባልደረቦቻችሁ ለህሊናቸው ሲኖሩ እናንተ ሆዳችሁን ማሳበጣችሁን እንደ ውጤታማነት እየጠቀሳችሁ ስም የምታጠፉ፣ ለማሰጠፋት ቀድማችሁ እጃችሁን የምትቀስሩ፡፡ ጨለማ ውስጥ  ሆናችሁ የጸዳ ሰው ለማጥፋት የምትረባረቡ፡፡ ፍርፋሪ ለመልቀም ሬሳ የምታስነሱ፡፡ እስርቤት ባሰገባችሁቸው እህትና ወንድማቾቻችሁ ስቃይ እናንተ የምትዝናኑ፣ ቂጣችሁን የምታሰፉ፣ በየሆቴሉ የአንድ ፍሬ ህጻናትን ገላን የምታረክሱ፡፡ ሲያሻችሁ በኢትዮጵያ ህዝብ ገንዘብ መሬት አይንካኝ ብላችሁ የድሃ ልጅ፣ የታጋይ ልጆች አፈር ሲበሉ፣ የእናት የአባት ያለህ ሲሉ እናንተና በአጢያት የፈለፈላችሃቸው ምንዓልባት ነገ እናንተ ብታመልጡ እንኳን እነሱ ፍዳቸውን የሚቆጥሩበትን የክፋት የማዕዘን ድንጋይ ያኖራችሁ፡፡   
እውነት እውነት እላችኃለው! ይህን ህዝብ ያጤሳችሁትን ያህል በሰፈራችሁት ቁና ተመርቆ ተዝቆ ይከፈላችሁል፡፡ ሰማዩ ጠቁሮ ሲታይ አይናችሁ አላይም ያላችሁ ምልክት ይሁናችሁ! የእናንተ ክፍት የመጨረሻ  ሰዓት ላይ መድረሱ ነው፡፡ እውነት እውነት እላችሃለው ይህ አይኑ ደም ለብሶ የሚያያቸሁ ሀዝብ በሶ ጨብጦ፣ደንጋይ ፈልጦ የእናተን ቡራኬ አይጠብቅምና ያን ጊዜ ወየውላችሁ! ማህበራችሁ፣ጉርሻችሁ፣ነፍጣችሁ፣ቁርኝታችሁ፣የተደገፋችሁት የሀሰት ግንባችሁ እንደ ጉም ብን ብሎ የሚቀር ነውና ያን ግዜ ወየውላችሁ! የእናታችሁ ቀሚስ፣  የሚስታችሁ ቀሚስ በህጻናት አምላክ ብላችሁ የህጻን ሴት ልጆቻችሁም ቀሚስ መደበቂያ አይሆናችሁምና፡፡
  እውነት እውነት እላችኋሃለው በቤቲክርስቲያን ውስጥ እንደ ካህን በመስጂድ ውስጥ እንደ ሼክ ለብሰው አመራር የሚሰጡ የሚቀበሉ አብዮተኞኝ ሲበዙ ያን ጊዜ አብዮት ራሷን ልተባላ ነውና ወደ ውስጥ ተመልከቱ!
አውነት እውነት እላችኋለው ለሀገሬ እያሉ ለጌታቸው እያቅራሩ፣እየጨፈሩ ያዙኝ ልቀቁኝ የሚሉ ሀገርና ጌታቸውን መለየት አልቻሉምና ወይም በሀገሬ ሰበብ ሆዳቸውን እየሞሉ ነውና ይህን ጊዜ አለን አለን ከሚሉ የቀለም ሽፍታዎች ጨኽት ምድብ ያልተለዩ ስለሆነ ያን ጊዜ በእውነት ላይ ሴራ እየተሰራ ስለሆነ ምልክቶችን ከወደ ምስራቅ ተመልከት፡፡  
   እውነት እውነት እላችኋለው! ጭፈራ ሲበዛ፣ ግርግር ሲመጣ፣ የራበው ህዝብ አንጀቱን ጨምቆ ራበኝ ማለት ሲያቆም፣ በእናንት  ግፍ ፍትህ አጥቶ እሲክርበው ሲጨሁ የነበረ ህዝብ ድምጹን ሲያጠፋ ያን ጊዜ ጊዜው ደርሳልና ወየውላችሁ፡፡ ነብሮች ድመት ድመቶች ነበር ሲሆኑ፣ የተማረ ያስተምር ያልተማረ ይማር የሚለው ተገልብጦ ያልተማረ ያስተምር የተማር ይማር የሚል መፈክር የበዛ ጊዜ የምትረግጡት መሬት ሊሰምጥ ነውና ያን ግዜ ወየውላችሁ፡፡
    ሀገሬ የሚሉ፣ አሁንስ በዛ፣ፍርዓት እራሱ ይፍራን፣ ሰይፍ አንፈራም ከሰይፍ የበለጠ እኛ ስል ነን የሚሉ ሰዎች ብቅብቅ ማለት ሲጀምሩ ያን ጊዜ ምልክት አይታችሃልና የእናቴ መቀነት ጠለፈኝ ሳትሉ ከንፋስ በፈጠነ ሁኔታ የማስመስል ለፍርፋሪ ለቴሌቪዥን ሳይሆን ለህዝብ የእውነት ሀገሬ ከሚሉ ወገኖች ተርታ ሳትሰለፉ የቀራችሁ ዕለት በግራ የመቆማችሁ ምልከት ይሁናችሁ፡፡                              
  ከአህያ ቆዳ የተሠራ ቤት፣ ፍርስርስ ይላል ጅብ የመጣ ዕለት፤ የሚባለውን ተረት የሚተርት ሲበዛ ቀኑ የተቃረበ ጊዜው የደረሰ መሆኑን በራዕይ አይነገርምና ያን ጊዜ ወየውላችሁ!!
    በዝራው አሻግሬ

ቅዳሜ 28 ፌብሩዋሪ 2015

በነጋዴዎች የተወረረች ቤተክርስቲያን!



በነጋዴዎች የተወረረች  ቤተክርስቲያን!

   
   «እየሱስም ወደ መቅደስ ገባና በመቅደስ የሚሸቅጡትንና፣ የሚገዙትን ሁሉ አወጣ የገንዘብ ለዋጮችንም ገበታዎች ፣የርግብ ሻጮችንም ወንበር ገለበጠና፡- ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላላች ተብሎ ተጽፎአል፤ እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋአችሁት፤ አላቸው፡፡»
                                     የማቴዎስ ወንጌል ምዕራብ 21 ቁ. 12

    አሁን አሁን መንገድ ዳር ያለ የቤተክርስሪያን አጥር ማግኘት ፈታኝ እየሆነ መጥቷል፡፡ ቤተከርስቲን በተለያየ የንግድ ተቋማት ዙሪያዋን ተወራ ነው የምናስተውለው፡፡ አንድ መእምን የቤተክርስሰቲያን በር ላይ መድረስ ቢያቅተው በርቀት የቤተክርስቲያና የግንብ አጥር በመዳሳስ እባረካለው ብሎ ማሰብ ለእርሱ እንደ በፊቱ አሁን ቀላል አይደለም፡፡ በተለያዩ የንግድ ቤቶች የተያዘውን አጥር በማለፍ ለንግድ ቦታ ለጊዜው ያልፈረሰ አጠር ለማግኘት ቤተክርስቲያናን  ዙሪያውን መሸከርከር ይጠበቅበታል፡፡ በመከራ በንግድ ቤቶች መካከል ወይም አጠገብ የተገኘ የቤተክስቲያና አጠር ቢኖር  መሳለማችን የተባረክን ያህል  ውስጣችን ላይሰማን ሁሉ ይችላል፡፡

    ቤተክርስሲያን የንግድ ማዕከል ወይም የጉልት አይነት ሳትሆን ቃለ እግዝሐብሔር የሚሰማበት፣ ጸሎት የሚደረግበት ፣የተረጋጋ መንፈስ የሚታይበት እንዲሁም ምዕምናኑ ራሱን ለማረጋት የሚመርጠውና የሰከነ መንፈስ አገኝበታለው ብሎ አንድ ክርስቲያን የመጀመሪያ ምርጫው የሚያደርገው ቦታ ቢኖረ  ቤ/ክርስቲያን ናት፡፡ ምክንያቱም የዓለም ጫጫታና ሁካታ ሰልችቶት ለዚህ ደግሞ የእግዛብሔር መንፈስን አገኛለው ብሎ መጥቶ ቤተክርስቲን ዙሪያዋን በነጋዴዎች እሰጣ ገባ ሰላሟ ተናግታ ቢያገኝ እሸሸግበት ጥግ አጣሁ ቢል ምን ይፈረድበታል፡፡
   ዛሬ ከቤቴክርስቲያን አጥር ዙሪያ የልብስ መሸጫ፣የመኪና ዕቃ መሸጫ፣ኢንተርኔት ቤት፣ካፌ፣ኤሌክትሮኒክስ መሸጫ፣ የመኪና  ማከራያ፣ፎቶ ቤት፣ባንክ ቤት፣ስፖርት ቤት፣ጸጉር ቤት፣ የብሎኬት ማምረቻ  ወዘተ…. ማየት አዲስ አይደለም፡፡ አዲስ ወይም እንግዳ  ሊሆን የሚችለው ቤተክርስቲያን አጥሯን ለነጋዴዎች ሳታከራይ ጦማን ስታድር ማየት ነው፡፡  ይህንን  ቢዘነስ የለመደ አንድ ካህን ዋ! ማኛ ቦታ  ነው ጦሙን ያሳደሩት ብሎ የቤተክርስቲያኗን  ሰበካ ጉባኤ በሆዱ ሊረግም፣ በጋዶኞቹ ወይንም ግንኙነት ካለው በአካል በመሄድ ጥቆማ አይሰጥም ማለት እንግዳ ነው፡፡ እያወራን ያለነው በከተማ ውስጥ ስለ አሉ ቤተክርስቲያናት ነው፡፡     
   የመጽሐፍ ቅዱስን ማቴዎስ ወንጌል ምዕራብ 21 ቁ.12 ምክንያት በማድረግ ቁጥራቸው ቀላል ያልተባለ የቤተክርስቲያን ሊቃውንት በቤተክርስቲን ዙሪያ መነገድ ወይም ማስነገድ ክርስቶስ ቤቴን የወንበዶች አደረጋችሁት ካለው ጋር የሚመሳሰል ነው፡፡ ይህ ተግባር የሽቀጣ ሥራ ሥለሆነ ትክክል አይደለም ይላሉ፡፡ አንዳንዶች ደግሞ የማይገናኝ አታገኛኑ ቤተስኪያን ቅጥር ጊቢ ውስጥ መሸቀጡ ነው ችግሩ! ከምዕመናን ከሚገኝ ገቢ ብቻ ቤተክርሰቲያን መተዳደር የለባትም፡፡ የራሷ የገቢ ምንጭ ሊኖራት ይገባል፡፡ ከኛ ተርፎ ለአባይ ቦንድ ልንገዛ አቅም ያገኘነው የገቢ ምንጭ በመፍጠራችን ነው ነው ይላሉ፡፡  

     ለምንድን  ነው ቤተክርስቲያን  አጥሯን እያፈረሰች  ገበያ የምታደርገው?   

   አንድ አንድ ለቤተክርስቲያና አስተዳደር ቀረቤታ አላቸው የሚባሉ ሰዎች እንደሚገልጹት ቤ/ክርስቲያን ከምዕመናኑ በተለያዩ ምክንያት ከምትሰበስባቸውና ከምእመናኑ መጽዋተ ሙዳይ ከምታገኘው ገቢ በስተቀር ይህን ያህል ለቤተክርስቲያና አገልጋዮች የምትከፍለውን ደምወዝና ለተለያዩ ልማታዊ ሥራዎችን የምታከናውንበት በቂ ገንዘብ ስለሌላት ነው የሚል ምክንያት ይሰጣሉ፡፡ 
      እርግጥ ነው የቤተስኪያን አገልጋዮችና ሌሎችም ልማታዊ ሥራዎችን ለመስራት  ገንዘብ  ያስፈልጋል፡፡  ቢሆንም የቤተክርስቲያን አጥርን እያፈረሱ  ቤተክርስቲያን በንግድ ቦታና በአምልኮተ እግዝሃብሔር ሥፍራነት ከመቀላቀል ውጪ የቤተክርስቲያንን የተረጋጋ  መንፈስና ቤተክርስቲያናዊ ድባብ ጠብቆ ገቢ የሚገኝበት ሁኔታ የለም? ከምዕመናኑ የሚሰበሰቡ የስለት ገቢዎች፣ የስብከተ ጉባኤ የአባልነት ክፍያ፣ ከመካነ መቃብር ማሰፈጸሚያ ገቢ፣ከሙዳየ መጽዋት ገቢ፣ በቤተክርስቲያን በሚተዳደሩት ትምህርት ቤቶች ከሚገኝ ገቢና መሰል ገቢዎች የሚገኝ ገንዘብ የተገለጸውን ወጪ ለመሸፍን አይቻልም ይሆን? ሌሎች መእመናኑን  በሃይማኖቱ ጸንቶ እንዲቆይ የሚያደርጉና በአንጻሩ ደግሞ ገንዘብም የሚገኝባቸው እንቅስቃሴውዎች ማድረግ አይቻል ይሆን?! የሚገርመው አንድ አንድ ገዳማት ምዕመናኑ ከቤቴክርስቲያኑ ውስጥ በአጥሩ ዙሪያ ቁጭ ብለው ጸሎት የሚያደርሱበትን፣ ስብከተ ጉባኤ የሚሰሙበትና በሰከነ መንፈስ ከፈጣሪያቸው ጋር እንዲገናኙ በሚል የተዘጋጀውን የፀሎት ቦታና ቂጥን ማሳረፊያ ሥፍራን  ሳይቀር በማፈራረስ ለንግድ ቦታ  እየተከራየ ነው ያለው፡፡

  ለንግድ  ተረግባር አጥር  በርግዶ መከራየት  ካለበትስ  የቤተክርስሰቲያና የእምነት ስፍራነት ለማያውክ የንግድ ሥራ ማከራየት ይቸግር  ይሆን?  

   በተለያየ አጋጣሚ ቤተክርስቲያና ለምታከራያቸው ግለሰቦች የምታዘጋጀውን የስምምነት ውል በሥራ አጋጣሚ እጄ  ሊገቡ ችለው የውሉን ይዘት ለማየት ችያለው፡፡ ውሎቹ በአብዛኛው በቤተክርስቲያኗ የሚዘጋጅ ወይንም አንዱ ደብር ከአንዱ ደብር ገልብጦ የሚያመጣው  በአብዛኛው ተመሳሳይ ይዘት ያላቸው የውል አይነቶች ናቸው፡፡ ሁል ጊዜ በቋሚነት የሚጠቀሰ አንድ አረፍት  ነገር/አንቀጽ አለ፡፡  ይህውም ተከራይ  ወገን (ውል  ተቀባይ) በተከራየው  ቤት ከቤተክርስቲያኗ እምነት ጋር የሚጣረስ ተግባር ማከናወን የለበትም የሚል ነው፡፡ ይሄ  አንቀጽ በተለያየ አገላለጽ በየተለያ ደብሮች የውል ስምምነት ውስጥ ተጠቅሶ  ቢገኝም  ሁለት  ችግሮች  ይታዩበታል፡፡
   አንደኛው የሀረጉ ግልጽነት መጉደል(vague)ወይም ምንድን ነው ከቤተክርሰቲያን እምነትና ስርዓት ጋር የሚጋጭ የንግድ ተግባር ሲባል? በአብዛኛው የቤተክርስስቲያን አከራይ የሰበካ ጉባኤ አባላቶች ትኩረት የሚያደርጉት የመጠጥ ንግድ፣ ቤተክርስቲያና ከምትከተለው ሃይማኖት ውጪ ያሉ የእምነት ድርጅቶች እንቅስቃሴ፣ሙዚቃ ቤት ወዘተ ሲሆን ከእነዚህ የንግድ ተግባሮች ባልተናነሰ የቤተክርስቲያኗ ሰላምና መረጋጋት ወይም ድባብ የሚያውኩ የንግድ ስራዎች ላይ እምብዛም ትኩረት አይሰጣቸውም፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ምንም እንኳን ከቤተክርሰቲያን እምነትና ስርዓት ጋር የሚጋጭ የንግድ ተግባር ማከናወን እንደ የውል ማፍረሻ ምክንያት ተደርጎ የተገለጸ ወይም የተከለከለ ተግባር ቢሆንም ተከራዩ ከአከራዮቹ ጋር  ባላቸው ግንኙነት ምክንያት ተገቢው ክትትልና ውሉን የማስፈጸም ሥራ አለመሥራታቸው ነው፡፡

  የንግድ ቦታ ኪራይ  ሁኔታ  እንዴት  ነው  የሚካሄደው?  

  የቤተክርስስቲያን የንግድ ቦታ ኪራይ በአብዛኛ የሚካሄደው ቤተክርስቲያና በምታቀርበው የጫራታ ውድድርን ማዕከል አድርጎ ነው፡፡ ይሁንና ጨረታውን በአደባባይ ገልጸው በህጋዊ መንገድ የሚሰሩ ገዳማት ያሉ ቢሆንም አንዳንድ ቤተክርስቲያኖች ላይ በጨራታና በጨራታው ሂደት ላይ የሚታዩ ቀላል የማይባሉ ችግሮች አሉ፡፡ ችግሮችን ለመጥቀስ ያህል አንድ ግለሰብ  በተለያየ ስም የሚያስገባቸው የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዶች፣ ጨረታው ብዙ ተወዳዳሪ እንዳያየው በአጭር ግዜ ውስጥ እንዲከናወን ማጣደፍና የጨረታው ማስታወቂያ የማይታይበት ቦታ መለጠፍ ዋና ዋናዎቸ ሲሆኑ የተለያየያ ጫራታውን የቤተስኪያኗ አስተዳደሮች ለሚፈልጉት ወይም ለተደራደሩት ሰው እንዲያመች ለማድረግ የሚፈጠሩ አንቅፋቶቸ አሉ፡፡ የሚመለከታቸው የቤተክርስቲያን አስተዳሮች ጨረታ ከማውጣታቸው በፊት ገንዘብ አለው ብለው ያሉትን ግለሰብ ወይም  ቡድን ፣ጨረታ ሊያወጡ መሆኑን የተጠየቀው ግለሰብ ለጨረታው  ፍላጎት ያለው መሆኑን ይጠየቃል፣ ወይም ከኮሚቴዎቹ አንዱ ለሚያውቀው ሰው መንገዱ እንደሚያመችለት  በመግለጽ ለጨረታው ይጋብዛል፡፡ ወይም የቤተክርስቲያኗ አጥርን አፍርሶ የሆነ ንግድ  ለመነገድ የቋመጠ ሰው ለሚቀርቡት የቤተስኪያን ሰዎች ወይም የቤተስኪያን ሰዎችን በሚቀርቧቸው ሰዎች አማካኝነት እነእርሱ በግል ሊያገኙ የሚችሉትን የገንዘብ መጠን በመግለፅ መነሻ ሀሳብ ያቀርባል፡፡ በዚህ ሁኔታ ሂደቱ የሚጀምረው የቤተክርስቲያን አጥር አፍርሶ የንግድ ቤት ማከራየት ድርድር ለቤተክርስቲያኗ ኃላፊዎች ከፍተኛ ገንዘብ ለእጃቸው የሚያስገኝ  ነው፡፡ ድርድሩ  ከቤተክርስቲያና ራቅ ተብሎ በመጠጥ  ቤት አንድ ሁለት እየተባለ ነው የሚካሄደው፡፡       

   በዚህ ድርድር የስብከተ ጉባኤ ኮሚቴዎች፣የቤተክርስስቲያና ቁጥጥር ኮሚቴ፣  የቤተክርስቲያኗ ጸሀፊዎችም ጭምር ሊካተቱበት ይችላሉ፡፡ ለዚህ ድርድር  የማይመቹ  ናቸው በመባል የሚታወቁ ሰዎች እና  እግዝሐብሔርን ልናገለግል ነው ብለው ከልባቸው እውነተኛ ስሜት ሥራቸውን የሚከውኑ ካህናትም ሆነ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ከተለያዩ ቦታ የተውጣጡ የስብከተ ጉባኤ አባላት በምንም መንገድ እንዳያውቁ ተደርጎ ነው በጀባቸው በቤተክርሰቲያን  ስም ገንዘብ የሚሰራው፡፡

   የቤተክርስስቲን  አጥር  ዙሪያ ቁማርተኞች

እነዚህ ግለሰቦች ወይም ቡድኖች ከቤተክርስቲያና አስተዳደር እስከ ከፍተኛ የሃይማኖቱ መሪዎች ድረስ ግንኙነት  ሊኖራቸው ይችላል፡፡ ትዕዛዝ ሊቀበሉ፣ ትዕዛዝ ሊያሰጡ፣ ትዕዛዝ ሊሰጡ ሁሉ ይችላሉ፡፡ የሥራ መደብና የቤተክርስቲያን የክብር መጠሪያ  ሊኖራቸው ይችላል፡፡ የሐይማኖት ትምህረትን ያወቁ የመጠቁና የተከበሩ ሰዎች ናቸው ሊባሉ የሚችሉ ጭምር ናቸው፡፡ የቤተክርስቲያን ትምህርት ምንም ዕውቀት የሌላቸው በቤተክርስቲያና ውስጥ የማያገለግሉ ነገር ግን የድለላ አይነት ተግባር በአገር ልጅነት የሚሰሩ ሰዎችም ይገኙበታል፡፡  ገንዘብ  ሲደራደሩ ይህ በእግዝሐብሔር ቤት ላይ ነው ወይስ አንድ አለማዊ በጣም ስነምግባር የሌለው፣ ነውር፣ ርህራሄ የማያቅ የንግድ ድርጀት ሰዎች ጋር ነው የምደራደረው ልንል ሁሉ እንችላለን፡፡ እነዚህ የቤተክርስቲያን አባቶች  አይደሉም  እንዴ?  ምንድን  ነው  ነገሩ?  ልንል ሁሉ እንችላለን፡፡ ምንአልባት በእርጋታ መንፈስ በማየት ጊዜው ነው ብለን እነሱን ሳይሆን ያላቸውን ሃይማኖታዊ ማዕረግ ወይም ልብሰ ተክህኖአቸውን ማየት ነው ብለን ራሳችንን ካላረጋጋን በስተቀር  ጭንቅላታችንን  አዙሮን  ሁሉ  መሬት ላይ  ልንፈጠፈጥ  እንችላለን፡፡ 
  አንድ ጊዜ አንድ የግል ድርጅት ያለው ባለጉዳዬ ከአንዲት ቤተክርስቲያን በጫራታ  በሺዎች ካሬ ሜትር በላይ የሆነ ቦታ አሸንፌ ተከራይቻለውና መጥትህ ውል ተዋዋል ስለተባልኩኝ ሂደቱ እኔን የማይጎደኝ መሆኑንና በህግ ሊያስከትልብኝ የሚችለው ችግር በማየት ምከር ትለግስኛለህ ይለኝና  ወደ አንድ  ቤ/ክርስቲያን  አመራን፡፡ መንገድ ላይ  መኪና ውስጥ እያለን ስልክ ከተለያየ አቅጣጫ ሲደወልልት በንዴት ሲመልስ እሰማዋለው፡፡ ይሀን ያህል መቶ ሺህ ብር ሰጥቻለው በድጋሚ ደግሞ አንተ በጎን ትጠይቀኛለህ? ከዚህ በላይ ምንም አላደርግም የፈለጋችሁትን አድርጉ፡፡ እዛው መጨረስ የሚገባችሁን ለምን ወደ እኔ ታመጣላችሁ፡፡ በተናጥል አትምጡብኝ ተስማምታችሁ ኑ! ወዘተረፈ ቃላቶች ይሠነዝራል፡፡  ገረመኝና ስልኩን አናግሮ ሲጨርስ ምንድን ናቸው እነዚህ ብዬ  አልኩት፡፡ የቤተክርስቲያና ሰዎች  ናቸው  ትንሸ   የሻይ(የሻይ  ያለኝ  ኃላ ስደርስበት በመቶ ሺህ የሚቆጠር ገንዘብ ነው) ሰጥቼአለቸው ነበርና እኔ ተጎድቻለው ለብዙ ነው የተከፋፈልነው በማለት የተወሰኑት በጎን እየመጡ ነው፤ አንጣ የሚሉን አለኝ፡፡ ለምን ትሰጣለህ ጫራታውን በህጋዊ መንግድ አይደል እንዴ ያሸነፍከው አልኩት፡፡ እሱማ ነው፡፡ ግን ምን መሰለህ ጨረታውን ያሸነፉት ሌሎች ድርጅቶች ነበሩ እኔ ውስጣቸው ሰው ስለአለኝ የተወሰነ ገንዘብ ስጥና በጫረታው ሰነድ ላይ «ያለውን አጫራች የተሻለ አማራጭ ካገኘ በጨረታው አይገደደም» የሚለውን አንቀጽ  በመጠቀም  ነው በጫራታ ካሸነፈው ድርጅት የተሻለ ዋጋ እሰጣለው ብለህ ደብዳቤ አስገባና ጫራታውን አንተ እንዳሸነፍክ እናደርጋለን  ብለውኝ  ነው ቦታውን ያገኘሁት  አለኝ፡፡

   አሁን የቤተክርስቲያኗ አስተዳደር ቢሮ ውስጥ  ነው ያለነው፡፡  ባለጉዳዬ  አባታችን  ብሎ  ወገቡን አጎንብሶ  የቄሱ ጉልበት ሥር  እንደመውደቅ ብሎ የእሳቸውን  ቡራኬ ሲቀበል  ይሄ ሰው ቅድም ሲያማቸው አልነበር እንዴ ብዬ  አይ ኢትዮጵያ እያልኩ ከራሴ ጋር ስነጋገር እኔንም ጎሸመኝና ውስጤን እየከነከነው ሳልወድ በግድ በደመነፍስ አባታችን አልኩ እየተደነባበርኩ፡፡ ከተወሰነ መነጋገር በኃለ ውል እንዋዋላለን  ብሎኝ ያመጣኝ  ርዕሱ ተቀይሮ ሌላ ጉዳይ ፊቴ አቀረቡልኝ  ቀና ብዬ ያመጣኝን  ሰው አየሁት፡፡  ችገር የለም ቀጥል የሚል ምልክት አሳየኝ፡፡ ገረመኝና  የሚያወሩትን  ዝም ብዬ  እሰማ  ጀመር፡፡ አሰተዳደሩ እንደከፋኝ ገብቷቸው ይሁን ወይ ደግሞ ውጥረቱን በማብረድ መቀራረብ ለመፍጠር ሥምህ ማን  ነው ያልከኝ… የሚገርም ሰም ነው ያለህ በማለት በስሜ ላይ መጽሐፈ ቅዱሳዊ  ትንታኔ ይሰጡ  ጀመር፡፡ እኔ ብዙ አልተመቸኝም፡፡ እዚህ ቢሮ ከመግባቴ በፊት የሰማሁት ነገር ውስጤን  ረብረሾታል፡፡  በሆዴ  በእኛ ሃይማኖት ነው አይደል እነዚህ ወንበር ላይ  ቁጭ ብለው  ቁማር የሚጫወቱት  አልኩኝ፡፡  አሁን  ማን እኝህን ሰው  በሌላ  ይጠረጥራል  አልኩ፡፡       

     ቢሮው  ውስጥ  4 ሰዎች ነን ያለነው፡፡ አባታችን፣ አንድ  ወጣት ሰው(ኋላ ላይ የሂሳብ  ባለሞያ ነው፣ ጉዳዩን የሚሸምነው  እሱ ነው ብሎ ባለጉዳዬ ነግሮኛል)፣ ባለጉደዬ እና  እኔ፡፡ ለእኔ ለማሳየት ፋይል ይዞ የመጣው ሰው ገብቶ ፋይሉን ከአስተዳደሩ አባታችን ጠረጴዛ ፊት ላይ  ሲዘረግፍው የባሰ ተናደድኩና ድንገት ድምጼን  ከፍ አድርጌ እኔ ከመጣሁበት  ጉዳይ  ሌላ ጉዳይ  አይመለከተኝም የእኔ  የህግ  አማካሪነት  ለእርሱ ድርጅት  ነው(ለባለጉዳዬ ማለቴ ነው)  የእናንተ ደግሞ ሌላ ድርጅት ነው፡፡  በራሳችሁ ጠበቃ ልትቀጥሩ ወይም ከበላያችሁ የእናንተ ቤተስኪያን የህግ አገልግሎትን በማናገር ለጉዳያችሁ መፍትሔ ማግኘት ትችላላችሁ  አልኩኝ፡፡ 
   እነ አባታችን ቀደም ሲል ከቤተክርስቲያኗ ጋር ለአለፉት ዓመታት በኪራይ ሲሰራ  የነበረው  የኮንስትራክሽን ማቴሪያል አምራች ድርጅት ባለቤት  የተከራየውንና  ባለጉዳዬ ያሸነፈበትን ሰፊ ቦታ ማሽኖች ስላሉኝ ለመንቀል ጊዜ ስጡኝ  በማለት አልወጣም ብሎኛል ምን እናድርግ በሚል ነው፡፡ ከድርጅቱ ባለቤት ጋር የተደረገውን ውልና የተለዋወጡትን  ደብዳቤዎችና  ሰነዶች ነው ያቀረቡልኝ፡፡ (ኋላ ላይ ከኮንስትራክሽን ማቴሪያል ድርጅቱ ባለቤት ጋር ስንገናኝ በእርሱ ህጋዊ ሆነ ህጋዊ ባልሆነ እንቅስቃሴው በሚረባ በማይረባ ነገር ከፍተኛ የሆነ ገንዝብ በየወቅቱ  እየሰጠ ያስለመደ  መሆኑን ተረድቻለው፡፡)
  ግዴለም እኛም እናንተም ማለት እኮ አንድ ነን፡፡ እንደ ሌላ ሰው አትየን፣ የቤተሰብ  ሥራ እኮ ነው፣ የጋራ ጉዳያችን እኮ ነው፣ ደሞ ቤተክርስቲያኗ የአንተም ጭምር ናት ከፈጣሪ ታገኘዋልህ…. በሚል የቃላት መኣት ወረወሩብኝ መልስ ለመስጠት እንኳን ጊዜ አሳጡኝ፡፡ አሁን ከእነዚህ ጋር እሰጣ ገባ ውስጥ መግባት ጠቃሚ እንዳልሆነህ  ተረዳሁና ከወንበሬ ተነስቼ  ያመጡት ዶክመንቶች እያገላበጥኩ ማየት ጀመርኩ፡፡ ምን ያህል አሻጥር በቤተክርስቲያኗ ላይ  እንደሚሰራ ተገንዝቤ ንዴቴን በማፈን አንዳንድ ጥያቄ መጠየቅ  ጀመርኩ፡፡ ይህንን ሰውዬ ማን  ነው ይህን ያህል ሠፊ ቦታ ያከራየው?(ከቤተክርስቲያና ጋር ያደረገው ውል ስላላየሁ)እኛ  ያከራየነው  ሌላ ድርጅት  ነው? የማከራየት ስልጣን  ማን  ሰጠው? እስቲ የማከራየት መብት እንዳለው የሚያሳይ ስምምነት ያሳዩኝ አልኩ፡፡ ፈገግ ብለው በምፅት እያዩኝ ነው፡፡ ብቻ  በርካታ ጥያቄዎች ማንሳት እየተቻለኝ  ማንም  ሰው ሊመልስልኝ እንዳለቻለ ስረዳ ጥያቄዎቼን ለጊዜው  ውጬ ማወቅ የግድ አለብኝ ያልኩትን ብቻ ጠየኩ፡፡ አባታችን እባክህ ልጄ አሁን የምትጠይቀው  ሁሉ እኔ ከመሾሜ በፊት የተደረገውን ነው፡፡ እኔ እኮ በቅርብ ነው እዚህ ቤ/ክርስቲያን የተመደብኩት አጨመላልቀውታል፣ መላም የለው አሉኝ፡፡ (እሳቸው በተራቸው ለማጨማለቅ የእጃቸውን እጅጌ ሰብስበው እንደተነሱ ያልታወቀባቸው በሚመስል ሁኔታ፤ በሆዴ  ተጫወቱባት ይህችን ቤተክርስቲያን አልኩ፡፡) ሁኔታው ስላላማረኝ አንድ ሀሳብ መጣልኝና እንዲህ በሚል መለስኩላቸው፡፡ ይህንን ጉዳይ ቢሮዬ በእርጋታ ቁጭ ብዬ ነው ማጥናት ያለብኝ፡፡ የሰነዶቹን  ኮፒ ግን እፈልጋለው አልኳቸውና የሰነዶቹን  ኮፒ እጄ  አሰገባው፡፡
   አዋቂ ሰውና አዋላጅ ያየውን በሙሉ አይናገርም የሚለውን አባባል ለጊዜው በመርህ ደረጃ ወስጄ  ይህንን ጉዳይ ለማሳያ  ከገለጽኩ  ወደ ተነሰሁበት ጹህፍ ልመለስ፡፡


 የቤተክርስቲን ኪራይ ሰበብ  ሙስናዎች

   በቅርብ ጊዜ ሊቀ ጳጳሳት የሆኑት አቡነ ማቲያስ  በተሾሙበት ሳምንታት የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲን ውስጥ ሙስና እናዳስቸገረ በመገናኛ ብዙሃን ሲናገሩ ሰምተን እኝህ ሰው ቤተስኪያኗ ውስጥ ለማገልግል ምድባ እንኳን ቤተሰባዊነት ወይም እጅ መነሻ የሚጠበቅባቸው የሃይማኖት አባቶችን ቢያንስ ቢያንስ እጅ መንሻውንና የቤተሰብ ምደባውነ ያስቀራሉ ይህንን  ችግር መንግለው ያወጣሉ የሚል በምእመናኑ እምነት ተጥሎ ነበር፡፡ መሬት ላይ ወድቆ የምናየው ግን ከጠበቅነው ውጪ ነው፡፡
    የቤተክርስቲያን አጥር ተንዶ ወይም ተቆርሶ የሚሰሩት ህንጻዎች ላይ ሳይቀር  የራስ  ኪስ ውስጥ የሚገባ ገንዘብ ይሰራባቸዋል፡፡ አንድ ጤነኛ ሆነ ጤነኛ ባልሆነ መልኩ የቤተክርስቲያንን ንብረት የተከራየ ግለሰብ ወይ ድርጅት ከቤተክርስቲያኗ አስተዳደር ጋር የጥቅም  ግንኙነት ከሌለው በአንድ አንድ ቤተክርስቲያን ድርጅቱ በተከራየው ቤት የመቀጠሉ እድል አናሳ ነው፡፡ መነሻ የሚያደረገው ምንአልባት ቤተስኪያኗ ውል ልታቋርጥበት ትችላላች ተብሎ በኪራይ ውሉ ላይ የተጠቀሰውን አንቀጽ በመጠቀም ሊሆን ይችላል፡፡ ምንአልባት ቤተክርስቲያና ለራሷ አገልግሎት የኪራይ ቤቱን ስትፈልግ ተከራዩን ልታስወጣ ትችላለች የሚልና መሰል ለመደራደሪያ የሚያመቹ  አንቀጾችን በመጠቀም ነው፡፡ እኔ እጄ በገቡ ውሎቹ ላይ እንዳየወት እንኳን ውሎቹ በአብዛኛው የእኩሌታ(win win negotiation) ደርድር ያለበት ሳይሆን አንደኛው ወገን ባለ ከፍተኛ ተደራዳሪነት(win lose negotiation)ያለበት መሆኑን መገንዘብ ችያለው፡፡  ወደ የህግ መሰረታዊ የውል ጉዳዮች ሳንገባ ቤተክርስቲያኗ ለራሷ የተሻለ አገልግሎት ለምስጠት በመፈለጋ ከተከራዩ ብትወስድ ምንአልባት ውልን መሰረት አድርጎ ስለሆነ እንዲሁም ቤተክርስቲያና የህዝብ ናት የበለጠ መጠቀም አለባት ትክክል ነው ልንል እንችላለን፡፡ ይሁንና ይህ ለቤተክርስቲያና አገልግሎት ተብሎ የሚሰጠው ምክንያት በእርግጥ ቤተክርስቲያና  የተሸለ ማከራየት ይጋበታል ፍትሃዊ አይደለም ኪራዩ ተብሎ ሳይሆን ከተከራዩ የሆነ መጠን ያለው ገንዘብ አከራዮቹ ለመቀበል ወይም ሌላ የተሻለ ገንዘብ የሚከፍልና ቀደም ብሎ ተከራይቶ የነበረውን ቤት ወይም ቦታ የሚፈልግ ነጋዴ መጥቶ ሊሆን ይችላል፡፡ በነገራችን ላይ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የቤተክርስቲያን አጥር ዙሪያ አከራዮች የኪራይ ብሩ ከፍ እንዲል ወይም ከፍ ባለ ገንዘብ እንዲከራይ መፈለግ ሳይሆን ዓላማቸው ኪሳቸው የሚገባውን ገንዘብ መጠን ማሳደግ ነው፡፡ እነሱ ለቤተክርስቲያና ከፍተኛ የኪራይ ዋጋ ህጋዊ በሆነ መንገድ የሚያስገባ ተከራይ እምብዛም አይመስጣቸውም፡፡ የቤተክርስቲያኗን መደበኛ ገቢ የሚንያስበት የማያስነቃ (የማየስነቃ ሲባል በጣም የማይታወቅ በጥንቃቄ የተሰራ ማለት ሳይሆን ትንሽ ብቻ ፊት ለፊት የማይታይ መሆኑ እንጂ አንድ ሁለት ጥያቄ ወይም ሰነድ ቢገላበጥ የሚደረስበት ሴራ ቢሆንም ችግር የለባቸውም) መንገድ ከተገኘ ስለ ቤተክርስቲያና ገቢ ትተው ኪሳቸው የሚገባ የደለበ ገንዘብ ላይ ነው ትኩረታቸው፡፡ ኪሳቸው የሚገባ ገንዘብ (አንዳንዴ ከኪራዩ ክፍያ በፐርሰንትም ይጠይቃሉ) ከተገኘ የክፍያ ጊዜ ሊያስረዝሙ፣ የእፎይታ ጊዜ (Grace period) ሁሉ ይሰጣሉ፡፡ በውሉ የተጠቀሰው አስገዳጅ አንቀፆች ሁሉ ዋጋ ቢስ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ የሚዋዋሉት የኪራይ ውል በውልና ማስረጃ ጽ/ቤት የተመዘገበ ላይሆን ይችላል፡፡ እየተሠራ ያለ ያላለቀ ህንጻ ሁሉ ቢሆን እንኳን ጥቅም የሚያስገኝ ከሆነ በቁሙ በጀርባ ስምምነት ተደርጎበት የይምሰል ጨረታ ይወጣለታል፡፡

           መእመናኑን እንደ አርጩሜ መጠቀም

  እነደዚህው በቤተክርስቲያን ኪራይና ተከራይ ጉዳይ የተገናኝን ተከራይ ነጋዴ የገጠመውን ሲገልጽልኝ እነዚህ በኪራይ ስም የሚቆምሩ የቤተስኪያን ሰዎች ከተዋዋሉት ውል ውጪ እርምጃ ቢወስዱብህም በህግ እጠይቃለው ብትል የባሰ ቀውስ (chaos)ውስጥ ልትገባ ትችላለህ፡፡ እንዴት በማለት ጥያቄዬን አስከተልኩ፡፡ የአከባባቢውን መእመናን የተለያየ ስም ለአንተ እየሰጡክ፣ የቤተክርስቲያን ጠላት እንደሆንክ አድርገው ሆ! ብለው እንዲነሱ መእመናኑ በተሰባሰበበት አጋጣሚ ይሰብካሉ፡፡ አንድ ጊዜ እኔ እንደዚሁ ገጥሞች በስንት በመከራ በጸጥታ ኃይሎች ነው ንብረቴን ይዤ አንኳን ላወጣ የቻልኩት አለኝ፡፡

ሲጠቃለል

  የማቴዎስ ወንጌል ምዕራብ 21 ቁ. 12 ክርስቶስ በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚሸቅጡትን ቤቴ የጸሎት ቤት ናት እናንተ የወንበዴ ዋሻ  አደረጋችሁት በማለት የሻጮችን ወንበር የገለጠው  ለቤተክርስቲን አጥር ዙሪያ የንግድ ማዕከልነት አይሰራም ሚስጥሩ ሌላ ነው ብንባል እንኳን(ይህ ፀሐፊ ቤተክርሰቲያን አጥር ዙሪያ ንግድ በጭራሽ ተገቢ አይደለም፡፡ ክርስቶስም ሲያወግዘው የነበረ ነው ንግድና የአምልኮ ስፍራ ሊጎራበቱ አይችሉም ባይ ነው፡፡) የሚነገደው  ነገር የቤተክርስቲያንን ሰላምና የተረጋጋ መንፈስ የሚያውክ ባይሆን፡፡ ምክንያቱም  ከቤተክርስቲያን ዓላማ ጋር የሚቀራረቡ የንግድ ተግባራት ወይም ግብረሰናይ እንቅስቃሴዎች የሚደረግባቸው ቤቶችን ማከራየት ስለሚቻል፡፡ ቤተክርስቲያን የመልካም ስነምግባር ማስተማሪያና ማነፂያ ተቋም ናት እንጂ የተበላሸ ስነምግባር በመንሰፈሳዊ ህይወት ጥላ ሥር ከዓላማዊ ሰዎች ባልተናነናሰ የምናይባታ መሆን የለባትም፡፡ በልብሰ ተክህኖ ተሸልመው የቤተክርስቲያናን ሥም የሚያጠፉ ሙሰኛ ካህናት ከቤተክርስቲያን ወጥተው ወደ ምድባቸው ቢሄዱ፡፡ ቤተክርስቲያን የመንፈሳዊ ህይወትን፣  የእግዛብሔርን መንገድ የምትሰብክ፣ የምታሳይ በመሆኗ የክፉ ነጋዴ አይነት ተግባር ቀዳዳ እየፈለጉ በተከራዮች ላይ ጫና በመፍጠር ይህችን ቤተክርስቲያን መእመናኑ እንዲያማርር እንዲጠላት በማድረግ እንደቤተክርስቲያን ጠላት ባንሰራ፡፡ ከሁሉም  በላይ ቤተክርስቲያናችንን  በውስጥና በውጭ ነጋዴዎች ባታስወርሩብን፡፡
                                    በዝራው አሻግሬ

ዓርብ 23 ጃንዋሪ 2015

አርቲስት በህዝብ መዳፍ ላይ እንዳለ እንቁላል.........!



  አርቲስት በህዝብ መዳፍ ላይ እንዳለ እንቁላል ነው!
    
  አርቲስት ማለት ተዋናይ፣ዘፋኝ፣ሙዚቀኛ፣ ኮመዲያን፣ዳንሰኛ፣ሠዓሊ፣ ቀራጺ  ወዘተ..  ሊባል ይችላል ብንል የተለያዩ  ጹህፎች (literatures)  ላይ በተለያየ  አገላለጽ  መጠቀሳቸው ዋቢ ማድረግ ይችላል፡፡ ይሁንና አርቲሰት የሚለው ቃል የእንግሊዘኛው ARTIST ከሚለው ቃል የተወሰደ  ስለመሆኑ  ግልጽ ነው፡፡ አርቲስት የአማርኛ አቻ ትርጉም ጠፍቶት ነው የእንግሊዘኛውን Artist የሚል ቃል የወረስነው ጥበብ፣ ጥበበኛ፣ የኪነጥበብ ሰው ልንል አንችልም ይሆን?! አሁን በህብረተሰቡ ውስጥ ሆነ በተለያየ የመገናኛ ብዙሃን አርቲሰት እከሌ፣ አርቲስት እከሊት በማለት የእንግሊዘኛውን ቃል ለአበሻ የኪነጥበብ ሰዎች እንደማዕረግ  ተሰጥቶአቸው እንሰማለን፣አናነባለን እንመለከታለንም፡፡

 የአንግሊዘኛ አማርኛ መዝገበ ቃላት Art የሚለውን  የእንግሊዘኛ ቃል ጥበብ፣ ብልሃት፣ ዘዴ በማለት ሲገልጸው artist  የሚለውን  ቃል  ደግሞ ሰዓሊ፣ የኪነጥበብ ሰው በሚል ትርጉም ይሠጠዋል፡፡  የኢትየጵያ ቃንቃዎችና ጥናትምርምር ማዕከል በ1993 ዓ.ም ባዘጋጀው መካከለኛ  ዘመናዊ መዝገበ ቃላት በሚል የሚመደበው መዝገበቃላት ላይ «ጥበብ» ለሚለው ቃል  ብልሃት፣ ዕውቀት፣ ዘዴ በሚል ፍቺ ስጥቶ የዚህ ቃል የሥም ገላጭ ቃል የሆነውን «ጥበበኛ» የሚል ቃል አዋቂ፣ ብልሃተኛ፣ ዘዴ የሚያውቅ በማለት ይፈተዋል፡፡
  አርቲስት/Artist፤ አርት/art ከሚለው የእንግሊዘኛ ቃል የተወሰደ መሆኑን የተለያየ የእንግሊዘኛ መዝገበ ቃላቶች ያሳያሉ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ የህግ ቃላቶችን ወይም ሀረጎችን በመተርጎም ከፍተኛ ተቀባይነት ያለው ብላክ ሎው (Black law) የህግ መዝገበ ቃላት እና በርካታ ሰው በማመሳከሪያ የሚጠቀመው ዊኪፒዲያ ኢንሳይክሎፒዲያ መዝገበ ቃላትን የጥበብ/አርት(Art) እና ጥበበኛ/አርቲሰት(Artist) ትርጉምን  እንዴት እንደሚገልጹት  እንይ፡-  
      
               1. Black law Dictionary፡-
          Art
1.       The methodical application of knowledge or skill in creating something. .
2.       An occupation or business that requires skill; a craft.
3.        Pat­ents. A process or method that produces a bene­ficial physical effect.
በሆነ ነገር በመፍጠር  ሂደት ላይ ዕውቀትንና ችሎታን ማስፈጸሚያ ዘዴ፣ ችሎታ የሚጠይቅ የሞያ  ወይም  የንግድ አይነት/ የእጅ ሞያ፣ የፈጠራ ባለቤትነት መብት፤  ጠቃሚነት ያለው ግዙፍ ውጤት የሚሰጥ ሂደት ወይም ዘዴ፤
                 2.  Wikipedia, the free encyclopedia
Art   is a diverse range of human activities and the products of those activities. In their most general form these activities include the production of works of art, the criticism of art, the study of the history of art, and the aesthetic dissemination of art. 
  ዊኪፒዲያ  ፍሪ ኢኒሳይክሎፒዲያ መዝገበ ቃላት፡-
   ጥበብ  ማለት መጠነ ሠፊ የሆነ የተለያዩ  የሰው ልጅ ተግባርና የተግባሩ ውጤት፡፡ በአጠቃላይ መልኩ ሲገለጽ ይህ  ተግባር  የተግባሩን  የሥራ ውጤት፣  ተግባሩን  መተቸት፣ የተግባሩን የኃላ ታሪክ ማጥናት እና ተግባሩን በማራኪ ሁኔታ ማሰራጨትን ያካትታል፡፡
     ጥበበኛ/አርቲሰት/Artist የሚለውን ቃል ደግሞ ዊኪፒዲያ ፍሪ ኢኒሳይክሎፒዲያ መዝገበ ቃላት እንደሚከተለው ገልጾታል፡፡
An artist is a person engaged in one or more of any of a broad spectrum of activities related to creating art, practicing the arts, and/or demonstrating an art. The common usage in both everyday speech and academic discourse is a practitioner in the visual arts only. The term is often used in the entertainment business, especially in a business context, for musicians and other performers (less often for actors).
    ጥበብን መፍጠር ፣ተግባራዊ ከማድረግ እና ሠርቶ ከማሳየት ጋር በተያዘ ከአንድ በላይ በሆኑ  በእነዚህ ሰፊ ህበረቀለም ባላቸው ተግባሮች የተሰማራ፡፡  ይህ ቃል በዕለት ዕለት ንግግራችንና ትምህርታዊ ገለጻዎች ላይ ለሥነ ጥበብ ባለሞያ ብቻ እንደሚያገለግል ተደርጎ በተለምዶ ይወሰዳል፡፡ ቃሉ ዘውትር  ጥቅም ላይ የሚውለው ለመዝናኛ ሥራዎች፣ በተለይ ለሙዚቀኞችና ሌለሎች ከዋኞች ነው( እምብዛም ለተዋናዮች መጠሪያነት አያገለግልም)፡፡ 
 አርት(Art)እና አርቲስትን(Artist)መደበኛ የማይክሮ ሶፍት(Microsoft Word) እና  ዊኪሸነሪ(wiktionary) መዝገበ ቃላት ቀለል ባለ ሁኔታና በተለመደ መልኩ  እንዲህ ይገልፁታል፡፡
      Microsoft Word
   Art: - talent, ability, drawing, skill, fine art, painting, sculpture, knack etc. /ተስጥኦ፣ችሎታ፣ ሥዕል፣ ዕውቀት ፣ሥነጥበብ፣ ቅብ፣ቅረጻ ቅርጽ ፣ቅልጥፍና ወዘተ…..
  Artist: - performer, dancer, musician, Actor, comedian, singer etc… /ከዋኝ፣ ዳንሰኛ፣ ሙዚቀኛ፣ ተዋናይ፣ ዘፋኝ ወዘተ….
              Wiktionary 
  1. A person who creates art.
  2. A person who creates art as an occupation.
  3. A person who is skilled at some activity.
     ጥበብን የፈጠረ ሰው፣ ጥበብን  በመጠበብ ሥራው ያደረገ፣  በሆነ ተግባር ላይ ባለዕውቀት የሆነ፡፡ የሚል ትርጉም ይሰጣል፡፡
     መነሻው  በመጠኑ ይህ ከሆነ  በሌላ መልኩ ደግሙ በእርግጥ አንድ ሰው አርቲሰት ነው ልንለው የምንችለው ምን አይነት የአርት ወይም የጥበብ  ሥራ ሲሰራ ነው?! አንድ ድራማ  ወይም አንድ ዜማ የተጫወተ  ሰው አርቲስት ነው ሊባል ይችል ይሆን?! የሠራው ሥራ ጥራቱ፣ ጥልቀቱ፣ ማህበራዊ ኢኮነሚያዊና ፖለቲካዊ  ጠቀሜታው ወይ ፋይዳው፣ እርካሽነቱ፣ ድሪቶ መሆኑ፣ የተሰረቀ ወይም የተገለበጠ(plagiarism) መሆኑ፣አዝናኝነቱ፣ ቢዚነስ ተኮርነቱ፣አሸር በአሸርነቱ፣አሸርጋጅነቱ፣ የፕሮፓጋዳ መንፈስ ያለው መሆኑ፣ በልታይ ባይነት የተሰራ መሆኑ አርቲስት የሚለውን ሥም አይገባውም፤ ይገባዋል የሚለውን የሚመልስ ነውን?! የሚለው ጥያቄ ብዙ ሊያነጋር የሚችልና ጥናት የሚያስፈልገው ጉዳይ ነው፡፡
    አሁን ባለው ሁኔታ አርቲስትነት ከላይ ከገለጽናቸው ተግባሮች አንዷን የሰራ እኔ አርቲስት ነኝ በሚለው ወይም የእንግሊዘኛው Arty የሚለው የአንግሊዘኛ አማርኛ መዝገበ ቃላት የሥነ ጥበብ ሰው ነኝ ባይ በሚል የሚተረጉመው አይነት እና የተለያዩ የመገናኛ ብዙሃኖች በእነርሱ በጎ ፍቃድ አርቲስት እከሌ በሚል የጠሩት ወይም ህዝቡ በራሱ መንገድ አርቲሰት ብሎ በሰጠው ስያሜ ነው አርቲስትነት፡፡ 
   የአገራችን የቅጅና ተዛማች መብቶች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 410/96  አንድ ሰው በአህምሮ ያሰበውን በወረቀት ወይም ግዙፍ በሆነ ነገር ላይ በማሳረፍ ከምናብነት ወደ ግዙፍነት  ሲቀይረው የፈጠራ መብት ጥበቃ አንደሚደረግለት  በአንቀጽ 6 ላይ ተገልጿል፡፡ ይህ ማለት  እንግዲህ  አንድ ህጻን ልጅ በወረቀት ላይ በደመነፍስ የጫጫረውን ምስል የሚመስል ነገር  ቢሆንም አዋጁ የቅጂ መብት ጥበቃ  አለው  ወይም ማንም ሰው ሊቀዳበት አይችልም እንደማለት ይወሰዳል፡፡ ምናልባት የሆነ ሥነ-ጥበባዊ ጉዳይ የፈጠረን  ግለሰብ አርቲስት የምንል ከሆነ በህጉ መሰረት ትርኪምረኪ ቢሆንም  ግለሰቡ ራሱ የሠራው ወጥ ሥራ  ከሆነ ፈጣሪ ነው ወይም አርቲስት ነው ልንል የሚያስችለን አንድ የአርቲስት ትርጉም ከዚህ  አንቀጽ ላይ  ልንመዝ እንችላለን፡፡
 በተመሳሳይ እዚህው አዋጅ ላይ  በአንቀጽ 19  ከዋኝ  የሚለውን  ቃል  አንዲህ በማለት  ይገልጸዋል፡፡
          ተዋናይ፣ ዘፋኝ፣ ዘማሪ፣ሙዚቀኛ፣ ተወዛዋዥ እና ሌላ ማንኛቸውንም የሚተውን፣ የሚያወጣ፣የሚጫወት፣የሚዘፍን የሚያዝናና ወይም በሌላ ማንኛቸውም አኳኋን የስነ ጹህፍና የኪነጥበብ ሥራ የሚከውን ግለሰብ ነው፤  ይለዋል፡፡
   ይህ ትርጉም ምንአልባት ከዋኝ ከሚለው ጋር አርቲስት የሚለውን አዛምደን ብንወስድ  በዚህ ጹህፍ በግቢያ ላይ ስለአርቲስት ዝርዝር ትርጉም ከተሰጠው ጋር  የሚመሳሰልና በተለምዶ ከምንጠቀምበት ማዕረግ ጋር በሚቀራረብ  መልኩ የተሰጠ የህግ ትርጉም ነው፡፡
  ዊኪሊ ፒዲያ ፍሪ ኢንሳክሊፒዲያ  አርቲስት የሚለውን ቃል ሲተረጉም  ደግሞ፡-
  “an artist is a person engaged in one or more of any of a broad spectrum of activities related to creating art, practicing the arts, and/or demonstrating an art.”  
ጥበብን መፍጠር ፣ተግባራዊ ከማድረግ እና ሠርቶ ከማሳየት ጋር በተያዘ ከአንድ በላይ በሆኑ  በእነዚህ ሰፊ ህበረቀለም ባላቸው ተግባሮች የተሰማራ በማለት  ከአንድ በላይ የአርት ሥራ ላይ መሳተፍ አርቲስት የሚለውን ማዕረግ ለማግኘት  መሟላት እንዳለበት ያሳያል፡፡  (የእንግሊዘኛ ጹህፎች አማርኛ ትርጉም የፀሐፊው ነው) 
   ለማንኛውም  በዚህ የማዕረግ ስም አጠራር ላይ ተገቢው ጥናት ተሰርቶ መግባቢያ የማዕረግ ቃል ላይ እስኪደረስ እኔም ለጊዜው ለዚህ ጹህፍ ዓላማ እንዲረዳኝ አርቲሰት እያልኩ  ጹህፌን እቀጥላለቀው፡፡       
   ለመግቢያ ያህል ስለ አርቲስት ማን ነው? ምን ማለት ነው? የሚለውን ሀሳብ መነሻ  ነገር ካስያዝኩ  ወደ ተነሳሁበት  በቅርብ  ጊዜ በሬድዮው በቴሌቪዥኑና በተለያየ መድረክ ያዙኝ ልቀቁኝ ስለሚሉት  ሠራዊት መራሽ አርቲስቶች  አንድ ዘገባን መሰረት ያደረገ ትዝብቴን  ወደ ማሰነበቡ ልግባ፡፡
   ከዚህ ቀደም በአንድ  ሁለት መጽሔት ላይ መንበር ናፋቂ ከያኒዎች በሚል  ርዕስ በአቋራጭ መበልጸጊያና መንበር ፍለጋን አልመው የሚሯሯጡ አካሄዳቸውን ምድብ፣ ምድብ በመስጠት ለአንባቢ ግንዛቤ ለመስጠት ሞክሬአለው ፡፡      
    በአሁኑ ሰዓት የተወሰነ የአሰላለፍ ለውጥ እየአየን ቢሆንም  ከህዝብ ማዶ ካለው ሰልፍ በሚገርም ሁኔታ በመመንጠቅ የህዝብ ጉያ ውስጥ  የገቡ፣ ሳይነካኩ እስከ መክሊታቸው  በጨዋነት፣ በክበር ያሉ፣ ከህዝብ  ጎን መቆም ወይም ሞት ያሉ ታዋቂ አርቲስቶች አሉ፡፡ በአንፃሩ በኪነጥበብ ሞያ ውስጥ ረጅም ዕድሜ አስቆጥረዋል የሚባሉ  ምደባቸውን ወደ ማዶ ያደረጉ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል አርቲስቶችም  ድምጽ ማጉያ ይዘው መፈከር ሲያሰሙ አስተውለናል፡፡ አንድ አርቲሰት በአንድ ወቅት የመንግስት ኃላፊዎቸ ጽፌ ያዘጋጀውትን ቲያትር የተለያየ ትርጉም ሰጥተው ለህዝብ እንዳይቀርብ አደረጉብኝ በማለት ብሶት ሲያሰማ የነበር በአሁን  ወቅት አሰላለፉን በመቀየር  በኪነጥበብ ስም  ወደ ሀብት ጉዞ ሰራዊት መር ተርታ መቀላቀሉ አይተናል፡፡ በቴሌቪዝን፣ በተለያዩ ምክንያት በሚዘጋጁ ዝግጅቶች ላይም እምቢ! እምቢ ላገሬ! ሲልም ታዝበናል፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ ሠራዊት መር አርቲሰቶች አይናቸውን አፍጥጠው ያዙኝ ልቀቁኝ ማለታቸው የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡  ስለመንበር ናፋቂ  አርቲስቶች ስናነሳ አርቲሰት ሠራዊት ፍቅሬ በአርቲሰት ማዕረግ ነጋዴ ከሆኑትና በተገኘው መድረኮች የአገሪቱ እጣ ፈንታ በእጃቸው  ከነበረው ከሟች ጠቅላይ ሚንስትር አጠገብ  ጎን ለጎን መቀመጥን ጨምሮ  በተለያዩ  መንግስት ሰራሽ መድረኮች ላይ ፊጢጥ ከሚሉት የጊዜው አርቲስት ነጋዴዎች ዋኖቹ ተርታ ልናነሳው የምንችለው ግለሰብ ነው፡፡ ምናልባትም  አሁን እዩኝ እዩኝ ሲሉ የምናያቸው አርቲስቶች የሠራዊት ፍቅሬን  በአርቲስትነት መነሻና ከገዢው መንግሰት ጎን የመቆሙ ምክንያት የአርቲሰቱ ባለሀብትነትን ታሳቢ በማድረግ ወደ ልማታዊ ባለሀብትነት ጎራ  መቀላቀልን የዕቅዳቸው ግብ በማድረግ የሚራወጡ ናቸው ማለት ይቻላል፡፡  ወደ ዘገባው ልግባ፡፡  
   በ19/4/2007 ዓ.ም  የወጣው የሪፖርተር ጋዜጣ የፊት ለፊት ገጽ ላይ «ኢሕአዴግ የታጋዮችን ዓላማ በሚያረክሱ ሹማምንቶቹ ላይ ዕርምጃ እንዲወስድ ጥያቄ ቀረበለት» የሚል  የዜና ዘገባ አይቼ ውስጡን ገልጬ  ሳይ  እነኚህ የህወሓት የተመሰረተበትን 40ኛ ዓመት ሊያከብሩ የሄዱት ባለ ራዕይ አርቲስቶች ያቀረቡት ጥያቄ መሆኑን ስረዳ  ፈገግ አሰኘኝ፡፡ ምን ማለት  ነው ብዬ  ራሴን መልሼ ጠየኩት፡፡ የዜናው የመጀመሪያ አንቀጽ እንደሚከተለው ይነበባል፡፡
#የሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) 40ኛ የልደት ዓመት አስመልክቶ፣ ድርጅቱ የተመሠረተበትን በረሃና በትጥቅ ትግሉ ወቅት እንደ ጽሕፈት ቤት ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት ታሪካዊ ዋሻዎች፣ እንዲሁም የደርግ 604ኛ ኮር የተደመሰሰበት የሽረ ጦርነት የጎበኙ ታዋቂ የአገሪቱ አርቲስቶች ያዩት ነገር ከዚህ በፊት ከሰሙትና ካነበቡት የተለየ መሆኑን ገልጸው፣ በዚህ ብዙ ውጣ ውረድና ከፍተኛ መስዋዕትነት የተገኘ ድል አሁን በኢሕአዴግ ሹማምንቶች እየረከሰ በመሆኑ ዕርምጃ እንዲወሰድ ጠየቁ፡፡; 
    ምን ማለት ነው ከአውራ ሹማሙንቶች ጋር እየተንደላቀቁ ስለ ሹማሙንት ማውራት?   ሌላ የኢህዴግ ልደትን  ከእነእርሱ ጋር እጅ ለእጅ ተያይዘው ያላከበሩ ሹማምንቶችን ማለት ይሆን?  መንገድ ላይ ተቀላቅለው ሹማምንት የሆኑትን  ነውን?  በትጥቅ ትግል ያለነበሩ አሁን ሹማምነት የሆኑትን ማለት ይሆን?  በሀቀኛ የጭቆና ስሜት ተነስተው በየበረሃው የተሰዉትን  ታጋዮች  ዓላማ  ወርውረው ጥለው  ዘመናዊ ጨቋኝ  የሆኑትን ይሆን? በሞት ሽረት ትግል ወቅት  በሴት ታጋዮች  ጀርባ ጥይት ሲከለሉ ነበሩ የተባሉት ይሆን?   እንማንን ይሆኑ እነዚህ ሹማሙንቶች? 
    ጎናቸው የተቀመጡትና የቆመት  እየተሸከረከሩ  አብረዋቸው ፎቶ የሚነሱት ሹማምንቶች  የኢህዴግ ሹማምነቶች አይደሉም ይሆን?!  ወይስ እርምጃ ወሳጆቹ  ጋር  ሆነው  ነው  የእርምጃ ይወሰድ ጥያቄ የሚያነሱት?!
     እረከሰ ማለት  ምን ማለት ነው?!
 ምክንያት እየፈጠሩ በህዝብ ገንዘብ መጨፈር፣ መዝናናት፣  ከሆቴል ሆቴል  እያማረጡ መጠጣት መብላት ነው? ስልጣንን መከታ  በማድረግ የህዝብ ገንዘብ መዝረፍ  ነው? ምክንያት እየፈጠሩ በቡድን  እየተከፋፈሉ የግዙፍ ካንፓኒ ባለቤት መሆን ነው? በሀገሪቱ ከሚገኙ ታላላቅ ኩባንያዎች ውስጥ ባለድርሻ መሆን  ነው?  ደሃውን ህዝብ ከቡና በጀበና እያፈላህ ከምትሸጠው የመንግስት ግብር ክፈል በሎ በማስጨነቅ በካንፓኒያአቸው  የንግድ እንቅስቃሴ ለመንግስት ግብር መግባት ያለበትን በቢሊዮን የሚቆጠር የህዝብ ገንዘብ  ሎሌዎቻቸአቸውን አላያችሁም ማለት ነው በማለት አይን በማሰጨፈን  በነጻ በመነገድ በሀበት መንበሽበሽ ነው?!
ዘገባውን   እያነበብኩ  በውስጤ የተፈጠሩትን  እንዚህ ጥያቄዎችን  አዝዬ  ወደ ታች ስወርድ   እንዲህ የሚል   ጹህፍ አነበብኩ፡፡
‹‹ይኼን የመሰለ ከባድ መስዋዕትነት የተከፈለበት መሆኑን እስከዛሬ አላውቅም ነበር፡፡ ነገር ግን ይህንን የታጋዮች ዓላማ የሚያረክስ ሥራ እየተሠራ ነው፡፡ እናንተን የማይመስሉ ባለሥልጣናት ሾማችሁብናል፡፡ ሕዝቡን ከታች እስከ ላይ እያማረሩ ነው፡፡ ትናንት የደማችሁለት ቅዱስ ዓላማ ዛሬ እየተበላሸና እየረከሰ ነው፡፡ አርሟቸው፡፡ እኛም ጦር ይዘን ከጎናችሁ እንቆማለን፤›› የሚለው ንግግራቸው በጉብኝቱ ተሳታፊዎች ከፍተኛ ጭብጨባ የታጀበ ነበር፡፡ ‹‹እናንተም ላሳያችሁ ፍቅርና ትህትናችሁ እግዚአብሔር ዋጋችሁን ይክፈላችሁ፤›› ሲሉ አስተያየታቸውን አጠናቀዋል፡፡
  ይህ  አንቀጽ  ቀደም ብዬ ያነሳዋቸውን ጥያቄዎችን የመለሰልኝ ቢሆንም ሌላ ጥያቄ እንዳነሳና  አቤት ውሸት!!  አቤት ቅጥፈት!  አቤት ጥምጠማ! አቤት  ማሸርገድ! አቤት ህሊና! ብዬ ጨንቅላቴን እንድይዝ ነው ያደረገኝ፡፡  እስቲ  አርቲስቶቹ የሰነዘሩትን  የመፈክር ሀረጎችን እየመዘዝን  እንገማገም፡፡
   ይህን የመሰለ ከባድ መስዋትነት የተከፈለበት መሆኑን እስከ ዛሬ አላውቅም ነበር!
   ለአለፉት 23 ዓመታት ኢህአዴግ ደርግን ያንበረከክንበት ቀን ግንቦት 20 ብሶት የወለደው…. ለህዝብ ጥቅም ተቆጣጥሮታል ሲል ይህ አስተያየት ሰጪ የጦርነቱን ፊልም በቴሌቪዥን ወይ በቪድዮ ወይ በሬድዮ አላየሁም ወይ አልሰማሁም እያለ ነው ማለት ነው፡፡ ወይ ደግሞ እየጠመጠመ ነው፡፡
 እናንተን የማይመስሉ ባለሥልጣናት ሾማችሁብናል!!
  በዚህ ሀረግ መስዋዕቱን አርካሾቹ  ቢያንስ ቢያንስ አበረዋቸው ያሉት  ሹማምንቶች አለመሆናቸውንና ታግለው ያልመጡ ሹማምንቶች መሆናቸውን  አረጋግጠዋል፡፡  እንደ እናንተ ምርጥ መሪ ያልሆኑ፣ እንደ እናንተ በስማቸው  ግዙፍ ካንፓኒ የሌላቸው፣ እንደ እናንተ ዲሞክራሲያዊ መብት የሚያከብሩ፣ እንደ እናንተ የማያሳድዱ፣ እንደ እናንተ ድንጋይ ለያዘ ጥይት የማይተኩሱ፣ እንደ እናንተ ሰማይ ጠቀስ ፎቅ የሌላቸው ፣እንደ እናንተ  ስንት ቁርጠኛ ታጋይ መስዋትነት የከፈለበት ድል የገባቸው፣ እንደ እናንተ የሴቶችን መብት የሚያከብሩ፣ እንደ እናንተ የማያዋክቡ፣ እንደ እናንተ  በነፃነት በህዝብ መሃል የሚሄዱ፣ እንደ እናንተ በሆድ ሰው የማይደልሉ፣ እንደ እናንተ  ሴራ ያማይጠነስሱ የማያስፈራሩ፣ እንደ እናንተ ዜጋውን የማያሰቃዩ   ወዘተ….አይደሉም  የሚሉ ይመስላሉ አርቲስቶቻችን፡፡ 
 ይሁንና በኢህአዴግ መዋቅር ውስጥ እነሱን ያልመሰለ  ከእነእርሱ ጋር የሚቀጥል ስላለመሆኑ ፀሃይ የሞቀው እውነታ መሆኑን ያላወቁ  በመምሰል  ሲጠመጠሙ ያሳየናል፡፡  ኢህአዴጎች አንድ መጽሀፍ እንደ አነበቡ ሰዎች  አይነት አነድ  መሆናቸውን  ነብሳቸውን ይማረውና  የቀድሞ  ጠቅላይ ሚኒስትርና የኢአህዴግ ሊቃመንበር በአንድ ወቅት  በፓርላማ ላይ  ነገርውን ነበር፡፡  
ሕዝቡን ከታች እስከ ላይ እያማረሩ ነው፡፡ ትናንት የደማችሁለት ቅዱስ ዓላማ ዛሬ እየተበላሸና እየረከሰ ነው፡፡ አርሟቸው፡፡ እኛም ጦር ይዘን ከጎናችሁ እንቆማለን፤››
 በዚህ ዓረፍተ ነገር ደግሞ የእዝቡ ምሬት ውስጣቸው የገባ መሆኑን ሊነግሩን ይሞክራሉ፡፡ ድንቄም  ለህዝብ ተቆርቃሪ፡፡ የያዛችሁትን የኪነጥበብ ጦር የህዝብን ምሬት  ለማሰማት  ስንታችሁ ናችሁ የተጠቀማችሁበት? ለህዝብ ከያኒ የህዝቡን ምሬት  መግለጫ ዋናው መሳሪያ  በእጃችሁ የያዛችሁት ኪነጥበብ አልነበር እንዴ? እናንተ ስትዝናኑ ህዝቡ  ጉልበቱን  ታቅፎ  በባዶ ሆዱ የሰው ያለህ ሲል ቢያንስ ቢያነስ በኪነታችሁ ስትጮሁ አላየንም ፣ የህዝብ መሆናችሁን ከማሳየት ይልቅ ፤ አልሰማንም አላየንም  ብላችሁ  ስለመንግስተ ሰማያት  ስትሰብኩን የቄሱን ሥራ  እናንተ ስትሰሩ  ያጢሳችሁን፣  ለአጭሩ ዕድሚያችሁ አይኔን ግንባር ያርገው ማላታችሁ አልበዛም ቢላችሁ ህዝቡ  መልስ ይኖራችሁ ይሆን?
  ጦር ይዛችሁ ላለመቆማችሁ ምን ያህል  እርግጠኞች  ናችሁ?  እጃችሁ ላይ የግድ ጦር ጨብጣችሁ ማየት ህዝቡ ከእናንተ የሚጠብቅ ይመስላችሁ ይሆን? የጨበጣችሁት ርህራሄ የሌለው የማይታይ ጦር  ስለመሆኑ ምን ዋስትና  አላችሁ? የሠራዊት መር አርቲስቶች አይደለንም  የማለት ሞራሉ እውን አላችሁ?! እስቲ የህዝቡን ምሬት ያሳያችሁበት አንዲት ጠብታ የጥበብ ስራችሁን  እንሆ በማለት ማስረጃ ጥቀሱ፡፡ የተመለመላችሁበት መስፈርት  የህዝብን ምሬት ለመንግሰት በማስተጋባታችሁ ይሆን?!  የህዝብን ምሬት የሚያስተጋቡ የት ነው ያሉት?
‹‹እናንተም ላሳያችሁ ፍቅርና ትህትናችሁ እግዚአብሔር ዋጋችሁን ይክፈላችሁ፤››
  ይህ ዓረፍተ ነገር   እንዲህ የሚል ቶን ያለው ይመስለኛል፡፡እናንተ በመኪና እያንሸራሸራችሁን ከእናንተ እኩል እንድንመስል  በማድረጋችሁ፣  ዘና እንድንል ስላደረጋችሁን፣  ሆቴሎች ስላሳያችሁን፣ አጠገባችሁ ፎተ ስለተነሳን፣  እናንተ የተታኮሳችሁበት ታንክ ላይ ፊጢጥ ብለን ስለአቅራራን፣  እንደ ጓዳችሁ አቅርባችሁ  አብዮታዊ መመሪያ ስለሰጣችሁን፣ ቢሮአችሁ ሰተት ብለን እንድንገባ አጋጣሚውን ስለፈጠራችሁልን፣ የሀገሪቷ  ቁንጮ ሹማምንቶችን ስልክ በቀላሉ ስለአገኘን፣  የሆነ ፕሮጀክት ይዛችሁ ኑ እናጸድቅላችሁለን  ስላላችሁን፣ የበለጠ በጋራ የምንሰራበትን ሁኔታ  የያዛችሁትን  ሥልጣን መከታ በማድረግ  እንደምታመቻቹልን  ቃል ስለገባችሁልን ወዘተ… እግዝሐብሔር ዋጋችሁን  ይክፈላቸሁ  እያላቸሁ ይመስለናል ብንልስ  ሰይጣናዊ ሀሳብ አሰብን እንባል ይሆን!? 
   ህብረ-ቃል፣ ሰሙ፣ ወርቁ እያልን የዘገባውን ይዘት በእኛ አይን ብንፈታው ክፉ አሳቢ! ቡዳ! ምን አለ ብንሞዳሞድ!? ምን አለ በተገኘው አጋጣሚ የድርሻችንን  ይዘን  አገራችንን ወደ መካከለኛ  ገቢ ያላት ሀገር ብንቅላቅላት!? ምን አለ በተዘዋዋሪ መንገድ  በቀኝ አዙር  ለአገራቸው የሰሩ ተብለን  ሽልማት ቢጤ በተመቻቸ መድረክ ቢሰጠንና ከፍ ከፍ ብንደረግ!  ምን አለ በኛ ከፍ ከፍ ማለትና በእኛ መሸለም አንሞዳሞድም ብለው በችጋር የሚቆራሞቱ እነ በዓሉ ግርማ፣ ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን ወዘተ.. የሚያክሉ የጥበብ ፈርጦች ናቸው፣ ክላሲክ ሥራ ሰርተዋል ሳይባሉ እንደተገለሉ ማለፋቸው ትርፍ ያላገኙበት ኪሳራ  መሆኑ ያልገባቸውን  የሞያ ታላላቆቻንን አንጎል ብናደርጋቸው!?  ደግሞ! ደሞ.. ደሞ! .. ከጎናችን የተሰለፉ በጸሐፊ እና በነፃ ጋዜጠኝነት ስም የሚጫወቱ ትርፍራፊ የሚለቃቅሙ አንድ አንድ ጋዜጠኛ ተብዬዎቻችንስ!? በቀኝ አዙር እጅ መንሻ የሚሰጣቸው፣ ወደ መካከለኛ ባለሀብትነት ለመቀላቀል የህዝብ ምሬት ብዕራችን አይጽፍልንም! አያዋጣም! አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ጹህፍ እየጻፍን፣ እያስጻፍን  አብዮቱ ግቡን እንዲመታ ዘና ብለን ማኪያቶአችንን እየጠጣን የድርሻችንን እናበረክታለን የሚሉትስ?!  ለምን እኛ ብቻ ልትሉ ትችላላችሁ፡፡ እውነተ ነው በዚህ እንስማማለን  በቀጣይ ግለ ሂሴን አወርዳለው፡፡
ሲጠቃለል!      
  የተወሰኑ አርቲስቶቻችን ከመሸ የደርግ ዘመን አብዮታዊ ኪነትን  ሊያመጡ ሲራወጡ እየታዘብን ነው፡፡ አንድ አንድ ጊዜ   በቴሌቪዠን መስኮት እነዚህን አርቲስቶችን ስመለከት በደርግ ዘመን  ከአብዮታዊ መሪያችን ጋር ወደፊት በማለት የፕሮፓጋንዳ ዘፈን ሲዘፍኑ የነበሩትን አስተኳሽ እርካሽ ተወዳጅ የኪነጥበብ ሰዎችን የስታውሱኛል፡፡ የሚገርመው አንዳንዱ አሁንም ማሊያቸውን  ቀይረው ልማታዊ መንግስታችን፤ ልማታዊ  መሪያችን ሲሉ  እንደ  ቅዠት ሁሉ ይታዩናል፡፡  በደርግ ዘመን  በአንድም ይሁን በሌላ መንገድ በውትድርና ውሰጥ ተሳትፈው የአንባገነኑን ደርግ መንግሰትን እድሜ ለማራዘም አንድ ጥይት እሰከሚቀር ድረስ በሚል ቀመር የበኩላቸውን አስተዋፆ ሲያደርጉ የነበሩ ግለሰቦች በአርቲስት ስም በሞቀበት የማድመቅ የረጅም  ጊዜ ልምድ አለን በማለት  የለመዱትን ወደፊት በሉለት! ከቀድሞ መንግስት ኢኮነሚያዊ ይዞታ በተሻለ መልኩ ሆነው በግል መኪናቸው እየተሸከረከሩ በተሸከርካሪ ወንበር ላይ እየተንደላቀቁ በትርፍ ሰዓታቸው አብዮታዊ ግዴታቸውን ሲወጡ ሳንፈልግ በግድ በየቤታችን ቤተሌቪዥን መስኮት አናያቸዋለን፡፡  የሚገርመው ጉዳይ እየሰሩት ያለው ነገር ከህዝብ ያጋጨኛል ብለው ለጥቂት ሰከንድም የሚያሰቡ አይመስሉም፡፡ አርቲስት ነኝ  የህዝብ ሀብት ነኝ፣ ነን እያሉ  እነ ህዝቡ የሰሩትን የኪነጥበብ ሥራ በማድነቅ፣ በማክበር ከእለት ጉርሱ እየቀነስ ከፍሏቸው እደጉ ተመንደጉ በማለት ከምንምና ከባዶ እርሱ እየተራበ ወደ ባለሃብትነት  ጎራ ሲቀላቅለቀቸው  ይህንን ምሲከን ህዝብ ቁልቁል በመመልከት በምን ታመጣለህ መንፈስ ሲፎክሩ፣ አመራር ሲቀበሉ፣ ከህዝብ ልብ ውስጥ ብንወጣም በቀኝ አዙር የህዝቡን ገንዘብና ሀብት እርግጫችን እስከ አለ ድረስ እኛም አለን ሲሉ፣  ከህዝብ ያልሆነ የህዝቡን ችግርና ብሶት ያላሳየ  አርርቲስት  ነኝ ባይ  የኪነ ጥበብ ባለሞያ ሳይሆን ሠራዊት መር ቡድን ነው፡፡ እርግጥ ነው አንድ የጋዜጠኛ ማህበር ሊቀመንበር  በኢትዮጵያ ውስጥ በጋዜጠኞች ላይ ስለሚደርሰባቸው  እስርና ወከባ ሲጠየቁ  ለጠያቂው ጋዜጠኛ እኔ ባክህ ቦሌ ላይ ማኪያቶዬን እየጠጣው ቺኬን(ቆነጃጅት ሴቶችን ማለቱ ነው) ነው ማየት የምፈልገው ብለው እንዳሉት እነዚህም እንደዚህ አይነት የህይወት ፍልስፍና የላቸውም ብለን ለማለት ሥራ ነገራቸውን ማስተዋል በቂ ነው፡፡
      ሰው በላው ኢዲያሚን ዳዳ፣የሰው ልጅን በቁሙ እያሰለፈ በእሳት የሚያቃጥለው በመርዝ የሚፈጀውም ሂትለር ህዝቡ፣ ህዝባችን እያሉ የሚፈጁት ህዝብ ፣ ህዝብ አይደለምን እንዴ ? የሚል ጥያቄ ሲነሳ መልሳቸው ለህዝብ ነው የምንኖረው፣ የምንሰራው በማለት ከአፋቸው የሚወጣ ሠርክ የምንሰማው መፈክራቸው መሆኑን ከታሪክ ስንረዳ በእርግጥም ለህዝብ ማለት ምን ማለት ነው ብለን ብንጠየቅ ትክክል ነው፡፡
    ምናልባት ህዝብ የሚለው ቃል ህዝብ የሚጨቁነውም ለህዝብ የቆመውም የሚጠቀምበት ስለሆነ ህዝብ ማለት መንግሰት ነው( የማይሰራ፤ ያረጀና ያፈጀ አይንህን ያዝ ላሞኝህ ፍልስፍና)፣  ታሪካዊ አመጣጥ፣ ትንታኔ፣ ትርጉም፣ ጽንሰ ሀሳብ በማለት አርቲስቶቻችንን  የባሰ ግራ  ሳናጋባ በዚህ ጸሓፊ እምነት ህዝብ ማለት ጎረቤታቸችን የሚበሉ የሚጠጡት ያጡ ወገኖቻችን፣ መንገድ ላይ በላስቲክ ቤት ልጆቻቸውን ሰብስበው በልመና ያገኟትን እንጀራ ለመብላት ድንጋይ ጎልተው ወጥ የሚወጠውጡ፣ ጀርባቸው እስኪጎብጥ በደከመ አቅማቸው ቅጠል ተሸክመው ቁና ቁና የሚተነፍሱ፣  ሆዳቸው  ተጣብቆ አውላላ ሜዳ ላይ ተዘርረው ማን ነህ ያልተባሉ ወገኖች፣ ከገንዳ ላይ ከውሻ አጥንት እየተናጠቁ የሚግጡ፣ በአስተዳደር በደል የህይወታቸው አቅጣጫ ተቀይሮ ከብርሃን በፈጠነ ሁኔታ ስራ አልባ የሆኑ ፣ቤት አልባ የሆኑ፣ ንብረት አላባ የሆኑ፣ በአመለካከታቸው ምክንያት የተሰደዱ፣ የታሰሩ ፣ የተገለሉ፣ ቤተሰባቸው የተበተነ፣ወዘተ….. ናቸው ብንል የህዝብ ትርጉምን አጣመሃል እነደማንባል ተሰፋ እያደረግን ነው፡፡ ስለ እነዚህ  የሚሰራ ነገር አይኖር ይሆን!? ይሄ ለኪነጥበብ ባለሞያው ውሃ የማይቋጥር ጭብጥ(theme) ሆኖ ይሆን! ወይስ ይሄ ወቅታዊ ጉዳይ ስላልሆነ!?  ወይሰ በእሳት ጫዋታ እናዳይሆን! የዚህ ጹህፍ ጸሐፊ መልዕክት ግን በምንም በማንኛውም  መንገድ!  በየትኛውም ሂሳብ ከያኒ ከህዝብ  ከተለየና ሹማምነት ልሁን ካለ ይሀ አርቲስት ሳይሆን ገዢ ነው!  ገዚዎች ደግሞ ሁሌ አይኖሩም ህዘብ ግን ለዘላለም ይኖራል፡፡ አሁን አገር ይያዝልኝ! ያዙኝ ልቀቁኝ የሚል( በአንድ ናይት ክለብ ሲዘፍን መዳከሙን አይተው ደጉ ሰውዬ  ሚሊየን ብር እጅ መንሻ  ሰጥተው ነፍሱን እንዲዘራ ያደረጉት አርቲስት፡፡) በደርግ ዘመንም እንደዚሁ ሀገሬን!... በማለት በመፎከሩ የምናውቀው አርቲሰት በሰባዎቹ አጋማሽ ላይ በአንድ መጽሔት  ላይ የጠቀሳትን ጥቅስ እኔም ልጥቀስና ጹሑፌን ላጠናቅቅ፡፡ «አርቲስት በህዝብ መዳፍ ላይ እንዳለ እንቁላል  ነው»፡፡  


በዝራው አሻግሬ