የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲዋ ዘመን የጎደለባት እናት!
በአንድ የፌድራል ፍ/ቤት ሬጄስትራር
ቢሮ ለጉዳዬ ቁጭ ብዬአለው፡፡ ቢሮው ውስጥ አምስት ጠረጴዛዎች የታያሉ፡፡ የሬጄስትራር የፍ/ቤት አራት
ፀኃፊያን ሁለት ወንድና ሁለት
ሴቶች ተግባራቸው ላይ ናቸው፡፡ ሁኔታውን የምንከታተል ቢሮ ውስጥ ያለነው ባለ ጉዳዮች
ሁለት ነን ፡፡ ቀሪ ባለጉዳዮች ውጪ ይጠባበቃሉ፡፡ የፀሐፊዎች
ኃላፊ ይጣደፋል፡፡ መዝገቦችን ማገላባበጥ ፣ለባለጉደይ መልስ መስጠት፣ መጥሪያ መጻፍ ወዘተረፈ…..ሌሎች
የቢሮ ሠራተኞች መዝገቦች ጠረጴዛቸው ላይ ከምረው የየምድባቸውን ሥራ ይሰራሉ፤ ይሁንና የጽፈት
ቤቱ ኃላፊ ሥራን ያህል ድካም አይታይባቸውም፡፡ እኔና አጠገቤ ያለው
ባለጉዳይ ምናለ የዚህን ሰው ሥራ ሌሎቸ ቢካፈሉት
ብለን ተነጋገርን፡፡ ምክንያቱም ይሄ ሰው እየሠራ ያለው
የእኛንና ውጪ
ተኮልኩለው የሚጠብቁትን ባለጉዳዮቹ አሰቸኳይ ሥራ ነው፡፡ የሌሎቹ ሥራ ጊዜ የሚሰጥ ሥለሆነ ዘና ብለው ነው ተግባራቸውን ይከውናሉ፡፡ ኃላፊው በደስታ ፊቱን
ፈካ አድርጎ እጁንና አህምሮውን እያወናጨፈ ይሰራል፡፡ እኛ በቴሊቪዥን የሚታየውን ትዕይንት በጸጥታ ውስጥ እያየን አልፎ አልፎ ሁኔውን እነከታተላለን፡፡
ቴሌቪዥን ውስጥ በጩኽት የተሞላ አብዮታዊ ሙዚቃዊ ተውኔት ይታያል፡፡ ቴሌቪዝኑ አጠገብ ሌላ ክፍል የሚሠራ
የመስሪያ ቤቱ ሠራተኛ ይመስለኛል እየሳቀ የሚያናግረው ሰው አልፎ አልፎ እየቃኘ ምንድን ነው ነገሩ በሚል ቴሌቪዥኑን
ይመለከታል፡፡ ቴሌቪዥኑ ውስጥ የሀዘን እሸሩሩሩ፣ መፈክር ፣ ጩህት ፣ዋይታ ይሰማል፡፡
የግንቦት ሃያ 23ኛ
ዓመት ማግስት ነው፡፡ ሰውዬው ለራሱ ፈገግ ሲል፣ በይገርማሉ ሁኔታ ሲያይ ቆይቶ እነንዚህ ምን እያሉ ነው?! ብሎ
ድንገት ፍንቅል አድርጎት ድምጽ
አወጣ፡፡ ወዲያው ከጸሐፊዎች መካከል አንገቷን ደፍታ ስትሰራ የነበረችው
ሴት ሥራዋን አቋርጣ እኔንም የገረመኝ ይሄ ነው አለቸ! ሥራ ፈቶች በሚል የድምጽ
ቶን ስሜት፡፡ አጋጣሚውን ለመጠቀምና አብዮታዊ ዘመቻ አይነት ሁኔታ
ያለውን ዝግጅት ለማወቅ ስለፈለኩ ጥያቄ ላነሳ አፌን ሳሞጠሙጥ ከውጭ
ባለጉዳይ ገብቶ ልጅቷን አናገራትና እኛም ዝም አለን፡፡ በቴሌቪዥኑ
ውስጥ ያለው ጩኽት ይረብሻል፡፡ በቢሮው ውስጥ አንድም ሠራተኛ ጥሞት እንደማይሰማ በእርግጠኝነት መናገር እችላለው(
የማይሰማ ያልኩት አንድ አንዴ ብራቅ ሲሰማ ቀና ከሚል በስተቀር ቴሌቪዥኑን
የሚከታለለው ስላላየው ነው፡፡)ለምን ቴሌቪዥኑ አይዘጉትም ብዬ ጠየኩና ትዕዛዝ ሊሆን ይችላል በማለት ለራሴ መልስ ሰጠሁኝ፡፡ ባለጉዳዩ
ጉዳዩን ጨርሶ ሲወጣ አፌን አሞጥሙጬ ለመጠየቅ ያሰብኩትን ጥያቄ የምን ዝግጅት
ነው? ብዬ በመጠየቅ የተቋረጠውን ለማስቀጠል ሞከርኩ፡፡ የቅድሟ ተናጋሪ
ቀና ብላ አየችና በተኮሳተረ ሁኔታ ማንን ልታናግር ነው!
በሚል ስሜት አይታ ወደ ሥራዋ ተመለሰች፡፡
ሌላ ሰውም
የመለሰልኝ አላገኘሁም፡፡ አሁን ተጨማሪ ጥያቄ
ማንሳት ጠቃሚ እንዳልሆነ አሰብኩ፡፡
እሁድ ዕለት
ረፋዱ ላይ ቴሌቪዥን ስከፍት ፍርድ ቤት ያየሁት ሙዚቃዊ ቲያትር በድጋሚ ለማሳየት ሲጀመር ደረስኩ፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቲያትር
ጥበባትና የአዲሰ አበባ የባህል ማዕከል ባለሞያዎች በጋራ ያዘጋጁት
ሙዚቃዊ ቲያትር ነው፡፡ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቲያትር ጥበበባት ዲፓርተመንት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ልማታዊ ቲያትሮች ለመስራት ቆርጦ የተነሳ መሆኑንን ከዚህ በፊት የዲፓርትመንቱ ዲን የሆኑት አርቲስት ነብዩ ባዬ
በሚዲያ መግለጻቸው ትዝ አለኝ፡፡ ይህ ዝግጅት እንግዲህ የእዛ አካል መሆኑ ነው፡፡ አሁን አሁን የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቲያትር ዲፓርትመንት ከወጣቶችና ህፃናት ቲያትር
ት/ቤት በመቀጠል ፕሮፓጋንዳ ቀመስ መዝሙርና ቲያትሮች መስራት የዲፓርትመንቱ አካል ማድረጉ በተለያየ አጋጣሚ በቴሌቪዥን የምናያቸው ዝግጅቶች ያሳዩናል፡፡
በአዲስ
አበባ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ የመንግስት ቲያትር ቤቶች ፕሮፓጋንዳዊ ቲያትር መስራት የቲያትር ቤቶች አንደኛው ዓላማቸው መሆኑ ቀደም
ሲል በነበረው የደርግ መንግሰት በቀበሌ፣ በከፍተኛ ኪነት ቡድን ጎን ለጎን ሲከናወኑ በነበሩ ዝግጅቶች አሁንም የኢአህዴግ መንግስት ልማታዊ
ቲያትና ድራማ ጻፉ፣ተውኑ፣አዘጋጁ በማለት በሥሩ ለአሉ አርቲስቶቹ ከሚሰጠው የግዴታ አብዮታዊ ሥራ ጀምሮ የተለያዩ ክብረ ባህሎችን
ምክንያት በማድረግ የሚሰሩ የዘመቻ ዝግጅቶች ጥሩ ማሳያዎች ናቸው፡፡
እነዚህ ብዙ ተለመዱ መመድረኪያ ሥፍራዎች ናቸው፡፡ ባልተለመደ
መልኩ አብየታዊ ምድረካ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቲያትር ጥበበባት ዲፓርትመንት እንደ አንድ ኮርስ አልያዘውም ለማለት ይቸግረናል፡፡
በተለይ ከረዳት ፕሮሴፈር አቦነህ አሻግሬ የዲፓርትመንቱን ዲንነት ስልጣንን አቶ ነብዩ ባዬ
ከተረከቡ በኃላ የድሮዋን ኪነት ተማሪዎቻቸውን በማሰለፍ
ደፋ ቀና ሲሉ አይተናል፡፡
በመድረኩ
ላይ የተለያየ የብሔር ብሄረሰብ አልባሳት ለብሰው በደርግ ጊዜ ዘመን
የጎደለባት እናት እያሉ እሹሩሩሩ፣ራበን እያሰባሉ ሙሾ ሲያስወርዱ ፣መሬት
ላይ ቁጥራቸው ከ30 የሚበልጡ ወጣት ተዋንያኖቾን ሲያንከባልሉ፣ህበረ ዝማሬ ሲያሰሙ፣ አብዮታዊ መፈክር ሲያሰደምጡን፣ ኢትዮጵያን የወከለቸው ሴት በሰዎቹ መሃል እየተዘዋወረች
እሹሩሩሩ! እያለች የሀዘን እንጉርጉሮ ስታሰማን ቆይቶ የብሶት
የወለደው ኢአህዴግ ዘመን ተተክቶ እልልታ ደስታ፣ የብሔረ ብሔረሰብ
ዘፈን፣ አባይ፣ ሰላም ካለ ብዙ እናያለን፣ ወዘተ…. ያች
በደርግ ዘመን እሸሹሩሩ ስትል የነበረች ሴት
በደስታ ፈክታ ባንድራ ለብሳ ልጆቿን ብዙ እናያለን ስትል፣ የዛሬ
ሃያ ዓመት በድሎት እንኖራለን ብለው
ሲነግሩን ኪነት ከ20 ምናምን ዓመት በኃላ ተመልሳ መጣች እንዴ ብሎ ለመጠየቅ እምብዛም አስተዋይ መሆን አያፈልግም፡፡
የዕለቱ
የክብር እንግዳ አቶ ሬድ ዋን ከተመልካቹ መሃል ተነስተው የቀረበውን ሙዚቃዊ ድራማ በማድነቅ የነበረውን ሁኔታ በሚገባ ገልፃችሁታል በማለት በማንቆለጳጰስ፣ በንግግሬ ሥራችሁን እንዳላበላሸባችሁ
በማለት ንግግራቸውን ቀጠሉ፡፡ዝግጅታችሁን እነዳለበላሸባችሁ ሲሉ ፕሮፓጋንዳ
አልጨምረም የሚሉ መስሎኝ ስጠብቅ የተለመደ ፕሮፓጋንዳዊ ንግግራቸውን በእናንተ ቅቡልነት ከአገኘን፣ የምንጋግረውን ኬክ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ
እንዲደርስ እንሰራልን!( በሆዴ ቂጣ በተገኘ አልኩ)ወዘተ.. የሚል ፕሮፓጋንዳ ሲያደርጉ ምኑን ነው እንዳላበላሽባችሁ
ያሉት አልኩ፡፡
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቲያትር ጥበባት በደራሲ መርሻ፣
በአርቲስት ነብዩ ባዬ አዘጋጅነት
በልማታዊ
ቲያትር ስም ይህንን ፕሮፓጋንዳ ሲሰራ በአእምሮዬ ውስጥ አንድ አንድ ጥያቄዎች
ድቅን አሉብኝ፡፡
ጥያቄ አንድ ፡-
የቲያትር ዲፓርትመንቱ የመንግስት ፕሮፓጋንዳ ሥራ ሲሰራ የትምህርት
ተቋሙ ከፖለቲካዊ ዘመቻ ገለልተኛ
አለመሆኑን የሚያሳብቅበት አይመስለው ይሆን?
ጥያቄ ሁለት፡- የቲያትር ጥበብ ለመቅሰም የመጡ
ተማሪዎች ከመጡበት ዓላማ በተቃራኒ የፕሮፓጋንዳ መሳሪያ ሲሆኑ ፍቃዳቸው ተጠይቆ ይሆን? (እዚህ ላይ በእንቅስቃሴው የማይሳተፉ ትምህርታቸውን መቀጠላቸው አደጋ ላይ የመውደቅና የትምህርት ውጤታቸው ላይ ችግርም ሊፈጠር እንደሚችል
በመገመት በማወቅ ሳይወዱ በግዳቸው የሚሳተፉትን ከግንዛቤ በማስገባት ነው፡፡)
ጥያቄ፡- የትምህርት
ተቋሙስ የተወሰነ ቡድን አቋም ይዞ ኪነታዊ ሥራ መሥራት
ከመማር ማስተማሩ መርህ ውጪ መሆኑንና አካዳሚካል ነፃነት የሌለውም መሆኑን አያሳይም?
እነዚህን ጥያቄዎች ሳነሳ ዩኒቨርስቲው
ውስጥ ቁጥራቸው ቀላል ያልሆነ የኢአህዴግ አባልና ካድሬዎች መማር
ማስተማሩን አይዘውሩትም ብዬ አይደለም፡፡ በዲንነት በትምህርት
ክፍል ኃላፊነት፣ በአስተዳደርነትና በተለያየ ኃላፊነት የተቀመጡ ሰዎች
አባሎች አይደሉም ብሎ በዋዛ ፈዛዛ ማየት ሞኝነት ነው፡፡ በተለይ እንደዚህ አለን አለን የሚሉት የካድሬነት ሚና ጭምርም አላቸው፡፡( ከሲስተሙ እየታገሉ ሞያቸውን ብቻ የሚሰሩ
ንጹሁ ሙሁራኖች መኖራቸውን እንዳትዘነጉብኝ፡፡)
ሲጠቃለል
ቢያንስ
ቢያንስ የትምህርት ተቋማት አካዳሚካል ነጻነት እንዲኖራቸው ብታደርጉልን! የቲያትር ጥበባት
ዲፓርትመንት የፕሮፓጋንዳ ሥራውን ለመንግስትና ለኢአህዴግ ፕሮፓጋንዳ ክፍሎች በመተው ንጸሁ
የአካዳሚክ ተግባር ቢሰራበት፣ በተለያየ መደብ ላይ ያለችሁ ካድሬዎችም የመማር ማስተማሩን
ሂደት ባታውኩት፣ ዩኒቨርሰቲው ለረጅም ጊዜ ይዞት የመጣውን አንጋፋነት በፖለቲካዊ አስተሳሰብ እየቃኛችሁ ደረጃውን ዝቅ ባታደርጉ፣
ኢአህዴጋዊ አስተሳሰቦችን ከዩኒቨርሰቲው ውጪ ብታደርጉ፣
ከተቋሙ ወጥታችሁ ለዚህ ሥራችሁ የሚረዳችሁ የመንግሰት
መዋቅር ውስጥ ብትገቡ ውጤታማ ሰለምትሆኑ ተቋሙን ለባለሞያዎች
ብትተው፤ ዘመን የጎደለባት እናት እያላችሁ
እግራችሁ ሥር ያለውን እውነት እንዳላየ በማለፍ ከሞተ ሥርዓት ጋር የማይወዳደር እያወዳደራችሁ ለመንበር ፍለጋ ጊዚያችሁን ባታባክኑ፣
አይናችንን ባታደክሙ እያልን በልማታዊ
ቲያትር ሥም በማክበር እንጠይቃለን፡፡
በዝራው አሻግሬ