መንበር
ናፋቂ ከያኒዎች!
Zirawashagre@yahoo.com
ክፍል -፫
ባለፈ ክፍል-፪ የመንበር ናፋቂ ከያኒዎች ባህሪና ተግባራቸውን ባሳየሁበት
ጹህፌ፤ ጹህፉን የተመለከቱ አንባቢያንና ጋዶኞቼ በኤሜልና በስልክ
የተለያየ አስያየት ጹህፉን በተመለከት ሀሳባችሁን ሰጣችሁኛልን፡፡ ሁላችሁንም አከብራችሁኃለው እወዳችሁለው፡፡ ከተሰጠኝ
አስተያየቶች አንድ ሁለቱን ላንሳና መልስ ሰጥቼ ወደ ክፍል-3 እና የመጨረሻ ጹህፌ የሆነው መንበር ናፋቂ ፀሃፍት ባህሪና
ተግባራቸው አመራለው፡፡
ከተሰጡኝ አሥተያየቶች ተደጋጋሚው ማንነታቸውን በደምብ ቁልጭ አድርገህ አሳይተህናል
ብዙዎቹ እነማን እነደሆኑ የምንገምተው ነገር ቢኖርም ምን አለ በነካ እጅህ አካፋን አካፋ ለማለት እንዲረዳን ስማቸውን ብትገልጽና
ግምታችንን እርግጠኛ አድርገን ባገኘነው አጋጣሚ ክብር ለሚገባቸው ክብር ይገባሃል!ክብር ይገባሻል! ብንል ፡፡ ክብር
የማይገባቸውን ደግሞ እናንተ የተሰጣችሁን ክብር የተንዘላዘላችሁበት! በእጃችን መዳፍ ሥር ነው
ያላችሁት እንደ እንቁላል በእንክብካቤ እነደያዝናችሁ አፍርጠን ጥለናችሁ ማጠፊያው እንዳያጥራችሁ ብንላቸው የሚልና ሌላው ደግሞ
ብዙዎች እያዩ እየሰሙ እንዳልሰሙ፣እንዳላዩ ዝም ብለው ያለፉትንና አትንካን አልንካህ በሚል የሚሞዳሞዱበትን ጉዳይ አፍረጥርጠህ
ልባችንን አርሠከዋል! የዜግነትህን አድርገሃል! በርታ የሚል
ነው፡፡
የእኔን
ሀሳብ ስገልጽ፡-
መንበር ናፋቂ ሁኔታውን
በቅርብ እኔ የማውቀው፣ አንባቢያን የሚገነዘቡት እንዲሁም መረጃዎቹ በቅርቤ ያለና በአደባባይ የተፈጸሙ ጉዳዮች ላይ ተመስርቶ የተጻፈ ጹህፍ ነው፡፡ ስለዚህ አካፋን አካፋ ለማለት ምድብ አየሰጠን የገለጽናቸውን ከያኒያን በስም
እየጠቀሱ የለየላቸውን ምስላቸውን በማሳየት ማንነታቸውን ለማሳየት ችግር ኖሮብኝ ሳይሆን እነዚህ ከያኒዎች ሆን ብለው ይሆን
ወይም በግዴለሽነት የሚያደርጉት ተግባር እንደ የጥበብ ባለሞያ ለራሳቸው ቦታ ሰጥተው ከጋደኞቻቸው ተመካክረው በሰከነ መንፈስ
እያደረጉት ያልሆነሊሆን ስለሚችልና የማስተማሪያ ጊዜ ወይም የማሰላሰያ ጊዜ(Grace period) ሳይሰጡ በሚደያ ላይ ቀጥታ
ስማቸውን መግለጽ ስሜታቸውን ይጎዳል በሚል ታሳቢነት፣እንዲሁም የሚዲያ አንደኛ ተግባሩ መረጃ መስጠት ስለሆነ፤በአንፃሩ ደግሞ ህብረተሰቡም
መረጃ የማግኘት መብት ያለው ስለሆነ ይህንን እየቀላቀሉ
የሚጫወቱትን ጨዋታ በስም እየጠቀሱ ለህብረተሰቡ መረጃ ለመስጠት ወደፊት ጊዜ ስላለን ለጊዜው ይቆየንከሚል ስሜት የተነሳ ሲሆን፤
በሁለተኛ ደረጃ የዜግነትህን ሰርተሃል በሚል የተጠቀሰው ማንም ሰው መልካም ያልሆነ ተግባር ሲያስተውል መልካም ተግባር የማይሰራውን
ሰው መገሰጽ፣ ማሳየት ማስተማር አለበት ባይ ነኝ፡፡ አለበለዚያ እነዚህ ለህሊናቸው ያላደሩ በተጨማሪም የራሳቸውን አድናቂዎቸ
እንደ ጅል አይናችሁን ጨፉኑ ላሞኛችሁ ለሚሉ ሰዎች ፊት
ከተሰጣቸው የአድናቂዎችቻቸው ጭንቅላት ላይ አይወጡም ማለት አስቸጋሪ የሚሆን ሲሆን የከያኒነት ሞያ ከፖለቲካ ሥራ ጋር ተደበላልቆባቸው አንድአንድ ከያኒዎች
የፖለቲካ መሪነትን ሠራ እንሰራለን በማለት የፈጠሩትን ኪሳራ እነዚህም እየደገሙ በመብታችንንና በሞራላችን ላይ ጥባጢቤ እንዳይጫወቱ መጠንቀቅ የግድ
ነው፡፡ የዚህ ጹህፍ ጸኃፊ የኢህአዴግ አባል ሆነካድሬ መሆን
አጢያት ነው ብሎ አያስብም! ይሁንና ለከያኒዎች መሞዳሞድ፣የካድሬ ሥራና የጥበብ ሥራን መቀላቀል ትክክል አይደለም ቢቻል
የኪነጥበብ ሰዎች የተቃዋሚም ሆነ የገዢው መንግስት ፓርቲ አባል መሆንም ወይም መወገን የለበትም ብሎ ያስባል፡፡ በነፃነት የህዝቡን ስሜት ማስተጋባት ብቻ ሥራቸው ቢሆን ይላል፡፡ በእርግጥ ከያኒያን ወይም የጥበብ ሰዎች የመንግስታቸው አስተዳደር ወይም ፖለቲካ
አይመለከታቸውም ወይም ፖለቲከኛ መሆን አይችሉም የሚል ህግ ሆነ ሥርዓት የለም! ወደ እውነታው ስንመጣ ግን መንግስት ይቀየራል፣
ፖለቲካም ይቀየራል፣ ፖሊስም ይቀየራል፣ ፓርቲም ይቀየራል፣ሥርዓትም ይቀየራል መሪም ይቀየራል፣ ፊተኞችም ዃለኛ ይሆናሉ ዃለኞችም
ፊተኞች ይሆናሉ፡፡ ይሁንና የጥበብ ሰው፣ ከያኒ መተባበር ያለበት ከእውነት ጋር ነው፣ መስራት ያለበት ጊዜ ዘለል የሆነ ስራ
እንጂ የጨበሬ ተስካር አጃቢነት ወይም ጨፋሪ መሆን የለበትም፣ ከያኒ የወጣበት ህብረተሰብ ስሜት ቁስል ችግር ብሶት ሊሰማው
ይገባል፣ እነደ አምባገነን መሬዎች አይሰማም! በማለት በህብረተሰቡ ቁስል ውስጥ እንጨት አይሰድም እነደዚህ የሚያደርግ ከያኒ
ከያኒ ወይም ጥበበኛ ሳይሆን ጨቃኝ ገዢና የጨካኝ ገዢዎች ጋሻጃግሬ ነው፡፡
መንበር ናፋቂ
ፀኃፊያን ፡-
እነዚህ ጸኃፊያን ወደ መንበር ናፋቂነት ያካተትናቸው የሚጽፉትን ጹህፍ
ወይም ድርሰት እና የሚያሳዩትን ዝንባሌ በማስተዋል
ነው፡፡ ፀሐፊዎቹ የግጥም ደራሲ፣የቲያትር ደራሲ፣ የፊልም እስክሪፕት ፀኃፊ፣የቴሌቪዥን ድራማ ፀኃፊ
፣የመጽሐፍ ፀኃፊ ወዘተ .. ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በአብዛኛው የእነዚህ መንበር ናፋቂነት ብዙ ጊዜ ለመንበር ሲያሳጫቸው አይታይም፡፡
ይሁንና መንበር ሊያሰጥ የሚያስችል ሥራ እየሰሩ በርካሽ ተወዳጅነትና በቀላሉ ገንዘብ ይሰራሉ፡፡በክፍል አንድና ሁለት ጹህፌ ላይ
እንዳደረኩት ለእነዚህም መደብ በመስጠት ተርታ ብናሲይዛቸው በቀላሉ ለማስረዳት ይቻላል፡፡
1ኛ. መሰረታዊ ዓላማ ያላቸው ኢአዴግ መር ፀኃፊያን፤
2ኛ. አጋጣሚዎችን የሚጠቀሙ ወይም አጋጣሚ የሚፈጥሩ ከታፊ ፀኃፊያን፡፡
1. መሠረታዊ ዓላማ ያላቸው ኢህአዴግ መር ፀኃፊያን፤
በዚህ ተርታ ውስጥ
ያሉ ጸኃፊያን በግልጽ የኢህአዴግ አባል የሆኑ ወይም
የተወሰነ የኃላ ታሪካቸው ቢመረመር የኢህአዴግ አባልነት ንክኪ ያላቸው ምንአልባት ፈልገውም ይሁን ሳይፈልጉ ከድርጅቱ
የተፋቱ ይሁንና የጋብቻ ወረቀታቸውን ያልቀደዱ ሆነው ከግምገማ ከሂስ ግለሂስ፣ ከድርጅት ጋዜጣ ግዙ፣ከድርጅት መዋጮ ወይም
ከንቅናቄ የተገላገሉ፤ ለእናት ድርጅታቸው በውጪ ሽፋን በመስጠት አብዮቱ እንዲቀጥል አባል ነኝና ትቼአቸዋለው በሚል ሁለት
አይነት መጫሚያ በማድረግ የማያቀቸውንና አዘቅዝቆ የተጫሙትን ጫማ ላላስተዋለ ለማደናገር የሚሞክሩ እነርሱን ለማወቅ ግን ብዙ
የማያለፉ! መርገጫቸውንብቻ ማየት በቂ የሆነ ፀኃፍያን
ናቸው፡፡
ቲያትር ከፃፉ፤ቲያራቸው ላይ በቀጥታ የሚሰለች የድርጅት ፕሮፓጋዳ
የሚነፉ፣ኪራይ ሰብሳቢነት፣ ልማታዊ ባለሃብት፣ባለፈው መንግስታት የተፈጸሙ አስከፊ ድርጊቶችን ደጋግመው በመተረክ አሁን ያለው
መንግስት ወደር የማይገኝለት መሆኑን በድፍረት በቀጥተኛ ቋንቋ ይናገራሉ፡፡ ፊልማቸው አስፈላጊው የፊልም ግበኣትንና ከፍተኛ
በጀትን(በጀታቸው በቀጥታ ወይም ቀጥተኛ ባለሆነመንገድ በተለያየዘዴ ከመንግስትካዝና የሚወጣ ሊሆን ይችላል )በመጠቀም ፊልሙ
ትኩረት እንዲያገኝ ያደርጋሉ፡፡ በፊልማቸው ላይ የሚያነሱት የደርግ መንግስት በአገዛዝ ዘመኑ የሠራውን አንኳር ስህተት ወይም
ኪሳራን እየመነዘሩ የህዝቡን ቁስል በእንጨት ጎርጎር፣ጎርጎር በማድረግ ለማመርቀዝ በመሞከር ኢህአዴግ መራሹ መንግስት የነብስ
አባት መሆኑን ያሳያሉ፤ ከኢህአዴግ በላይ ተዋጊ ላሳር የሚል አድቬንቸር ፊልም ይሠራሉ፤ ቢፈልጉ በገፀ-ባህሪያቶቻቸው አሊያ
በፊልሙ ታሪክ ይዘት፤ የቀድሞው መንግስት የሰራው ግፍ ቀላል ያልነበረ መሆኑን የዛሬ አገዛዝ ዓለም ነው የሚል መንፈስ ያለው፣ ይህ
ነፃነት በዋዛ እንዳልተገኘ፤ በዋዛ ሥልጣንም አንደማይለቀቅ እንድምታ ያለው ሁኔታ ያሳያሉ፤ ለፊልማቸው ግብዓት ኢቲቪን ሆነ
በአገሪቱ አሉ የተባሉ የመንግስት አርካይቮችን እንደ እናታቸው ጋዳ ያለምንንም አዛዥና ናዛዥ ይበረብራሉ፤ የቀድሞ መንግስት ሆነ
የአሁኑ መንግስት ወታደራዊ ሆነ የሲቭል ሎጆስቲክን ይጠቀማሉ፡፡ መጽሐፋቸው
ለይ ልቦለዳዊና ኢልቦለዳዊ በሆነ መልኩ የተለመደ ደርግን ጭራቅ አድርጎየመሳልና ኢህዴግ መራሹን ቡድን መላህክት
አድርጎ የመተረክ ሥራቸውን ይሠራሉ፤የአሳታሚ ችግር የለባቻውም፤ የህወአት ካምፓኒዎች ናቸው በሚባሉ ድርጅቶች በፍቃደኝነት በይፋ
ወይም ይፋዊ ባልሆነመንገድ ይታተምላቸዋል፤ ወጣ እንባል ብለው ካሉ የኢህአዴግ አባል ወይም ደጋፊ የሆነ ባለሀብትን ወጪውን
እንዲሸፍን ያደርጋሉ፤ አሊያም በፍርሃት የሚዋዝዥቀውን ግራ የገባው ገለልተኛ ባለሃብት የመጽሐፉን ኣላማ እነማን የመንግስት ከፍተኛ
ባለስልጣኞች የድጋፍ ደብዳቤ እንደፃፉለት በማሳየት መደበኛ ባልሆነ የማስገደድ ተግባር እነዲታተምላቸው ግፊት ያደርጋሉ፣ በሬድዮ
ወይም የቴሌቪዝን ከፍተኛ የዜና ዘገባና ፕሮግራም ምክንያትእየተፈጠረ በሰፊ ሊሰራላቸው ይችላል፡፡ የመንግስትና የድርጅት
የህትመት ውጤቶች ለተወሰነ ጊዜ ሥራቸው ሥለመጽኃፋቸው ገራሚነት መቦትለክ ይሆናል፡፡ የግጥም መድበል ከሆነጹህፋቸው ተዓምር
እነደሰሩ በመንግሰት አዳራሾች የተለያየ የመንግስት ባለሥልጣኖችን፣ ከያኒያንና ሥመጠር ሰዎችን በመጥራት ያዙኝ ልቀቁኝ ይላሉ፤
የጹፋቸው ጨብጥ ከላይ ከገለጽኩት ውጪ እምብዛም አይሆንም፡፡
ምንዓልባት ለየት የሚያደርገው አይን ውስጥ የገባ ወይም በህይወት የሌለ የነባር ታጋይ ግለሰብን የሚያሞካሽ ይሆናል፡፡ ልክ
አሁን እንደምናየው የመለሰ ዜናዊ የቀብር ሥነሥርት ወይ ሙት ዓመትን የመሰለ ነጥብ የማስመዝገቢያ መልካም አጋጣሚ ካገኙ
እየዘለሉ እየተወራጩ ፊታቸውን ቀጨም ለቀቅ፣ እንባቸውን በጉንጫቸው ላይ እያፈሰሱ(እንባቸው በእርግጥ ለጠ/ሚኒስትሩ የሚፈስ
ዓለመሆኑን እኛም እነሱም እናውቃለን፡፡) ለአነባበባቸው የመፈክር ፣የእንጉርጉሮ፣የዛቻ ድምጸት እየሰጡ ድርሰታቸውን በትወና ያሳዩናል፤ለመጽሃፍ ምረቃቸው ከጋበዙአቸው ስመጥር
ከያኒያን ከመድበላቸው ውስጥ እንደቅርጫ እያከፋፈሉ የስመጥሩን ከያኒ ክብር ወደ ራሳቸው ለማጋባት ይሻሉ፣ሥራቸው የህዝብ ድጋፍ
እንዳለው ለማስመሰል ይሞክራሉ፡፡ የቴሌቪዥን ድራማ የሚጽፉ ከሆነሲጀምሩ የህዝቡን ቀልብ አፈፍ አድርጎ ለመሳብ የሚረዳቸውን ማሀበራዊ
ጉዳይ በማንሳት ለስለስ አድርገው ይገቡና ሰውር በሆነ ስልት የመንግስትን ፖሊሲ ይሰብካሉ፤የአፈፃፀም ችግር ነው አይነት
የመንግስት ጉንጭ አልፋ ወሬ ቀጥተኛም ሆነቀጥተኛ ባልሆነመልክ
ሲሰብኩ ይታያል፡፡ በተጨባጭ የሚታይ የህብረተሰቡን ችግር ባለፉ በአገደሙበት እያዩ ለመንግስት ፖሊሲ ይረዳል ብለው ካላሰቡ
ብዕራቸው አይጽፍላቸውም፤ የመንግስት አገልግሎትን በአብዛኛው እንከን የለሽ አድርገው ያሳያሉ፣በሆነ የመንግስት አጀንዳ ላይ
ወቅታዊ መጽሄት ሰርተው በየመንግስት ቢሮ የሚመለከተውን ኃላፊ በማነጋገር ወይም ከላይ ለመጽሀፍ ደራሲዎች በገለጽት መልኩ
በስፖንሰር ከፍተኛ ገንዘብ ይሰበስባሉ ፡፡
እነዚህ
ኢህአዴግ መራሹ ፀሐፍት በተለይ በአባልነት ላይ ያሉ መንበር ያላቸው ሊሆኑም ይችላሉ ይሁንና በሚያሳዩት ትጋት በተለያየ
ምክንያት ያላገኙትን የተሻለ መንበር ለማግኘት ነው የሚንቀሳቀሱት ምናልባትም ነባር አባላት ከሆኑ የፕሮፓጋንዳ ጹህፎች በመፃፍ
ረጅም ጊዜ ልምድ ያካባቱ ናቸው፡፡በነገራችን ላይ የመራሾቹ ጹህፍ በየትኛውም መድረክ እነደ የበቃና እነከን የለሽ ሥራ
ስለሚወሰድ የድርሰት ግምገማ አያሳጋቸውም! ተጨማሪ ሀሳብ የሚሰጥ እንጂ ደፍሮ የሚገመግማቸውም ገምጋሚም የለም፡፡
አንድ
ጊዜ አንድ የመንግስት መ/ቤት ለሥራ ጉዳይ
ሄጄ የሥራ ኃላፊውን ለማነጋር ቢሮው ሥገባ ኃላፊው ስልክ ድንገት ተደውሎለት በእጁ ምልክት ቁጭ እንድል
ጋበዘኝና ቁጭ ብዬ ቢሮውን ስቃኝ ቆይቼ ኃላፊው ስልኩን በቀላሉ መቋጨት የሚችል አለመሆኑን ስገነዘብ ፊት ለፊቴ ያለባለመስታወት
ጠረጴዛ ላይ የተዘረሩትን መጽሔት ሳይ አንድ ባለ ሙሉ ቀለም ህዳሴ የሚል ርዕስ ያለው መጽሄት አየውና መዘዝ ሳደርገው እጄን ከበደኝ፤የገፆቹ
ብዛትን ሳየው መጽሄት ለማለት ተቸገርኩ፤ መፅሐፍ እንዳልል ደግሞ የመጽሄት ሌይ አውትና ፎርማት ነው ያለው፡፡ ከአንድ መቶ ገጾች
የማያንስ መሆኑና ባለ ሙሉቀለም ወፍራም ገጾች ያሉት መሆኑን
አስታውሳለው፡፡ ተገርሜ የመጽሃፉን የመጀመሪያ ገጽ ስገልጽ አዘጋጅ ብሎ የማውቀው ጋዜጠኛ ፎቶ ሱፍልብስ በከረቫት ገጭ አድርጎ አየሁ፡፡
ግርም አለኝ ይህንን ሰው የዛሬ አሥር ዓመት
በአገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያ ማስሚዲያ ማሰልጠኛ ማዕከል በሚል ጋዜጠኝነት በከፍተኛ ትምህርት ደረጃ ሲሰጥ
አብረን አንድ ክፍል ውስጥ የህትመት ጋዜጠኝነት(print jouranalism)ተምረናል፡፡ በቴሌቪዝን መስኮት ላይ አልፎ አልፎ
አየዋለው፤ በአካልም አንዳንዴ መንገድ ላይ ስንገናኝን እረ አንተ ሰው ይሄ ….. ተጠቀመው ባክህ ጡር ነው ይለኛል፡፡ በቅርብ
ጊዜ እይኔ እያየ በኢኮነሚ ሽቅብ ሲሸቀናጠር አስተውያለው፡፡ፌቴን
በገረሜታ ፈገግ አድረጌ መጽሄትና መጽሐፉ መሳዩን ጥራዝ እየገለጥኩ አየው፡፡
አቤት ፕሮፓጋንዳ! አቤት ድርሰት! አቤት ጥምጠማ!አቤት ስፖንሰር! ያላማጋነን ጥሩ ገንዘብ እንደተሰራበት ለመረዳት
የሽያጭ ሙያ ኤክስፐርት መሆንአያስፈልግም፡፡በሆዴ እንዲህ ነው እንግዲህ ህዳሴ፣የኣባይ ግድብ፣ንቅናቄ፣ጂኒቁልቋል ብሎ ገንዘብ
ሥራ አልኩኝ!!
2.አጋጣሚዎችን
የሚጠቀሙ ወይም አጋጣሚ የሚፈጥሩ ከታፊ ፀኃፊያን
እነዚህ ይፋዊ
በሆነሁኔታ የድርጅት አባል አይደሉም፡፡በአብዛኛው ዓላማቸው በኢኮነሚ የዳበረ ሰው የሚሆኑበትንሁኔታናቀዳዳም ከተገኘ
ጭራቸውንቆልተው የድርጅት አባል መሆንየሚጠበቅባቸው ከሆነእንደ ገለልተኛ ሰው አክት ሲያደርጉ የነበሩትን ጊዜ ከነአካቴው ረስተው
መንበር ላይ ቁጢጥ በማለት በተሰጣቸው መንበር ላይ ሆነው መግለጫ ሁሉ ሲሠጡ ቤቴሌቪዝን መስኮት ልናያቸው በሬድዮ ልናደምጣቸው
እንችላለን፡፡አንዳንዶቹ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ በብዕራቸው መንግስትን ሲያወግዙ የነበሩ ነገር ግንየያዙትአቋም
በኑራቸው ላይ ለውጥ እንዳላመጣ ሲረዱና ምንም ለውጥ አይመጣም ብለው ሲደመድሙ ከመሸ ወደ ጎራው ለመቀላቀል ብዕራቸውንና አፋቸውን አሹለው እንደ የኢላማ
ጥይት ለመተኮስ ዝጉጁነታቸውን የሚያሳዩ ናቸው፡፡የህነዚህ ብዕር የሚያተኩረው በዋነኝነት የመንግስት ወቅታዊ አጀንዳዎች ላይ
ብዕራቸውን በመቀሰር በከፍተኛ ባለስልጣኖች ፕሮፋይላቸው መገንባት እግረ መንገዱንም ገንዘብ የማካበት ሥራ ነው የሚሰሩት፤
የህዝቡን ሀሳብ የሚያስቀይሱ ወይም በዋዛ ፈዛዛ ፌዝ አዘል ድርሰታቸው ህዝቡ ስለችግሩ እንዳያስብ መፍትሄ እንዳይፈልግ
የማደንዘዝ ሥራም ስልታዊ በሆነ ሁኔታ ይሰራሉ፡፡ በሆነ የመንግስት ዝግጅቶች ላይ የጫጫሩትን ይዘው እየተንጎራደዱ፣ ማልቀስ
አስፈላጊ ከሆነ እያለቀሱ ግጥም ሊያነቡ፣ መነባንብ ሊያነበንቡ፣ ቅኔ ሊቃኙ ሁሉ ይችላሉ፡፡ እነደዚህ፡-
ይይ….መለስ
አባታችንመሌ…
የሥራ ባተሌ
የኛ ባለመላ
ድንገተኛ
ደራሽ
የወደቀ
አስታዋሽ
ያላአንተ
ማን አለ
ለአገር
የታገለ፤
ደህነትን
ተረት አድርጎ የሄደ
በአመነበት
መንገድ በርትቶ የነጎደ
የኛ ሁሉን አወቅ…
ፈጣሪችን
እሱ፣
ቀያሻችን
እሱ፣
ፈጻሚያችን
እሱ፣
ገምጋሚያችን
እሱ፣
ቃላችንም
እሱ፣
እረ
ፈጣሪያችን….. (የእሪታ መንፈስ አለው)
ይ-መለስ
ይይይ..መለስ……… (ቃላቱ ተረግጦ አንጀቴ አረረ ስሜት አለው)
ት….መለስ!
ያች ነፍሱ!!........ (የእርካታ አይነት ምናልባት የማች
ፎቶ በእጁ ካለ ወደ ሆዱ ወሽቆ ወደ ሆዱ ውስጥ ለማስገባት ባለ
ሁኔታ
ነው)
የጠቅላይ
ሚኒስትሩን ወይም የደህንንት ኃላፊውን የሚወክል ድረሰት ጽፈው ባለፈ ጊዜ ስለ መንበር ናፋቂ ተዋንያን ሳነሳ ስለ ህዝብ፣ ስለ
ስም መጠልሸት፣ ስለ ህሊናዊነት ግድ የሌላቸው እውቅናና ገንዘብ ብቻ ወደፊት የሚሉ በሚል የገለፅኳቸውን ያልበሰሉ ተዋናዮችን በማሰተውን
ነጥብ ያስመዘግባሉ፡፡ ወደ መንበር መጠጋጋታቸው የሚጀምረው የተለያየ የመንግስት ክብረ በዓል ሰበብ ዝግጅቶች ላይ ኮሚቴ
፣አስተባባሪ በመሆን ሲሆን የቀደሞ ድርሰታቸውን እውቅናቸውን እንደ ቀብድ በማስያዝ ነው፡፡ ሲያሻቸው ከእነእርሱ በላይ ፀኃፊ እንደለሌ ባገኙት
መድረክ ሊገልጹ ይችላሉ፡፡ በኮሚቴ የሚሰሩ ልቦለዳዊ ወይም ኢልቦላዲዊ ለማለት የሚያሰቸግሩ መጽሀፍቶች ላይ አዋቃሪ ወይም
አጠናቃሪ ፀሃፊ እየሆኑ በመስራት ወደ መንበረ ጠጋጠጋ ይላሉ፡፡ የሚታወቅ ወይም ወጥ ሥራ በህዝቡ ውስጥ አስመዝግበው
ካልሆነትናንሽበትህዛዝ የሚሰሩ የፕሮፓጋንዳ ድራማዎች የማስታወቂያ ስፖቶች በመስራት አጋርነታቸውን የሚያሳዩበት አጋጣሚን ያድናሉ፡፡አነስተኛ መጠንያለው
የግጥም መድበላቸውን እነደ የጸኃፊነት ማረጋገጫ ሰርትፍኬት ያቀርባሉ፡፡
ይድረስ ለመንበር ናፋቂ ከያኒያን!
እስቲ የትኛው ከያኒ ነው ህብረተሰቡንአስከፍቶ በህብረተሰቡ ላይ ቀልዶ
ሲወሳ የኖረው? በዓለም ላይ የተከበሩ የተባሉ ከያኒዎች መንበር ናፍቀው አይታዩም(በጣት ከማይቆጠሩትና ከከሸፈባቸው በስተቀር)የሕዝብ
ከያኒያን መንበራቸው የሚወዱት የሚወዳቸው ህዝብ ልብና ጥበባቸውን የሚያሳዩበት መድረካቸው ነው፡፡ ብዙ እርቀት መሄድ
አያስፈልግም እነ በዓሉ ግርማ፣ብርሃኑዘሪሁን፣ የክብር ዶ/ርከበደ ሚካኤል፣ ሀዲስ ዓለማየሁ፣ ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድኅን፣ወጋየው
ንጋቱ፣ የፓርቲ አሽከር፣ካድሬ፣መንበር ናፋቂ ሆነው አይደለም፡፡የህዝቡን ስሜትን ስለተረዱ፣የህዘቡ ስቃይ የእነርሱ ስለሆነ፣ጨ ቋኝንና
አምባገነን ገዢን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ በብዕራቸው ሲሸነቁጡ በቃላት ሲገርፉ እነዲህ እነደዛሬ ዲሞግራሲያዊ ሰብአዊ መብት
ተቀዳጅተናል ተብሎ አቦ ከበሬ ሳይደለቅ ነው በእሳት ላይ እየተረማመዱ የህዝባቸውን ብሶት በብዕራቸው እየከሸኑ ሁኔታው ሲመች
ፊት ለፊት ሁኔታው ሲያመር በፈሊጥ፣ በተምሳሌት ጆሮ ያለው ይስማ ስላሉ ነው፡፡
እኔን የሚገርመኝ ከያኒያን ሥራዎቻቸው በየትኛውም መልኩ ይምጣ ወደ ገንዘብ
የሚቀይርላቸው ይሄው ከመቀነቱ እየፈታ እየራበው ርሃቡንየገለጸለትን አደባባይ ያወጣለትን ከያኒ ሥራ በገንዘቡ በመግዛት ነው፡፡
በየትኛውም ነመንገድ ይሁን የከያኒን ሥራ መንግስት ገንዘብ አውጥቶ ሲገዛ አላየሁም(በእርግጥ ገንዘብ የሚገኝበትን ወይም ከህብረተሰቡ በስልት የሚሰበሰብበትን ሁኔታ ሊያመቻች ይችላል፣ሸነጥከኝ
ምርጥ አሽከር ብሎ አንድ ጥገኛ ባለሃብት መኪና ሊሸልም ቤት
ሊሰጥ ይችል ይሆናል!! ዘለቄታ የሌለው ባዶ ሽልማት!! ግን የትኛውንም ያህል ቢሸለም ከህዝብ ሽልማት የበለጠ ማንም ቱጃር ነኝ
የሚል ግለሰብ ወይም ቡድን ዘለቄታዊ ሽልማት አይሸልምም! ህዝብ
የሌለው ገንዘቡን ብቻ አይደለም የሚሸልም! ህይወቱንም ጭምር እንጂ!!! ህዝብ የሚሸልምህ ነፃነትህንጭምር ነው! ምክንያቱም ነጻነት ለማይሰማቸው መሪዎች አሽከር የሆነ ከያኒ ነጻነት ሊሰማው
አይችልም፡፡)ለገንዘብ እንኑር ብንል ዋናው ነገር ገንዘብ ይዞ መገኘት ነው ቢባል እንኳን የህብረተሰቡን ስሜትና ቁስልን መከየን
ሀብት ብቻ አይደለም ዝናንም ያከናንበናል፡፡የቅርብ ጊዜ ምሳሌን
ማየት ይቻላል አርቲስት ቴዲ አፍሮ ለዚህ ህዝብ አኮ የተለየ ተአምር ስርቶ አይደለም፤ ወጣት ሽማግሌ ልጅ አዋቂ ሴት ወንድ
ሳይል ለዚህ አቀንቃኝ ከወንበር እየተነሳ አድናቆቱን የቸረው በፍርድ ቤት በእስር ቤት እነደ የፖለቲካ መሪ አትፍራ እውነት
አይሞትም በማለት የአርቲስቱ ጉዳይ የእነእርሱ መሆኑን በተግባር ያሳየው፡፡ የፓርቲ አሽከር፣ካድሬ ወይ ሆዳም ስለሆነ
አይደለም፡፡ የእርሱን ሥራ ከመደበኛ ዋጋ ሃምሳ እጥፍ በመጨመር በሽሚያ የገዛው የእርሱ ኪነት የህብረተሰቡን ሥቃይ መንግሎ
ወዲያ የሚጥል ሆኖ ወይም የህይወት ፍሬ ሆኖ አይደለም እኮ!! አንድ ነገር ብቻ ነው ያለው ተስጦውን ዕውቀቱን ሞያውን ለፍቅር፣
ለነፃነት፣ በደለን ሥለማቆም፣በዳይን ለመገሰጽ፣ አድላዊነት ክፉ ስለመሆኑ፣ በህሊና ስለመኖር አሸናፊነት፣ መነጣጠል ብስለት
አለመሆኑ፣ታሪክ የሁሉም ነገር መሰረት ስለመሆኑና ፍቅር አሸናፊ መሆኑን ስለሰበከበት ነው፡፡ አንድ ልጨምር ይሄ ህዝብ እኮ ብዙ
መስዋትነት የሚፈልግ አይደለም! አላስፈላጊ መስዋትነት ይገባዋል! በባዶ እጅ የጦር ሜዳ ላይ ፉከራ ጠቀሜታ እንደሌለው ከኛ
ቀድሞ ያውቃል፡፡ብቻ ሞያችሁን፣ ተሰጦአችሁን ተጠቅማችኑ ለኛ አገልግሉን ነው ጥያቄው!
በቅርብ ጊዜ አንድ ወጣት ፀሀፊ መጣ ዴርቶጋዳ ብሎ ፃፈ፤ በድርስቱ
ኢትዮጵያ ያለችበትን ሁኔታ እንግዳ በሆኑና ግራ በሚያጋቡ ሥሞች አንዳንዴም ህዝቡ ስለእርሱ ሊሰማ የናፍቀውን ፣ለኢትዮጵያ
መመኪያና የንጹህ እውነተኛ ኢዮጵያዊ ሰምን በስልት እየተጠቀመ
በምናቡ የሳለውን አኛ የምንገምተውን አካፋን አካፋ ማለት ሳያስፈልገው በጥበብ ያለንበት ሁኔታና ቦታን ጠቆመን የማይታወቅ ሰው
ታወቀ! ስለዚህ መጽሃፍና ስለዚህ ፀሐፊ ያለምንም የማስታወቂያ
ወጪ አንባቢው ያልተከፈለው አስተዋዋቂ ሆኖ በኢትዮጵያ ምድር ተወራ! ፀሃፊው ኪለቱ ስልስቱ አያለ ያለአታሚ ችግርና ያለአንባቢ
እጥረት ድርሰቶቹን አከታታለ! አንባቢው የዚህን ፀሐፊ ሥራ የመጀመሪያውን ሥራ ይስተካከል አይስተካከል እምብዛም
አላስጨነቀውም እንግዳ የመጸፅሀፍት ርዕሶች እየተጠቀመ ቁጥራቸው
ቀላል የማይባል የድርሰት ሥራዎች ሠራ፡፡አሽከር መሆን ሳይገባው
ጌታ ሆነ፣ ገንዘብ የማግኘት ፍላጎትም ካለው የሚፈልገውን ገንዘብ በህዝቡ ፍቃድ ከህዝቡ አገኘ፡፡ ከምንም ወደ የሆነ ነገር፣ ከማይታወቅ ሰው በኢትዮጵያ ስነ ጹህፍ የሚጠቀስ ሰው!
አያችሁ ህዝባችን ብዙ እንደማይፈልግ!? የሚገርመው ደግሞ የእነዚህን አይነት አሸከርነት የማያሳዩ ከያኒያን ሥራ አሽከር
የሚኮንላቸው ባለሥልጣኖችሁላ የሥራዎቻቸው አሽከሮች፣አድናቂዎች በየጓዳቸው የሙዚቃዎቻቸው አድማጮቻች፤ የመጽሐፍታቸው አንባቢዎች
ናቸው! ታዲያ ማን ነው አሽከር ወይስ ማን ነው ጌታ? ወይ ማነው ሎሌስ!?
በዝራው አሻግሬ
በዝራው አሻግሬ