በነጋዴዎች የተወረረች ቤተክርስቲያን!
«እየሱስም
ወደ መቅደስ ገባና በመቅደስ የሚሸቅጡትንና፣ የሚገዙትን ሁሉ አወጣ የገንዘብ ለዋጮችንም ገበታዎች ፣የርግብ ሻጮችንም ወንበር
ገለበጠና፡- ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላላች ተብሎ ተጽፎአል፤ እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋአችሁት፤ አላቸው፡፡»
የማቴዎስ
ወንጌል ምዕራብ 21 ቁ. 12
አሁን አሁን መንገድ ዳር ያለ የቤተክርስሪያን አጥር ማግኘት ፈታኝ እየሆነ መጥቷል፡፡ ቤተከርስቲን በተለያየ የንግድ
ተቋማት ዙሪያዋን ተወራ ነው የምናስተውለው፡፡ አንድ መእምን የቤተክርስሰቲያን በር ላይ መድረስ ቢያቅተው በርቀት የቤተክርስቲያና
የግንብ አጥር በመዳሳስ እባረካለው ብሎ ማሰብ ለእርሱ እንደ በፊቱ አሁን ቀላል አይደለም፡፡ በተለያዩ የንግድ ቤቶች የተያዘውን
አጥር በማለፍ ለንግድ ቦታ ለጊዜው ያልፈረሰ አጠር ለማግኘት ቤተክርስቲያናን
ዙሪያውን መሸከርከር ይጠበቅበታል፡፡ በመከራ በንግድ ቤቶች መካከል ወይም አጠገብ የተገኘ የቤተክስቲያና አጠር
ቢኖር መሳለማችን የተባረክን ያህል ውስጣችን ላይሰማን ሁሉ ይችላል፡፡
ቤተክርስሲያን የንግድ ማዕከል ወይም የጉልት አይነት ሳትሆን ቃለ እግዝሐብሔር የሚሰማበት፣ ጸሎት የሚደረግበት
፣የተረጋጋ መንፈስ የሚታይበት እንዲሁም ምዕምናኑ ራሱን ለማረጋት የሚመርጠውና የሰከነ መንፈስ አገኝበታለው ብሎ አንድ
ክርስቲያን የመጀመሪያ ምርጫው የሚያደርገው ቦታ ቢኖረ ቤ/ክርስቲያን
ናት፡፡ ምክንያቱም የዓለም ጫጫታና ሁካታ ሰልችቶት ለዚህ ደግሞ የእግዛብሔር መንፈስን አገኛለው ብሎ መጥቶ ቤተክርስቲን
ዙሪያዋን በነጋዴዎች እሰጣ ገባ ሰላሟ ተናግታ ቢያገኝ እሸሸግበት ጥግ አጣሁ ቢል ምን ይፈረድበታል፡፡
ዛሬ ከቤቴክርስቲያን አጥር ዙሪያ የልብስ መሸጫ፣የመኪና ዕቃ መሸጫ፣ኢንተርኔት ቤት፣ካፌ፣ኤሌክትሮኒክስ መሸጫ፣
የመኪና ማከራያ፣ፎቶ ቤት፣ባንክ ቤት፣ስፖርት ቤት፣ጸጉር ቤት፣ የብሎኬት
ማምረቻ ወዘተ…. ማየት አዲስ አይደለም፡፡ አዲስ ወይም
እንግዳ ሊሆን የሚችለው ቤተክርስቲያን አጥሯን ለነጋዴዎች
ሳታከራይ ጦማን ስታድር ማየት ነው፡፡ ይህንን ቢዘነስ የለመደ አንድ ካህን ዋ! ማኛ ቦታ ነው ጦሙን ያሳደሩት ብሎ የቤተክርስቲያኗን ሰበካ ጉባኤ በሆዱ ሊረግም፣ በጋዶኞቹ ወይንም ግንኙነት ካለው በአካል
በመሄድ ጥቆማ አይሰጥም ማለት እንግዳ ነው፡፡ እያወራን ያለነው በከተማ ውስጥ ስለ አሉ ቤተክርስቲያናት ነው፡፡
የመጽሐፍ ቅዱስን ማቴዎስ ወንጌል ምዕራብ 21 ቁ.12 ምክንያት በማድረግ ቁጥራቸው ቀላል ያልተባለ የቤተክርስቲያን
ሊቃውንት በቤተክርስቲን ዙሪያ መነገድ ወይም ማስነገድ ክርስቶስ ቤቴን የወንበዶች አደረጋችሁት ካለው ጋር የሚመሳሰል ነው፡፡
ይህ ተግባር የሽቀጣ ሥራ ሥለሆነ ትክክል አይደለም ይላሉ፡፡ አንዳንዶች ደግሞ የማይገናኝ አታገኛኑ ቤተስኪያን ቅጥር ጊቢ ውስጥ
መሸቀጡ ነው ችግሩ! ከምዕመናን ከሚገኝ ገቢ ብቻ ቤተክርሰቲያን መተዳደር የለባትም፡፡ የራሷ የገቢ ምንጭ ሊኖራት ይገባል፡፡
ከኛ ተርፎ ለአባይ ቦንድ ልንገዛ አቅም ያገኘነው የገቢ ምንጭ በመፍጠራችን ነው ነው ይላሉ፡፡
ለምንድን
ነው ቤተክርስቲያን አጥሯን እያፈረሰች ገበያ የምታደርገው?
አንድ አንድ ለቤተክርስቲያና አስተዳደር ቀረቤታ አላቸው የሚባሉ ሰዎች እንደሚገልጹት ቤ/ክርስቲያን ከምዕመናኑ
በተለያዩ ምክንያት ከምትሰበስባቸውና ከምእመናኑ መጽዋተ ሙዳይ ከምታገኘው ገቢ በስተቀር ይህን ያህል ለቤተክርስቲያና አገልጋዮች
የምትከፍለውን ደምወዝና ለተለያዩ ልማታዊ ሥራዎችን የምታከናውንበት በቂ ገንዘብ ስለሌላት ነው የሚል ምክንያት
ይሰጣሉ፡፡
እርግጥ ነው የቤተስኪያን አገልጋዮችና ሌሎችም ልማታዊ ሥራዎችን ለመስራት ገንዘብ
ያስፈልጋል፡፡ ቢሆንም የቤተክርስቲያን አጥርን
እያፈረሱ ቤተክርስቲያን በንግድ ቦታና በአምልኮተ እግዝሃብሔር
ሥፍራነት ከመቀላቀል ውጪ የቤተክርስቲያንን የተረጋጋ መንፈስና
ቤተክርስቲያናዊ ድባብ ጠብቆ ገቢ የሚገኝበት ሁኔታ የለም? ከምዕመናኑ የሚሰበሰቡ የስለት ገቢዎች፣ የስብከተ ጉባኤ የአባልነት
ክፍያ፣ ከመካነ መቃብር ማሰፈጸሚያ ገቢ፣ከሙዳየ መጽዋት ገቢ፣ በቤተክርስቲያን በሚተዳደሩት ትምህርት ቤቶች ከሚገኝ ገቢና መሰል
ገቢዎች የሚገኝ ገንዘብ የተገለጸውን ወጪ ለመሸፍን አይቻልም ይሆን? ሌሎች መእመናኑን በሃይማኖቱ ጸንቶ እንዲቆይ የሚያደርጉና በአንጻሩ ደግሞ ገንዘብም
የሚገኝባቸው እንቅስቃሴውዎች ማድረግ አይቻል ይሆን?! የሚገርመው አንድ አንድ ገዳማት ምዕመናኑ ከቤቴክርስቲያኑ ውስጥ በአጥሩ
ዙሪያ ቁጭ ብለው ጸሎት የሚያደርሱበትን፣ ስብከተ ጉባኤ የሚሰሙበትና በሰከነ መንፈስ ከፈጣሪያቸው ጋር እንዲገናኙ በሚል
የተዘጋጀውን የፀሎት ቦታና ቂጥን ማሳረፊያ ሥፍራን ሳይቀር
በማፈራረስ ለንግድ ቦታ እየተከራየ ነው ያለው፡፡
ለንግድ ተረግባር አጥር
በርግዶ መከራየት ካለበትስ የቤተክርስሰቲያና የእምነት ስፍራነት ለማያውክ የንግድ ሥራ ማከራየት
ይቸግር ይሆን?
በተለያየ አጋጣሚ ቤተክርስቲያና ለምታከራያቸው ግለሰቦች የምታዘጋጀውን የስምምነት ውል በሥራ አጋጣሚ እጄ ሊገቡ ችለው የውሉን ይዘት ለማየት ችያለው፡፡ ውሎቹ በአብዛኛው
በቤተክርስቲያኗ የሚዘጋጅ ወይንም አንዱ ደብር ከአንዱ ደብር ገልብጦ የሚያመጣው በአብዛኛው ተመሳሳይ ይዘት ያላቸው የውል አይነቶች ናቸው፡፡ ሁል ጊዜ በቋሚነት
የሚጠቀሰ አንድ አረፍት ነገር/አንቀጽ አለ፡፡ ይህውም ተከራይ
ወገን (ውል ተቀባይ) በተከራየው ቤት ከቤተክርስቲያኗ እምነት ጋር የሚጣረስ ተግባር ማከናወን የለበትም
የሚል ነው፡፡ ይሄ አንቀጽ በተለያየ አገላለጽ በየተለያ ደብሮች
የውል ስምምነት ውስጥ ተጠቅሶ ቢገኝም ሁለት
ችግሮች ይታዩበታል፡፡
አንደኛው የሀረጉ ግልጽነት መጉደል(vague)ወይም ምንድን
ነው ከቤተክርሰቲያን እምነትና ስርዓት ጋር የሚጋጭ የንግድ ተግባር ሲባል? በአብዛኛው የቤተክርስስቲያን አከራይ የሰበካ ጉባኤ
አባላቶች ትኩረት የሚያደርጉት የመጠጥ ንግድ፣ ቤተክርስቲያና ከምትከተለው ሃይማኖት ውጪ ያሉ የእምነት ድርጅቶች
እንቅስቃሴ፣ሙዚቃ ቤት ወዘተ ሲሆን ከእነዚህ የንግድ ተግባሮች ባልተናነሰ የቤተክርስቲያኗ ሰላምና መረጋጋት ወይም ድባብ የሚያውኩ
የንግድ ስራዎች ላይ እምብዛም ትኩረት አይሰጣቸውም፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ምንም እንኳን ከቤተክርሰቲያን እምነትና ስርዓት ጋር
የሚጋጭ የንግድ ተግባር ማከናወን እንደ የውል ማፍረሻ ምክንያት ተደርጎ የተገለጸ ወይም የተከለከለ ተግባር ቢሆንም ተከራዩ
ከአከራዮቹ ጋር ባላቸው ግንኙነት ምክንያት ተገቢው ክትትልና
ውሉን የማስፈጸም ሥራ አለመሥራታቸው ነው፡፡
የንግድ ቦታ ኪራይ ሁኔታ
እንዴት ነው የሚካሄደው?
የቤተክርስስቲያን የንግድ ቦታ ኪራይ በአብዛኛ የሚካሄደው ቤተክርስቲያና በምታቀርበው የጫራታ ውድድርን ማዕከል
አድርጎ ነው፡፡ ይሁንና ጨረታውን በአደባባይ ገልጸው በህጋዊ መንገድ የሚሰሩ ገዳማት ያሉ ቢሆንም አንዳንድ ቤተክርስቲያኖች ላይ
በጨራታና በጨራታው ሂደት ላይ የሚታዩ ቀላል የማይባሉ ችግሮች አሉ፡፡ ችግሮችን ለመጥቀስ ያህል አንድ ግለሰብ በተለያየ ስም የሚያስገባቸው የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዶች፣ ጨረታው ብዙ
ተወዳዳሪ እንዳያየው በአጭር ግዜ ውስጥ እንዲከናወን ማጣደፍና የጨረታው ማስታወቂያ የማይታይበት ቦታ መለጠፍ ዋና ዋናዎቸ ሲሆኑ
የተለያየያ ጫራታውን የቤተስኪያኗ አስተዳደሮች ለሚፈልጉት ወይም ለተደራደሩት ሰው እንዲያመች ለማድረግ የሚፈጠሩ አንቅፋቶቸ
አሉ፡፡ የሚመለከታቸው የቤተክርስቲያን አስተዳሮች ጨረታ ከማውጣታቸው በፊት ገንዘብ አለው ብለው ያሉትን ግለሰብ ወይም ቡድን ፣ጨረታ ሊያወጡ መሆኑን የተጠየቀው ግለሰብ ለጨረታው ፍላጎት ያለው መሆኑን ይጠየቃል፣ ወይም ከኮሚቴዎቹ አንዱ ለሚያውቀው ሰው
መንገዱ እንደሚያመችለት በመግለጽ ለጨረታው ይጋብዛል፡፡ ወይም
የቤተክርስቲያኗ አጥርን አፍርሶ የሆነ ንግድ ለመነገድ የቋመጠ
ሰው ለሚቀርቡት የቤተስኪያን ሰዎች ወይም የቤተስኪያን ሰዎችን በሚቀርቧቸው ሰዎች አማካኝነት እነእርሱ በግል ሊያገኙ የሚችሉትን
የገንዘብ መጠን በመግለፅ መነሻ ሀሳብ ያቀርባል፡፡ በዚህ ሁኔታ ሂደቱ የሚጀምረው የቤተክርስቲያን አጥር አፍርሶ የንግድ ቤት
ማከራየት ድርድር ለቤተክርስቲያኗ ኃላፊዎች ከፍተኛ ገንዘብ ለእጃቸው የሚያስገኝ ነው፡፡ ድርድሩ
ከቤተክርስቲያና ራቅ ተብሎ በመጠጥ ቤት አንድ ሁለት
እየተባለ ነው የሚካሄደው፡፡
በዚህ ድርድር የስብከተ ጉባኤ ኮሚቴዎች፣የቤተክርስስቲያና ቁጥጥር ኮሚቴ፣ የቤተክርስቲያኗ ጸሀፊዎችም ጭምር ሊካተቱበት ይችላሉ፡፡ ለዚህ
ድርድር የማይመቹ ናቸው በመባል የሚታወቁ ሰዎች እና እግዝሐብሔርን ልናገለግል ነው ብለው ከልባቸው እውነተኛ ስሜት ሥራቸውን
የሚከውኑ ካህናትም ሆነ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ከተለያዩ ቦታ የተውጣጡ የስብከተ ጉባኤ አባላት በምንም መንገድ እንዳያውቁ ተደርጎ
ነው በጀባቸው በቤተክርሰቲያን ስም ገንዘብ የሚሰራው፡፡
የቤተክርስስቲን አጥር
ዙሪያ ቁማርተኞች
እነዚህ ግለሰቦች ወይም ቡድኖች ከቤተክርስቲያና አስተዳደር
እስከ ከፍተኛ የሃይማኖቱ መሪዎች ድረስ ግንኙነት ሊኖራቸው
ይችላል፡፡ ትዕዛዝ ሊቀበሉ፣ ትዕዛዝ ሊያሰጡ፣ ትዕዛዝ ሊሰጡ ሁሉ ይችላሉ፡፡ የሥራ መደብና የቤተክርስቲያን የክብር መጠሪያ ሊኖራቸው ይችላል፡፡ የሐይማኖት ትምህረትን ያወቁ የመጠቁና የተከበሩ
ሰዎች ናቸው ሊባሉ የሚችሉ ጭምር ናቸው፡፡ የቤተክርስቲያን ትምህርት ምንም ዕውቀት የሌላቸው በቤተክርስቲያና ውስጥ የማያገለግሉ
ነገር ግን የድለላ አይነት ተግባር በአገር ልጅነት የሚሰሩ ሰዎችም ይገኙበታል፡፡ ገንዘብ
ሲደራደሩ ይህ በእግዝሐብሔር ቤት ላይ ነው ወይስ አንድ አለማዊ በጣም ስነምግባር የሌለው፣ ነውር፣ ርህራሄ የማያቅ
የንግድ ድርጀት ሰዎች ጋር ነው የምደራደረው ልንል ሁሉ እንችላለን፡፡ እነዚህ የቤተክርስቲያን አባቶች አይደሉም
እንዴ? ምንድን ነው ነገሩ? ልንል ሁሉ እንችላለን፡፡ ምንአልባት በእርጋታ መንፈስ በማየት ጊዜው ነው
ብለን እነሱን ሳይሆን ያላቸውን ሃይማኖታዊ ማዕረግ ወይም ልብሰ ተክህኖአቸውን ማየት ነው ብለን ራሳችንን ካላረጋጋን
በስተቀር ጭንቅላታችንን አዙሮን
ሁሉ መሬት ላይ ልንፈጠፈጥ
እንችላለን፡፡
አንድ ጊዜ አንድ የግል ድርጅት ያለው ባለጉዳዬ ከአንዲት ቤተክርስቲያን በጫራታ በሺዎች ካሬ ሜትር በላይ የሆነ ቦታ አሸንፌ ተከራይቻለውና መጥትህ ውል ተዋዋል
ስለተባልኩኝ ሂደቱ እኔን የማይጎደኝ መሆኑንና በህግ ሊያስከትልብኝ የሚችለው ችግር በማየት ምከር ትለግስኛለህ ይለኝና ወደ አንድ
ቤ/ክርስቲያን አመራን፡፡ መንገድ ላይ መኪና ውስጥ እያለን ስልክ ከተለያየ አቅጣጫ ሲደወልልት በንዴት ሲመልስ
እሰማዋለው፡፡ ይሀን ያህል መቶ ሺህ ብር ሰጥቻለው በድጋሚ ደግሞ አንተ በጎን ትጠይቀኛለህ? ከዚህ በላይ ምንም አላደርግም
የፈለጋችሁትን አድርጉ፡፡ እዛው መጨረስ የሚገባችሁን ለምን ወደ እኔ ታመጣላችሁ፡፡ በተናጥል አትምጡብኝ ተስማምታችሁ ኑ!
ወዘተረፈ ቃላቶች ይሠነዝራል፡፡ ገረመኝና ስልኩን አናግሮ ሲጨርስ
ምንድን ናቸው እነዚህ ብዬ አልኩት፡፡ የቤተክርስቲያና
ሰዎች ናቸው
ትንሸ የሻይ(የሻይ
ያለኝ ኃላ ስደርስበት በመቶ ሺህ የሚቆጠር ገንዘብ
ነው) ሰጥቼአለቸው ነበርና እኔ ተጎድቻለው ለብዙ ነው የተከፋፈልነው በማለት የተወሰኑት በጎን እየመጡ ነው፤ አንጣ የሚሉን
አለኝ፡፡ ለምን ትሰጣለህ ጫራታውን በህጋዊ መንግድ አይደል እንዴ ያሸነፍከው አልኩት፡፡ እሱማ ነው፡፡ ግን ምን መሰለህ
ጨረታውን ያሸነፉት ሌሎች ድርጅቶች ነበሩ እኔ ውስጣቸው ሰው ስለአለኝ የተወሰነ ገንዘብ ስጥና በጫረታው ሰነድ ላይ «ያለውን
አጫራች የተሻለ አማራጭ ካገኘ በጨረታው አይገደደም» የሚለውን አንቀጽ
በመጠቀም ነው በጫራታ ካሸነፈው ድርጅት የተሻለ ዋጋ
እሰጣለው ብለህ ደብዳቤ አስገባና ጫራታውን አንተ እንዳሸነፍክ እናደርጋለን
ብለውኝ ነው ቦታውን ያገኘሁት አለኝ፡፡
አሁን የቤተክርስቲያኗ አስተዳደር ቢሮ ውስጥ ነው
ያለነው፡፡ ባለጉዳዬ አባታችን
ብሎ ወገቡን አጎንብሶ የቄሱ ጉልበት ሥር
እንደመውደቅ ብሎ የእሳቸውን ቡራኬ ሲቀበል ይሄ ሰው ቅድም ሲያማቸው አልነበር እንዴ ብዬ አይ ኢትዮጵያ እያልኩ ከራሴ ጋር ስነጋገር እኔንም ጎሸመኝና ውስጤን
እየከነከነው ሳልወድ በግድ በደመነፍስ አባታችን አልኩ እየተደነባበርኩ፡፡ ከተወሰነ መነጋገር በኃለ ውል እንዋዋላለን ብሎኝ ያመጣኝ
ርዕሱ ተቀይሮ ሌላ ጉዳይ ፊቴ አቀረቡልኝ ቀና ብዬ ያመጣኝን ሰው አየሁት፡፡
ችገር የለም ቀጥል የሚል ምልክት አሳየኝ፡፡ ገረመኝና
የሚያወሩትን ዝም ብዬ እሰማ
ጀመር፡፡ አሰተዳደሩ እንደከፋኝ ገብቷቸው ይሁን ወይ ደግሞ ውጥረቱን በማብረድ መቀራረብ ለመፍጠር ሥምህ ማን ነው ያልከኝ… የሚገርም ሰም ነው ያለህ በማለት በስሜ ላይ መጽሐፈ ቅዱሳዊ ትንታኔ ይሰጡ
ጀመር፡፡ እኔ ብዙ አልተመቸኝም፡፡ እዚህ ቢሮ ከመግባቴ በፊት የሰማሁት ነገር ውስጤን ረብረሾታል፡፡
በሆዴ በእኛ ሃይማኖት ነው አይደል እነዚህ ወንበር
ላይ ቁጭ ብለው ቁማር የሚጫወቱት
አልኩኝ፡፡ አሁን ማን እኝህን ሰው
በሌላ ይጠረጥራል አልኩ፡፡
ቢሮው ውስጥ 4 ሰዎች ነን ያለነው፡፡ አባታችን፣ አንድ ወጣት ሰው(ኋላ ላይ የሂሳብ ባለሞያ ነው፣ ጉዳዩን የሚሸምነው እሱ ነው ብሎ ባለጉዳዬ ነግሮኛል)፣ ባለጉደዬ እና እኔ፡፡ ለእኔ ለማሳየት ፋይል ይዞ የመጣው ሰው ገብቶ ፋይሉን
ከአስተዳደሩ አባታችን ጠረጴዛ ፊት ላይ ሲዘረግፍው የባሰ
ተናደድኩና ድንገት ድምጼን ከፍ አድርጌ እኔ ከመጣሁበት ጉዳይ ሌላ
ጉዳይ አይመለከተኝም የእኔ የህግ
አማካሪነት ለእርሱ ድርጅት ነው(ለባለጉዳዬ ማለቴ ነው) የእናንተ ደግሞ ሌላ ድርጅት ነው፡፡ በራሳችሁ ጠበቃ ልትቀጥሩ ወይም ከበላያችሁ የእናንተ ቤተስኪያን የህግ
አገልግሎትን በማናገር ለጉዳያችሁ መፍትሔ ማግኘት ትችላላችሁ
አልኩኝ፡፡
እነ አባታችን ቀደም ሲል ከቤተክርስቲያኗ ጋር ለአለፉት ዓመታት በኪራይ ሲሰራ የነበረው
የኮንስትራክሽን ማቴሪያል አምራች ድርጅት ባለቤት
የተከራየውንና ባለጉዳዬ ያሸነፈበትን ሰፊ ቦታ ማሽኖች
ስላሉኝ ለመንቀል ጊዜ ስጡኝ በማለት አልወጣም ብሎኛል ምን
እናድርግ በሚል ነው፡፡ ከድርጅቱ ባለቤት ጋር የተደረገውን ውልና የተለዋወጡትን ደብዳቤዎችና
ሰነዶች ነው ያቀረቡልኝ፡፡ (ኋላ ላይ ከኮንስትራክሽን ማቴሪያል ድርጅቱ ባለቤት ጋር ስንገናኝ በእርሱ ህጋዊ ሆነ
ህጋዊ ባልሆነ እንቅስቃሴው በሚረባ በማይረባ ነገር ከፍተኛ የሆነ ገንዝብ በየወቅቱ እየሰጠ ያስለመደ
መሆኑን ተረድቻለው፡፡)
ግዴለም እኛም እናንተም ማለት እኮ አንድ ነን፡፡ እንደ ሌላ ሰው አትየን፣ የቤተሰብ ሥራ እኮ ነው፣ የጋራ ጉዳያችን እኮ ነው፣ ደሞ ቤተክርስቲያኗ የአንተም
ጭምር ናት ከፈጣሪ ታገኘዋልህ…. በሚል የቃላት መኣት ወረወሩብኝ መልስ ለመስጠት እንኳን ጊዜ አሳጡኝ፡፡ አሁን ከእነዚህ ጋር እሰጣ
ገባ ውስጥ መግባት ጠቃሚ እንዳልሆነህ ተረዳሁና ከወንበሬ
ተነስቼ ያመጡት ዶክመንቶች እያገላበጥኩ ማየት ጀመርኩ፡፡ ምን
ያህል አሻጥር በቤተክርስቲያኗ ላይ እንደሚሰራ ተገንዝቤ ንዴቴን
በማፈን አንዳንድ ጥያቄ መጠየቅ ጀመርኩ፡፡ ይህንን ሰውዬ
ማን ነው ይህን ያህል ሠፊ ቦታ ያከራየው?(ከቤተክርስቲያና ጋር
ያደረገው ውል ስላላየሁ)እኛ ያከራየነው ሌላ ድርጅት
ነው? የማከራየት ስልጣን ማን ሰጠው? እስቲ የማከራየት መብት እንዳለው የሚያሳይ ስምምነት ያሳዩኝ አልኩ፡፡
ፈገግ ብለው በምፅት እያዩኝ ነው፡፡ ብቻ በርካታ ጥያቄዎች ማንሳት
እየተቻለኝ ማንም ሰው ሊመልስልኝ እንዳለቻለ ስረዳ ጥያቄዎቼን ለጊዜው ውጬ ማወቅ የግድ አለብኝ ያልኩትን ብቻ ጠየኩ፡፡ አባታችን እባክህ ልጄ
አሁን የምትጠይቀው ሁሉ እኔ ከመሾሜ በፊት የተደረገውን ነው፡፡ እኔ
እኮ በቅርብ ነው እዚህ ቤ/ክርስቲያን የተመደብኩት አጨመላልቀውታል፣ መላም የለው አሉኝ፡፡ (እሳቸው በተራቸው ለማጨማለቅ የእጃቸውን
እጅጌ ሰብስበው እንደተነሱ ያልታወቀባቸው በሚመስል ሁኔታ፤ በሆዴ
ተጫወቱባት ይህችን ቤተክርስቲያን አልኩ፡፡) ሁኔታው ስላላማረኝ አንድ ሀሳብ መጣልኝና እንዲህ በሚል መለስኩላቸው፡፡
ይህንን ጉዳይ ቢሮዬ በእርጋታ ቁጭ ብዬ ነው ማጥናት ያለብኝ፡፡ የሰነዶቹን
ኮፒ ግን እፈልጋለው አልኳቸውና የሰነዶቹን ኮፒ
እጄ አሰገባው፡፡
አዋቂ ሰውና አዋላጅ ያየውን በሙሉ አይናገርም የሚለውን አባባል ለጊዜው በመርህ ደረጃ ወስጄ ይህንን ጉዳይ ለማሳያ
ከገለጽኩ ወደ ተነሰሁበት ጹህፍ ልመለስ፡፡
የቤተክርስቲን
ኪራይ ሰበብ ሙስናዎች
በቅርብ ጊዜ ሊቀ ጳጳሳት የሆኑት አቡነ ማቲያስ በተሾሙበት ሳምንታት የኦርቶዶክስ
ቤተክርስቲን ውስጥ ሙስና እናዳስቸገረ በመገናኛ ብዙሃን ሲናገሩ ሰምተን እኝህ ሰው ቤተስኪያኗ ውስጥ ለማገልግል ምድባ እንኳን
ቤተሰባዊነት ወይም እጅ መነሻ የሚጠበቅባቸው የሃይማኖት አባቶችን ቢያንስ ቢያንስ እጅ መንሻውንና የቤተሰብ ምደባውነ ያስቀራሉ ይህንን ችግር መንግለው ያወጣሉ የሚል በምእመናኑ እምነት ተጥሎ ነበር፡፡ መሬት
ላይ ወድቆ የምናየው ግን ከጠበቅነው ውጪ ነው፡፡
የቤተክርስቲያን አጥር ተንዶ ወይም ተቆርሶ የሚሰሩት
ህንጻዎች ላይ ሳይቀር የራስ ኪስ ውስጥ የሚገባ ገንዘብ ይሰራባቸዋል፡፡ አንድ ጤነኛ ሆነ ጤነኛ
ባልሆነ መልኩ የቤተክርስቲያንን ንብረት የተከራየ ግለሰብ ወይ ድርጅት ከቤተክርስቲያኗ አስተዳደር ጋር የጥቅም ግንኙነት ከሌለው በአንድ አንድ ቤተክርስቲያን ድርጅቱ በተከራየው ቤት
የመቀጠሉ እድል አናሳ ነው፡፡ መነሻ የሚያደረገው ምንአልባት ቤተስኪያኗ ውል ልታቋርጥበት ትችላላች ተብሎ በኪራይ ውሉ ላይ
የተጠቀሰውን አንቀጽ በመጠቀም ሊሆን ይችላል፡፡ ምንአልባት ቤተክርስቲያና ለራሷ አገልግሎት የኪራይ ቤቱን ስትፈልግ ተከራዩን
ልታስወጣ ትችላለች የሚልና መሰል ለመደራደሪያ የሚያመቹ
አንቀጾችን በመጠቀም ነው፡፡ እኔ እጄ በገቡ ውሎቹ ላይ እንዳየወት እንኳን ውሎቹ በአብዛኛው የእኩሌታ(win win
negotiation) ደርድር ያለበት ሳይሆን አንደኛው ወገን ባለ ከፍተኛ ተደራዳሪነት(win lose negotiation)ያለበት
መሆኑን መገንዘብ ችያለው፡፡ ወደ የህግ መሰረታዊ የውል ጉዳዮች ሳንገባ
ቤተክርስቲያኗ ለራሷ የተሻለ አገልግሎት ለምስጠት በመፈለጋ ከተከራዩ ብትወስድ ምንአልባት ውልን መሰረት አድርጎ ስለሆነ
እንዲሁም ቤተክርስቲያና የህዝብ ናት የበለጠ መጠቀም አለባት ትክክል ነው ልንል እንችላለን፡፡ ይሁንና ይህ ለቤተክርስቲያና
አገልግሎት ተብሎ የሚሰጠው ምክንያት በእርግጥ ቤተክርስቲያና የተሸለ ማከራየት ይጋበታል ፍትሃዊ አይደለም ኪራዩ ተብሎ ሳይሆን ከተከራዩ
የሆነ መጠን ያለው ገንዘብ አከራዮቹ ለመቀበል ወይም ሌላ የተሻለ ገንዘብ የሚከፍልና ቀደም ብሎ ተከራይቶ የነበረውን ቤት ወይም
ቦታ የሚፈልግ ነጋዴ መጥቶ ሊሆን ይችላል፡፡ በነገራችን ላይ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የቤተክርስቲያን አጥር ዙሪያ አከራዮች
የኪራይ ብሩ ከፍ እንዲል ወይም ከፍ ባለ ገንዘብ እንዲከራይ መፈለግ ሳይሆን ዓላማቸው ኪሳቸው የሚገባውን ገንዘብ መጠን ማሳደግ
ነው፡፡ እነሱ ለቤተክርስቲያና ከፍተኛ የኪራይ ዋጋ ህጋዊ በሆነ መንገድ የሚያስገባ ተከራይ እምብዛም አይመስጣቸውም፡፡
የቤተክርስቲያኗን መደበኛ ገቢ የሚንያስበት የማያስነቃ (የማየስነቃ ሲባል በጣም የማይታወቅ በጥንቃቄ የተሰራ ማለት ሳይሆን
ትንሽ ብቻ ፊት ለፊት የማይታይ መሆኑ እንጂ አንድ ሁለት ጥያቄ ወይም ሰነድ ቢገላበጥ የሚደረስበት ሴራ ቢሆንም ችግር
የለባቸውም) መንገድ ከተገኘ ስለ ቤተክርስቲያና ገቢ ትተው ኪሳቸው የሚገባ የደለበ ገንዘብ ላይ ነው ትኩረታቸው፡፡ ኪሳቸው
የሚገባ ገንዘብ (አንዳንዴ ከኪራዩ ክፍያ በፐርሰንትም ይጠይቃሉ) ከተገኘ የክፍያ ጊዜ ሊያስረዝሙ፣ የእፎይታ ጊዜ (Grace
period) ሁሉ ይሰጣሉ፡፡ በውሉ የተጠቀሰው አስገዳጅ አንቀፆች ሁሉ ዋጋ ቢስ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ የሚዋዋሉት የኪራይ ውል
በውልና ማስረጃ ጽ/ቤት የተመዘገበ ላይሆን ይችላል፡፡ እየተሠራ ያለ ያላለቀ ህንጻ ሁሉ ቢሆን እንኳን ጥቅም የሚያስገኝ ከሆነ
በቁሙ በጀርባ ስምምነት ተደርጎበት የይምሰል ጨረታ ይወጣለታል፡፡
መእመናኑን
እንደ አርጩሜ መጠቀም
እነደዚህው በቤተክርስቲያን ኪራይና ተከራይ ጉዳይ የተገናኝን ተከራይ ነጋዴ የገጠመውን ሲገልጽልኝ እነዚህ በኪራይ
ስም የሚቆምሩ የቤተስኪያን ሰዎች ከተዋዋሉት ውል ውጪ እርምጃ ቢወስዱብህም በህግ እጠይቃለው ብትል የባሰ ቀውስ (chaos)ውስጥ
ልትገባ ትችላለህ፡፡ እንዴት በማለት ጥያቄዬን አስከተልኩ፡፡ የአከባባቢውን መእመናን የተለያየ ስም ለአንተ እየሰጡክ፣
የቤተክርስቲያን ጠላት እንደሆንክ አድርገው ሆ! ብለው እንዲነሱ መእመናኑ በተሰባሰበበት አጋጣሚ ይሰብካሉ፡፡ አንድ ጊዜ እኔ
እንደዚሁ ገጥሞች በስንት በመከራ በጸጥታ ኃይሎች ነው ንብረቴን ይዤ አንኳን ላወጣ የቻልኩት አለኝ፡፡
ሲጠቃለል
የማቴዎስ ወንጌል ምዕራብ 21 ቁ. 12 ክርስቶስ በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚሸቅጡትን ቤቴ የጸሎት ቤት ናት እናንተ
የወንበዴ ዋሻ አደረጋችሁት በማለት የሻጮችን ወንበር የገለጠው ለቤተክርስቲን አጥር ዙሪያ የንግድ ማዕከልነት አይሰራም ሚስጥሩ ሌላ ነው ብንባል
እንኳን(ይህ ፀሐፊ ቤተክርሰቲያን አጥር ዙሪያ ንግድ በጭራሽ ተገቢ አይደለም፡፡ ክርስቶስም ሲያወግዘው የነበረ ነው ንግድና
የአምልኮ ስፍራ ሊጎራበቱ አይችሉም ባይ ነው፡፡) የሚነገደው
ነገር የቤተክርስቲያንን ሰላምና የተረጋጋ መንፈስ የሚያውክ ባይሆን፡፡ ምክንያቱም ከቤተክርስቲያን ዓላማ ጋር የሚቀራረቡ የንግድ ተግባራት ወይም ግብረሰናይ
እንቅስቃሴዎች የሚደረግባቸው ቤቶችን ማከራየት ስለሚቻል፡፡ ቤተክርስቲያን የመልካም ስነምግባር ማስተማሪያና ማነፂያ ተቋም ናት እንጂ
የተበላሸ ስነምግባር በመንሰፈሳዊ ህይወት ጥላ ሥር ከዓላማዊ ሰዎች ባልተናነናሰ የምናይባታ መሆን የለባትም፡፡ በልብሰ ተክህኖ
ተሸልመው የቤተክርስቲያናን ሥም የሚያጠፉ ሙሰኛ ካህናት ከቤተክርስቲያን ወጥተው ወደ ምድባቸው ቢሄዱ፡፡ ቤተክርስቲያን
የመንፈሳዊ ህይወትን፣ የእግዛብሔርን መንገድ የምትሰብክ፣
የምታሳይ በመሆኗ የክፉ ነጋዴ አይነት ተግባር ቀዳዳ እየፈለጉ በተከራዮች ላይ ጫና በመፍጠር ይህችን ቤተክርስቲያን መእመናኑ እንዲያማርር
እንዲጠላት በማድረግ እንደቤተክርስቲያን ጠላት ባንሰራ፡፡ ከሁሉም
በላይ ቤተክርስቲያናችንን በውስጥና በውጭ ነጋዴዎች
ባታስወርሩብን፡፡
በዝራው አሻግሬ