የህግ ታራሚዎችና እርቅ ጉዳይ
አሁን አሁን
ስለ እርቅና ስላም የሚወራበት መድረኮች ስጋትና ውጥረት
የሚታይባቸው ከባቢዎች ሆነዋል' ለወትሮ እርቅና ሰላም ማንንም የሚያግባባ ጉዳይ መሆኑ የሚታወቅ
ቢሆንም'
ዛሬ
ጥቅምት 8 2007 ነው ይህን ለ2ኛ ጊዜ የተጠራሁበትን ስብሰባ መቅረት የለብኝም ብዬ እየተጣደፍኩ ነው' ጎጃም በረንዳ አካባቢ ሆኜ ወደ ስብሰባው ቦታ ራስ ሆቴል የሚወስደኝ ታክሲ እየፈለኩ ነው' አልፎ አልፎ እኔ በመፈልገው መንገድ የሚሄድ ታክሲ ሲመጣ ሰዎች
ተሽቀዳድመው በመጋፋት ይገባሉ' አንድ ሰው ግን የተወሰነ እየሞከረ ወደ ኋላ ይቀራል' ከእኔ ጋር ወደ ኋላ መቅረቱን አዬቼ ሁኔታውን አስተዋልኩት' ባጋጣሚ አንድ ታክሲ
እኔ ያለሁበት ቦታ መጥቶ ሲቆም ዘልዬ ገባው' ወንበር ይዤ
ከተረጋጋው በኋላ ሁኔታውን ስቃኝ ቅድም አጠገቤ
የነበረው ሰው ተከትሎኝ ታክሲው ውስጥ መግባቱን አየሁ'
አምባሳደር
አካባቢ ስደርስ ወራጅ አለ ብዬ ስወርድ የቅድሙ ሰው አብሮኝ ወረደ' ምንድነው ነገሩ ስለ ታራሚና እርቅ እወያያለው ብዬ በቅጽበት የህግ ታራሚ ልሆን
ነው እንዴ? አልኩ' ከአሁን በኋላ ከተከተለኝ
እፋለመዋለው አልኩና በኢትዮጵያ ሆቴል ጀርባ በቅያስ ሄድኩኝ' በላየን ሬስቶራንት አጠገብ ስወጣ በርቀት ወደ ብሔራዊ ቲያትር አስፓልት ሲሻገር አየሁት' ቀስ ቀስ እያልኩ በመሄድ በተቃራኒ መንገድ ስጋዝ ቆይቼ በራስ ሆቴል ፊት ለፊት ስደርስ አስፓልቱን አቋረጥኩ' አሁን ሰውየው
አይታየኝም' የሆቴሉ በራፈ ስደርስ
ዙራዬን ቃኘሁና ጥበቃውን ለስብሰባ እንደመጣው ስነግረው በጀርባ
በኩል እንድሄድ ጠቆመኝ' በጀርባ በኩል ገብቼ አንዲት ሴትን የስብሰባው አዳራሽ የት እንደሚገኝ ስጠይቃት ፎቅ ላይ ውጣ አለችኝ' ፎቁን ወጣሁ' አንድ ኮሪደር
ላይ “ስብሰባ ስለሆነ ጸጥታ ይከበር”
የሚል በወረቀት የተለጠፈ ማሳሰቢያ አዬቼ የስብሰባ አዳራሽ የመሰለኝ አንድ
ገርብብ ያለ ከፍል ጋር ሰጠጋ ሰዎች በአንድ ረጅም የመጠነኛ
ስብሰባ ጠረጴዛ ዙሪያ ተኮልኩለው ሸሚዝና ከረባት በበዛበት አለባበስ ዘና ባለ ሁኔታ
ተቀምጠው እየተሳሳቁ ሰፊ ኤኤልሲዲ ስክሪን ቴሌቪዝን እያዩ ያለ ተራ በመሽቀዳደም የየራሳቸውን አስተያየት ይሰጣሉ' ዘና ተብሎ የሚደረግ ስብሰባ ነው እንዴ የተጠራሁት አልኩኝ ለራሴ! በሩን ገፋ አድርጌ ልገባ ስሞክር
ከውስጥ አንድ ሰው ጨዋታውን አቋርጦ ጌታዬ! ይህ የእርሶ
ስብሰባ አይደለም በማለት ወደ ውስጥ ሳልዘልቅ ከበር አሰቀረኝ'
ሌላ
ልሞክር አልኩና በኮሪደሩ ወደ ሌላ ኮሪደር ማምራት ስጀምር ከሶስት እርምጃ በኋላ
የስብሰባ ድምጽ ሰማው' ይሄ በርካታ ተስብሳቢ ያለበት ትልቅ አዳራሽ መሆኑን በሰፊ መጋረጃ በተጋረደው ክፍት በር ለመመልከት ችያለው' አንድ ሁለት እርምጃ አንደተራመድኩ የእድገትና ትራንሰፎርሜሽኑ
ዕቅድ ማሳከታቸን...መሰል ንግግሮች ስሰማ በተሳሳተ
ቀጠና ወስጥ እንደገባው ገባኝ' በድጋሚ ከስብሰባው ልቀር ለመወሰን ትግስቴን ተፈታተነኝ' ለምን በነጥብ (specific)የስብሰባ አዳራሹን የጥሪ ወረቀቱ ላይ አልጠቀሱም አልኩ አርፍጄ መምጣቴን እንደ ስህተት
ሳላይ' የመበሳጭት ነገር እየታየብኝ
ደረጃውን ስወርድ አንዲት የጽዳት ስራተኛ አገኘውና ከዚህ
ሌላ ስብሰባ አዳራሽ አለ እንዴ አልካት? ሌላኛው ህንጻ አዲሱ መሰብሰቢያ አለ ብላ ቦታውን ጠቆመችኝ'
የስብሰባ አዳራሹን እንደደረስኩበት ሳረጋግጥ በአንድ
ቀን በተመሳሳይ ሰዓት በአንድ ሆቴል ሁለት& ሶስት ስብሰባ ምን መጣ አልኩ?! ትዝ ሲለኝ ለካ
ምርጫ ደርሷል! ልክ ነው! ለዛ
ነው ስብሰባ በስብሰባ የሆነው አልኩ' ወዲያው ቀድም ሲል ታክሲ
ላይ አብሮኝ ሲወጣ ሲወርድ የነበረው ሰው በእጁ አጀንዳ ነገር ይዞ
የነበረ መሆኑ ትዝ አለኝና ይሄኔ
እኮ ከእነዚህ ስብሰባዎች አንዱ ላይ ተሳታፊ ይሆናል አልኩና
ቀደም ብሎ
በውስጤ ተፈጥሮ የነበረውን ስጋት በጥቂቱ ቀረፍኩኝ'
አዳራሹ
ውስጥ ሶስት ሰዎች መድረክ ላይ ከተሰብሳቢዎች ፊት ለፊት ተቀምጠው ስለ
እርቅ እያወሩ
ነው' ምንአልባት ይህ መድረክ የሚያወራው
እርቅ ታራሚዎችን የተመለከተ ስለሆነ ውጥረት እንደማይኖረው መገመት አያዳግትም' በርካታ ተሰብሳቢዎች በስብሰባው አዳራሽ ተገኝተዋል' በአብዛኛው የህግ ባለሙያ&የሃይማኖት ሰዎች&የተለያዩ ሲቪክ ማህበራት መሪዎች&የሀገር ሽማግሌዎች&ታዋቂ ሰዎች& የፖሊስ ድርጅት ተወካዮች
&የማረሚያያ ቤት ተወካዮች ናቸው' እኔም ጉዳዩ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ የሚመለከተኝ ስለሆነ
የዓለም የዕርቅና የሰላም ግብረ ሰናይ ማህበር የህግ ባለሙያና ጋዜጠኛ በሚል
ማእረግ የግብዣ ወረቀት ተሰጥቶኝ በስብሰባው አዳራሽ ተግኝቻለው'
መድረኩ ዘውትር በየስብሰባው የምናየው
የዛሬ ስብሰባን ልዩ የሚያደርገው አገራችን ምናምን ምናምን የሚል አካል& የክብር እንግዳችን የተከበሩ& በመሃላችን እነ እከሌ ይገኛሉ መሰል ንግግሮችና መጀመሪያ
የተከበሩ እከሌ አጭር ንግግር ያደርጉልናል& በመቀጠል ደግሞ አቶ እከሌ የእንደዚ እንደዚ ምናምን የሚል አሰልቺ ንግግርና የተንዛዛ ሥነሥርዓት ሳይታይ መድረኩ ላይ የሚታዩት ሰዎች
ወደ ዋና ጉዳያቸው ሰተት ብለው ገብተዋል '
ከሦስቱ ሰዎች መካከል ለተሰብሳቢዎች በተያዘው ርዕስ ላይ ማብራሪያ የሚሰጡትን
ባለሙያዎች መድረኩን በመምራት እንቅስቃሴ የሚያደርጉት ፕሮፌሰር አህመድ
ዘካሪያ የመግቢያ ንግግር አድርገው ተራውን ማብራሪያ
ለመስጥት ተዘጋጅተው ለአሉት ለፕሮፌሰር ታረቀኝ አቀበሉ ፔሮፌሰር
ታረቀኝም የመጀመሪያው ተናገሪ ግለሰብን በማስተዋወቅ
የማብራሪያ ቅድሚያውን አሳልፈው ሰጡ'
የመጀመሪያው
ተናጋሪ አቶ ጋረደው አሰፋ ይባላሉ' በግጭት አፈታት ዙሪያ እንደተማሩ &እንደሰሩና ጥናት እንዳደረጉ በተጨማሪም በዓለም ላይ ካሉ
እንደ አውሮፓ&ደቡብ አፍሪካ&ኬንያንና አትዮጵያን
ጨምሮ የ60 ሀገራት ማረሚያ ቤቶች መጎብኘታቸው ተገልጻል' አቶ አሰፋ ታራሚ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ትርጉም በመስጠት ማብራሪያቸውን በፕሮጀክተር በመታገዝ ጀመሩ'
ታራሚ ማለት ወንጀል ሥለመስራተቸው:- 1/ማስረጃ የቀረበባቸው& 2/ማስረጃ ቀርቦባቸዋለል የተባሉ
እና&3/ የቀረበባቸው ክስን ማስተባበል ያልቻሉና ተመጣጣኝ ቅጣትና
እርማት በመውሰድ ላይ ያሉ ናቸው' ሲሉ ገልጽዋል'
በተመራማሪው
ገለጻ ላይ ስፋ ተደርገው ያልተገለጹ ግን መገለጽ የነበረባቸው
የታራሚዎች አይነት ዝርዝር ነበሩ' ለምሳሌ ማስረጃ የቀረበባቸው ሲባል ትክክለኛ ማስረጃ ቀርቦባቸው ነው? በማሰረጃ ከጥርጣሬ በላይ ወንጀል መፈጸማቸው ተረጋግጦ ነው? ማስረጃ ቀርቦባቸዋል የተባሉ ሲባል@ የቀረበው ማስረጃ ትክክል አይደለም ማለት ነው? ወይስ በሀሰት የተፈበረከ ክስና ማሰረጃ የቀረበባችው
ሰዎች ይሆኑ? አሊያ በቀረበባቸው ማስረጃ ሳያምኑ በዳኞች በተገቢው ሁኔታ ማሰረጃ ቀርቦባችሃል የተባሉ ናቸው? የቀረበባቸው
ክስን ማስተባበል ያልቻሉ የተባሉት በራሳቸው ተከራክረው አቅም አነሳችው ነው? ወይስ ጠበቃዎቻው ደካማ ሆነው? አሊያ ከባልገሮቻቸው ጋር ተመሳጥረው? ወይስ መንግስት ጠበቃ ሊያቀርብላቸው ባለመቻሉ ወይም ጠበቃ አያስፈልገንም
ብለው ራሳቸው ተከራክረው ራሳቸውን መከላከል ያልቻሉ ናቸው? የሚሉት ቢመለሱ ገለጻውን የበለጠ ገላጭ ያደርገው ነበር'
በሀገራችን
120 ማረሚያና እስር ቤቶች አሉ' በእነዚህ እስርና ማረሚያ ቤቶች 100,000.00 ወንድና ሴቶች በእስር ላይ የሚገኙ
ሲሆን ከእነዚህ ሰዎች ጋር በተያያዘ ምንም ጥፋት ሳይሰሩ 800 የሚደርሱ ህጻናት ከወላጆቻቸው ጋር ታስረዋል' በማለት በመግለጽ በተጨማሪም እሥር ቤቶችና ማረሚያ ቤቶች የሚሉ ቃሎችን: እስር ቤት(prison)ማለት
ደረጃውን ያልጠበቀ& ለመቆያነት የሚያስቸግርና
ያልተማሏ ሲሆን ማረሚያ ቤት(correction center)ግን ደረጃውን የጠበቀ ለታራሚዎቹ የተለያዩ የሚያስፈልጉአቸው ነገሮች የተሟላበት' አንዳንዴ
ማረሚያ ቤት ልኑር አይባልም እንጂ!
አትውጡ አትውጡ የሚያሰኝ ነው በማለት ማብራሪያ
ሰጥተዋል'
አጥኚው በጥናታቸው ማካተት የነበረባቸው ወይም አካተውት ከሆነ ሳይገልጹ ያለፉት የእኛ አገር ማረሚያ ቤቶች በማረሚያ ቤት ደረጃ ነው ያሉት? ወይስ በእስር ቤት ደረጃ? ምን ያህሉ ማረሚያ ቤት ናቸው? ምን ያህሉስ እስር
ቤት ናቸው? እርሳቸው 120 እስር
ቤት አለ ሲሉ አድራሻቸው በይፋ የማይታወቁ የስውር እስር ቤቶች
አሉ እያሉ የተለያየ አካላትና ግለሰቦች በመንግስት ላይ
የሚያቀርቡትን ክስ የሚያሳዩ እሥር ቤቶች በዚህ ዳታ ላይ ተካተዋል? መጠናት ያለባቸው ወይም ከተጠኑ መገለጽና መብራራት ያለባቸው ጉዳዮች ነበሩ'
አቶ ጋረደው ለታራሚዎች ይቅርታና ምህረት ማድረግ የተጀመረው
ከአጼ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ጀምሮ መሆኑን በመግለጽ በኢህአዴግ የአገዛዝ ዘመን በሰባት እመት ውስጥ ብቻ በአገራችን ታይቶ በማይታወቅ
መልኩ 100,000.00 የሚደርሱ የህግ
ታራሚዎች በይቅርታና በምህረት መለቀቃቸው ይበል የሚባል ገንቢ ተግባር ነው ብለዋል' እኔ እኔ በአንጻሩ ደግሞ እስረኛው ለምን በዛ? ፈጸሙ የተባለው የወንጀል አይነትስ ምን ምን እንደሆኑ እግረ መንገዳቸውን
ቢገለጹ በገለጻቸው ላይ ያሳዩት የነበረውን ቁርጠኝነት የበለጠ ትረጉም ይሰጠው ነበር እላለው'
ታራሚ
ማለት በታራሚዎችና በህብረተሰቡ ዘንድ ያለው ትርጉም በገለጻው የተካተቱ ሲሆን ገለጻው መሰረት ያደረገው አነኳራ ጉዳይ የሆነውን የነብስ ግድያ የፈጸመ ሰው ቅጣቱን
ጨርሶ ሲወጣ ከህብረተሰቡ ለመቀላቀል የሚገጥማቸውን ተግዳሮት& ሥለ ምህረትና ይቅርታ ጉዳይ ነው ማስረዳት የቀጠሉት'
እርቀሰላም ማለት እውነት&ምህረት&ፍትህና ስላም ነው በማለት
አስረድተዋል' ያለ እውነት በውሸት እርቅ ሠላም የለም& ያለምህረትና ፍትህ እርቅ የለም@ ተበዳይ ምህረት
ማድረግ አለበት@ የተበደለውንም ሊካስ ፍትህ ሊያገኝ ይገባል& ያለስላም እርቅ የለም በማለት አብራርተዋል'
ገለጻውን
ከአቶ ጋረደው
ጋር በመሆን የሚያካሂዱት ፔሮፌሰር ታረቀኝም አቶ ጋረደው ሳይዘረዘሩት ያለፉትን ጉዳዮችን በተወሰነ በማብራራት የባህላዊ እርቀ ስላም ፋይዳን ለማስረዳት
ሞክረው የሻይ ሰዓት በማለፉ ማብራሪያቸውን በአጭሩ አጠናቀዋል'
ከሻይ እረፍት
በኃላ የተሰበሳቢው ጥያቄና አስተያየት ይካሄዳል በተባለው ፕሮግራም መሰረት ለመንደርደሪያ
እንዲሆነ በቃሊቲ በእስር ያሳለፉን አቶ ኤሊያስ የተባሉ
ግለሰብ መድረኩ ላይ በመቅረብ በእስር የነበሩበት ክፍል ዞን ሁለት
የሚባል እንደሆነና አራት ክፍል ያላቸው መሆኑን በመግለጽ በአንድ ክፍል ውስጥ 500 ሰው የሚኖር መሆኑን& ሻይ በተቆረጠ የሃይላንድ መጠጫ እንደሚጠጡና በሀሰት ክስና ማስረጃ ቁጥራቸው
ቀላል የማይባል ታራሚዎች በማረሚያ ቤቱ እንዳሉ አስረድተዋል' አቶ ኤሊያስ ከእስር ቤት ሲወጡ መድረኩን የሚመሩት የነበሩት ሙህራን ታራሚዎች ከእስር ሲለቀቁ የሚገጥማቸው ተግዳሮት ብለው ከገለጹት ጉዳዮች መካከል ቤት መፍረስና
ለፍቺ መዳረግ እኝህ ሰውም ላይ የደረሰ መሆኑን ገልጸዋል' ተሰብሳቢውን ፈገግ ያሰኘው አንድ ለአምስት የሚባለው ማረሚያ ቤትም ያለ መሆኑን አንድ ለሃያ አምስት በጋንታ&አንድ ለአምስት በስተመጨረሻም አንድ ለአሥር ተደራጅተው እንደሚንቀሳቀሱ መናገራቸው
ነው'
ተሰብሳቢው
ውስጥ በተለያየ ጉዳይ ልምድና እውቅት ያላቸው ሰዎች ያሉበት
መሆኑን የተረዳውት በገለጻው ላይ አሰተያይትና ጥያቄ ለመስጠት በተሰጠው እድል ለመጠቀመ በመነሳት ሀሳባቸውን ሲሰነዝሩ
ነው' አሁን ከአሉት ፍትህ ሚኒስትር በፊት ቀደም ብለው
የፍትህ ሚኒስቴር የነበሩት አቶ አሰፋ ከሲቶ& ኢንጂነር ታደለ ብጡል& አንጋፋው የማስታወቂያ ባለሙያ አቶ ውብሸት ወርቃለማው& የቪኮድ ዳይሬክተሬ አቶ ታደለ& አርቲስት ኪሮስ ኃይለ ሥላሴ & የፌድራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ተወካይ& ረዳት ኢንስፔክተር አሰፋ መዝገቡና መሰል ታዳሚዎች መታየታቸው ነው'
ለጥያቄና አስተያይት
መድረኩ ክፍት ሲሆን እድሉን ለማግኘት እኔን ጨምሮ
እጆች ሲዘረጉ ስዓት ያለን ትንሽ ነው በሚል ለተወሰኑ ሰዎች እድል የተሰጠ ሲሆን በሚሰነዘሩ ሀሳቦች ላይ መግቢያዬ ላይ
ስለ እርቅ ሰላም ማውራት ከባድ ነው ያልኩትን በሚገባ መረዳት ይቻላል' አስተያይት ሰጪዎቹ ወይም ጥያቄ አቅራቢዎቹ በአብዛኛው
ገለጻው ጥሩ ነገር እንደፈጠረባቸው በዚህ ጉዳይ ላይ የሚጠበቅባቸውን ለማድረግ ዝግጁነታቸውን ያረጋገጡበት ሲሆን ከጉልበታቸውን& ከዕውቀታቸው በላይ በገንዘብም ድርጅቱን እንደግፋለን የሚሉ ሀሳቦች የመጡ ሲሆን በተለይ እዚህ
ላይ ሳላነሳ ማለፍ የማልፈልገው ጉዳይ አስተያይት ለመስጠት እጃቸውን አየር ላይ አንሳፈው እድል ካገኙት ሴት በሁለተኛ
ተናጋሪነት አጠገቧ ባሉ ተሰብሳቢዎች ግፊት እድል ያገኘች በሙስሊም
አልባሳት በመጠኑ የተሸፈነች ሱአድ የተባለች
ወጣት ሰሜቷ እይተናጠ ይህንን አይነት ዓላማ ያላቸውን ድርጅት መደገፋ ወሳኝ እንደሆነ የማህበሩ መሪዎች ከፊት ለፊታቸው
ሊገጥማቸው የሚቸል ተግዳሮቶች እንደሚኖር በመግለጽ ሁላችንም ለዚህ
ዓላማ በቻለውን ድጋፍ ማድረግ ያለብን መሆኑን በመግለጽ የድርጅቱ
ዓላማን ለማሳካት 20,000.00 ብር ለመለገስ ቃል መግባቷ
ተሰብሳቢውን ያስደመመ ጉዳይ ነው'
እንዲህ
አይነት የመተባበር ስሜት እያይን በሌላ መልኩ የተወሰኑት ግለሰቦች በመድረኩ የተብራራውንና በአንድ አንድ ተሰብሳቢዎች የተገለጹትን ሀሳቦች ለመመከት ያደርጉት የነበረውን ሀሳብ ለአንባቢ ማሳይት ስለ እርቅ& ስለ ስለም& ስለ ታራሚና መሰል ጉዳዮች መወያየትና መስራት ምን ያህል ፈታኝ እንደሆነ በጥቂቱ ያሰገነዝበናል'
አንድ ሰው ከተሰብሳቢው መሃል እጃቸውን አነሱና ንግግር ጀመሩ' ከሶስት ዓመት በፊት የፍትህ ሚኒስቴር ነበርኩ ሲሉ ተሰብሳቢው ወደ ተናጋሪው መዞር ጀመረ' አቶ አሰፋ ከሲቶ
እባላለው በማለት የስብሰባው አካሄድ መደበኛ(formal) ያልሆነና ትንሽ ከተለመደ ውጭ በመሆኑ የተለያየ የሚመለከታቸው ሰዎች አስተዋጾ እንዳያደርጉ ሆኗል' ቢሆንም ኢመደበኛ(informal) ቢሆንም በማለት መልሰው የራሳቸውን ሀሳብ በማስተባበል
አስተያየታቸውን ቀጥለው በመድረኩ ላይ የተገለጸው ጥናት
ጥልቀት ይጎለዋል አሉ' በጥልቀት መጠናት ነበረበት በማለት ሀሳባቸውን በመሰንዘር በተለይ ፕሮፌሰር
ታረቀኝ ከጨዋነትና መበቃቀል ጋር አያይዘው የሰጡትን ማብራሪያ በመቃወም
ኢትዮጵያውያን ጨዋዎች ነን በማለት ለማስረዳት እንዲጠቅማቸው በማሰብ በሥራ
የገጠማቸውን አጋጣሚዎች ሲገልጹ አንድ ጊዜ አንድ በነብስ ግድያ ወንጀል የታሰረን ታራሚ ምህረት ልናደርግለት ወሰንና
ታራሚው ከእስር ብንፈታው በሟች ቤተሰቦች ሊደርስ የሚችለውን ብቀላ
ከግምት አስገብተን የሟች ወንድምን የወንድምህን ገዳይ የታሰረው ይበቃዋል ብለን ልንፈታው አስበናልና ምን ትላልህ ብለን ጠይቅነው' ምን ትላላችሁ እናንተ! ልትፈቱት ከአሰባችሁማ እኔ ነኝ ይዤው የምሄደው
ብሎናል በማለት መበቃቀል እምብዛም መሆኑን አስረዱ' በማያያዝ ደግሞ እንደዚሁ አንድ በነብስ ገድያ
ወንጀል ተፈርዶበት የእስር ጊዜውን አጠናቆ የወጣ ሰው@ የገዳይ ቤተሰብ ይገለኛል በሚል ስጋት መሣሪያ ገዝቶ ወደ መንደሩ ሲጓዝ የገዳይ ቤተሰቦች ሊበቀሉት ወደ እርሱ ሲያመሩ መንገድ ላይ ያገኛቸውና በጥይት ገደላቸው' ወደ ማረሚያ ቤት ሲመለስ ለምን ገደልክ ተብሎ ሲጠየቅ እኔ አይደለውም ጥፋተኛ!
መቼ ተታረቅንና በማለት ያለመታረቃቸው ለድጋሚ ግድያው መንስሔ መሆኑን መናገሩን አሰረድተዋል' እንደዚሁም
አሉ አቶ አሰፋ የማረሚያ ቤቱ ሰፊና አጥር የሌለው ማረሚያ ቤት ውስጥ
ያለ ታራሚ በእስር ላይ እያለ እርሻ ያርስ
ነበርና የእስር ጊዜው ሲጠናቅ ከእስር ቤቱ እንዲወጣ ሲነገረው አልወጣም ሽንኩርቴ አልደረሰም እዚህ ልቆይ ፍቀዱልኝ በማለት
አሻፈረኝ ይላል' ሁኔታውን በማየት ይህ ግለሰብ እንዲቆይ ተፈቅዶለት ሽንኩርቱ ሲደርሰ ጠብቆ
ከወሰደ በኃላ ወደ መንደሩ ሲገባ የሟች ቤተሰብ የገደለው መሆኑንና ሌሎች በስራ ልምድ አገኘሁት ያሉትን
የሚያሰደምሙ ታሪኮች ሲተርኩ ተሰብሳቢው በትኩረት እንዲያዳምጣቸው አድርገዋል'
አቶ አሰፋ በሚያስደምሙ ታሪኮች በማሰደገፍ ይናገሩ እንጂ ታሪኮቹን በሁለት ሳይድ
እያጣቀሱ በመግለጽ ከመድረኩ የተሰጠውን ማብራሪያ በስልት እየተቃወሙ ወይም ተሰብሳቢውን በገለጻው የተሰነዘሩትን ሀሳቦች እንደተገለጸው እንዳልሆነ ለማሳይት ሲሞክሩ
ነው ታዳሚው ያስተዋለው'
ሌላኛው ተናጋሪ ከማረሚያ ቤት የአሰተዳደሩ ተወካይ የሆኑ ግለሰብ ንግግራቸውን የጀመሩት እስር ቤት በሚል
የተገለጽውን ቃል አገራችን ከዓመታት በፊት እስረኛ የሚለውን ቃልና
ሁኔታዎች በማስተካከል ማረሚያ ቤት በማለት መጠራት ተጀምራል' በተለያዩ
ማረሚያ ቤቶችም ደረጃቸው የጠበቁና የተሟሉ የማረሚያ ቤት
ህንጻዎች ለመስራት ዕቅድ ተይዟል አሉ' የማረሚያ ቤት ቆይታ ልምዱን ለማካፈል የቀረበው ግለሰብ አንድ ለአምስት የተባለው አንድ ለአሥር በማቀናጀት የምንሰራው ቀደም ብሎ የነበረውን ሲጋራ
ማጨስ&ሀሺሽ መጠቀም&ጫት መቃመ መሰል ነገሮችን ለመቆጣጠር
የተጠቀምንበት ውጤትም ያገኘንበት አሰራር ነው በማለት ገልጸው በማያይዝ
ከግብረ ሰናይ ማህበሩ ጋር ተቀራርበው ለመስራት በተለይ ታራሚውች የእርማት ጊዚያቸውን
ጨርሰው ሲውጡ የሚገጥማቸው ፈታኝ ሁኔታ ያለና እኛም የምናስብበት ነው ይህ ማህበር የት እንዳለ እስከ ዛሬ አልታወቀም
ብለው የራሳችውን ሀሳብ በማከል አስተያየተቸውን አጠናቀቁ'
እኝህ
ተናጋሪ በለሰለሰ መልኩ የተወሰነ ማረም አለብኝ ባሉት መልኩ እስር
ቤት መባሉን በመቃወም የአጸፋ ምላሽ ለዘብ አርገው የወረወሩ ቢሆንም መልካም ግንኙነት መ/ቤታቸው እንደሚፈልግ ገልጸው በተወሰኑ በተቃወሙት ቃላት ለውጥረቱ ትንሽ አግዘዋል'
ቀጣዩ አስተያይት ሰጪ የቪኮድ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ታደለ ያቀረቡት የህይወት ልምዳቸውን ያማከለ ንግግር ነው' ከዘጠኝ ዓመት በፊት
በሞያዬ መምህር ነበርኩና የማስተምርበት ክፍል ወስጥ አንድ ሰው መጥቶ ልናነጋግርህ እንፈልጋልን አለኝ ቆይ ይሄንን የጀመርኩትን
ገለጻ ልጨርስ አልኩ@ ቆይ ደርሰው ይመለሳሉ ተባልኩና ወደ ፖሊስ ቢሮ ሄድኩኝ'
ከትንሽ ቆይታ በኃላ ህገ መንግሰታወዊ ሥርዓቱን ለመናድ የሚል ክስ ቀረበብኝና በዕለቱ ሳልመለስ ቀርቼ ዋሰ በመጥራት ነው የወጣሁት ካሉ በኃላ የማስተምርበትን
ትምህርት ቤትን ጨምሬ የተለያዩ አካላትን በመክሰስ ሁኔታውን ስከታተል በሰተመጨረሻ ፋይሉ ጠፋ ተብዬ ነው ጉዳዩ ለጊዜው የቆመው በማለት እንደዚህም እኮ አለ በሚል መንፈስ ያለውን ሁኔታ በስሜት አስረዱ' እግረመንገዳቸውን በአናሳ
ገንዘብ የተቋቋሙበትን ዓላማ ለማስካት የሚተጉትን የማህበሩ መሪዎች የገንዝብ ድጋፍ የሚያገኙበትን መንገድ በመጠቆም ከ1992 ዓም
ጀምሮ እንደተቋቋማችሁት ራሳችውን አላስተዋወቃችሁም እኔም አላውቃችሁም ነበር በማለት አስተያየታቸውን አጠቃለዋል'
አቶ ታደለ በንግግራቸው
ወቅት ያቀረቡት ታሪክና የሚታይባቸው ስሜት ከእሳቸው ቀደም ብለው የተናገሩት የመንግስት ተወካዮች በመድረክ የተገለጽውን ለማረም
ያደረጉትን ትንቅንቅ ምን እያላችሁ ነው መሬት ላይ ያለው እውነት እኮ
ይሄ ነው የሚል ይመስላል'
አንድ የሙስሊም ሃይማኖት መለያ
ባርኔጣ ያደረጉ ሰው ተራውን ያዙ' ንግግራችውን ምን እያላችሁ ነው! አገሩ ላይ እኮ ፍትህ
የሌለ ነው እያሰመሰላችሁ ያላችሁት! አገራችን ፍትህና ሰላም የተረጋገጠባት ሀገር ናት በማለት የተወሰነ ማብራሪያ በመስጠት የራሳቸውን ነጥብ በማስመዝገብ
ንግግራቸውን ቋጩ'
እኔም በይቅርታ
እርቅና ሰላም ላይ በሀገሪቱ አሉ የተባሉ ከዚህ ጉዳይ ጋር ግንኙነት ያላቸው& ጥናት የሰሩና የሚመለከታቸው አካላቶችን
በመጋበዝ ልምዳቸውን እንዲያካፍሉ ያደረኩ መሆኑ ይታወቃል' የሀጋራችንን የተለያዩ የሽምግልና ሥርዓት ለአድማጩ በማስተዋወቅ ያልተግባቡ
ሰዎችን በአየር ላይ በግጭት መፍታት ልምድ ያካበቱ& ትምህርታቸው እዚህ ላይ የሆነና በዚህ ላይ የሚሰሩ ግለሰቦችን ከሀገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት
ሰዎችን በማካተት የእርቅ ሥራ ‹ሚዛን› በሚል ርዕስ እኔና ባልደረቦቼ በአንድ ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያ ላይ የአየር ሰዓት በመከራየት በአገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ በግል አዘጋጅተን ከ2001ዓም እስከ 2003 ዓም ድረስ በማዘጋጀት ያቀረብን መሆኑ ይታወሳል' በዚህ ወቅት በተለይ እኔ
እንደ ዋና አዘጋጅነቴ የገጠመኝን ውጣ ውረድ
እዚህ ላይ ማቅረቡ ጠቃሚ ነው ብዬ በማሰብ በውይይቱ ላይ አስተዋጾ ለማድረግ እጄን በመዘርጋት ከመቀመጫዬ ብድግ ቁጭ እል ጀመረ' ይሁንና የስብሰባው ማጠቃለያ ሰዓት ተዳርሷል በመባሉ ለተነሳው
ጥያቄና አስተያየት ገለጻ አቅራቢዎች ምላሽ እንዲሰጡ ከመድረኩ
መልዕክት በመተላለፉ ውይይቱ ብዙ አስተያየት የሚሰጡ ተሰብሳቢዎች እያሉ
ድምጽ ማጉያው ወደ መድረኩ ዞረ'
መድረኩ ላይ ገለጻ ከሚያደርጉት መካካል ጥናት ያቀረቡት አቶ
ጋረደው ማረሚያ ቤትና እስር ቤት የሚለው
የእንግሊዘኛው ፕሪዝን የሚለውና ማረሚያ ቤት ኮሬክሽን ሴንተር የሚለው ነው አዲስ ነገር የለውም በማለት አስረድተው በማስከተል
አቶ አሰፋ የገለጹት የታራሚዎች ኬዞች መካከል እሳቸው በኃላፊነት በነበሩበት ጊዜ ለእርሳቸው ያቀረብኩትና እሳቸው ገብተውበት በጋራ
የሰራንበት እንዲሁም እኔ ባለፈ ጊዜ ለገለጻዬ የተጠቀምኩት ነው በማለት የአቶ አሰፋ የተለየ ገጠመኝ እንዳልሆነ በመግለጽ ሌሎችንም የተነሱ ጉዳይችን
ጨምረው በጥድፊያ ለመመለስ ሞክረዋል'
ለዚህ
ጹህፍ ማዘጋጀት ይረዳኝ ዘንድ መሰረታዊ የሆኑ የውይይቱ አንኳር ጉዳይ
ናቸው ያልኳቸውን አስተያየትና ማብራራያዎችን ለማሳየት የሞከርኩ ሲሆን አንድአንድ የተደጋገሙና ውጥረት አለፈጥሩም ያልኳቸውን አስተያይትና
ማብራሪያዎች ጹሁፉን እንዳያስረዝምብኝ አላነሳቸውም' ሌላው የዓለም የዕርቅና የሰላም ግብረ ሰናይ ማህበር ይህንን ፕሮግራም ከፍተኛ ድካም አድርጎ አዘጋጅቶ በግማሽ ቀን ውሰጥ መጠናቀቁ
ተጀመረ አለቀ ሁኔታ ተፈጥራል' ጥናት አቅራቢዎችም በዝርዝር ሁኔታ እንዳያቀርቡ የሆነና ተሳታፊውም በሰፊው
ጉዳዩ ላይ እንዳይወያይ የሆነ ሲሆን ሙሁራኑን ሆነ ተሰብሳቢውን በደንምብ
ሳንጠቀም ባክነውብናል ማለት ይቻላል'
ሲጠቃለል
በሰላም እርቅና ይቅርታ ላይ መሥራት ከዓለማዊ ጠቀሜታው ባሻገር መንፈሳው ጠቀሜታው የትየለሌ ነው' ስላም እርቅና ይቅርታ ላይ የሚሰራ
ግለሰብ ሆነ አካላት በምንም መንገድ የራሰ ጥቅምን የመቀላቀል ነገር ጉዳዩ አይስማማውም& እውነት ከሌለ አሁንም እነዚህ ጉዳዮች
ፋይዳ ቢስ ናችው& ለሰላም የቆመ ለእርቅ የሚሰራ
የሚፈራ ከሆነ ምድቡ እዚህ አይደለም& ስላምና እርቅ ጦረኛ ካልሆነ በስተቀር ባልጋራ የለውም& የሰላምና የእርቅ መንገድ መቻቻልን የሚጠይቅና መንገዱ ስፖንጅ ላይሆን
ይችላል' ቢሆንም በምንም መንገድ የትኛውም
ልዩነት ይኑር
የሰላም ሀሳብ ያቻችላል& በምንም መንገድ ስለስላም ስለ እርቅ ስለይቅርታ የሚሰበክበት ቦታ ውጥረት
ሊሰፍን አይገባም' እርቅና ሰላም የግጭቶች ሁሉ መፍቻ
ቁልፍ ነው'
በዝራው አሻግሬ